ሩሲያን በማቋረጥ አውሮፓን ከቻይና የሚያገናኘው የ2 ሺህ ኪሎ ሜትር ማሳለጫ መንገድ ግንባታ እንዲከናወን ከሩሲያ መንግስት ባለስልጣናት ፈቃድ መሰጠቱ ተነገረ፡፡

ሜሪዳን የሚል ስያሜን ያገኘው እና የ2 ሺህ ኪሎ ሜትር የሚረዝመው መንገድ ሩሲያ ከካዛኪስታን በምትዋሰንበትን ምዕራባዊ ክፍል የሚያቋርጥ ነው፡፡

ይህ የማሳለጫ መንገድ ከአውሮፓ ወደ ቻይና የተለያዩ ምርቶችን ለማመለስ ተመራጭና አጭሩ የአስፓልት መንገድ እንደሚሆን ተነግሯል፡፡

የሩሲያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴሚትሪ ሜድቬዴቭ በመንግስትና የግሉ ሴክተሮች ባለው ስምምነት መሰረት የፕሮጀክቱን የመጀመሪያ ደረጃ ዕቅድ ማፅደቃቸው ተነግሯል፡፡

ለዚህ መንገድ ግንባታ 9 ነጥብ 4 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር እንደሚያስፈልግ የተነገረ ሲሆን፥ ለመንገድ ግንባታ ከሚያስፈልገው መሬት 80 በመቶ ግዥ መፈፀሙ ተጠቁሟል፡፡

አዲሱ መንገድ አውሮፓውያን ከመካከለኛው እስያና ምዕራብ ሩሲያ ጋር የሚገኛኙበትን ሁኔታ በእጅጉ ያሻሽለዋል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡
የመንገድ ግንባታው ፕሮጀክቱ በአካባቢው መሰረት ልማትን እና መንገዶችን ለማሳደግ የተያዘው ውጥን አንድ አካል እንደሆነ ነው ሲ ኤን ኤን በዘገባው ያሰፈረው፡፡

(ኤፍ.ቢ.ሲ)

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ደመቀ መኮንን በፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሚመራ የአውሮፓ ህብረት ልዑክ ጋር ተወያዩ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *