“Our true nationality is mankind.”H.G.

የደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ግምገማ ሂደቱን በተመለከተ የቀረበ አጭር ማብራሪያ፦

የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) ማዕከላዊ ኮሚቴ ከሰኔ 28/2011 ዓ.ም ጀምሮ ልዩ ስብሰባውን እያካሄደ ይገኛል፡፡ በውይይት መድረኩም አገራዊ እና ክልላዊ፣ ፖለቲካዊ ሁኔታዎችን በዝርዝርና በጥልቀት እየገመገመ ይገኛል፡፡ በክልሉ ህዝቦች የተነሱ የአደረጃጀት እና የመልካም አስተዳደር ጥቄዎችን አስመልክቶ ማዕከላዊ ኮሚቴው ፍፁም በሆነ በሰከነና በኃላፊነት መንፈስ እየተወያየ ይገኛል፡፡

ውይይቱም እጅግ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ በሳል በሆነ መንገድ እየተካሄደ ያለ ሲሆን የህዝቡን የጋራና ዘላቂ ጥቅሞችን እንዲያረጋግጥና የተጀመረው የለውጥ ጉዞ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚያስችል ውይይት ማዕከላዊ ኮሚቴው እያካሄደ ይገኛል፡፡

ደኢህዴን በክልሉ ህዝቦች የተነሱ የአደረጃጀት ጥያቄዎችንም አስመልክቶ ዝርዝር እና ሳይንሳዊ በሆነ አግባብ ሲያስጠና በቆየው የጥናት ውጤት ላይ ማዕከላዊ ኮሚቴዉ እጅግ ኃላፊነት በተሞላበት አኳሃን እየተወያየ ይገኛል፡፡ በክልሉ ህዝቦች የተነሱ ጥያቄዎች በመሪ ድርጅቱ ደኢህዴን እና በህዝቡ ፍቃድና ይሁንታ ብቻ ዘላቂ መፍትሄ የሚሰጠው ነው፡፡

ማዕከላዊ ኮሚቴው ልዩ ስብሰባውን ሲያጠቃልል ለአባላቱና ለክልሉ ህዝቦች እንዲሁም ለደጋፊ ኃይሎች ዝርዝር መረጃ የሚሰጥ ይሆናል፡፡ የክልሉ ህዝብም በሚቀርቡ የመፍትሄ ሐሳቦች ላይ በየደረጃው በሚዘጋጁ የውይይት መድረኮች እንዲሳተፍ የሚደረግ ይሆናል፡፡ ከዚህ ውጪ በተለያዩ ሃይሎች በሚሰራጨው ውዥንብሮች እና የተሳሳቱ መረጃዎች ሳይደነጋገር በትግስት እንዲጠብቅ ደኢህዴን ጥሪውን ያስተላልፋል።

የደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   አገርን የከዱ ተደመሰሱ፤ የሳተላይት መገናኛና መድሃኒት " ጁንታው" እጅ ሳይገባ ተያዘ
0Shares
0