የኤፈርት ኩባንያዎች የባለቤት መብት ቀደም ሲል የትግራይ ህዝብ ነው ይባል ነበር ።ቆዮት ብሉ የታጋዮች የጦርነት ኣካል ጉዳቶኞች ተባለ ። ጥያቄ ሲበዛቸው በጥቂት ማእከላይ ኮሚቴ ባለቤትነት በኣክስዮን ስም ተሰጥተው ።ኣሁንም ማጭበርበራቸው በመቀጠል ሁሉም ኩባንያዎች እያንዳንዳቸው ሓላፍነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ተባሉ ። ኣንድ ጊዜ ደግሞ ለስብሀት ነጋ የኤፈርት ኩባንያዎች ባለቤትነታቸው የማን ነው ተብሎ ሲጠየቅ የህዋሓት ነው ብሎ ነበር ።ባለፈው ኣመትም የኢፈርት ኩባያዎች የትግራይ ህዝብ ናቸው ስለሆነ ከእንግዲህ በትግራይ ክልል ምክርበት የባለቤትነት ስም ሆነዋል ተባለ ። ይሁን እንጅ ካለፉት የነበሩ የኣጭበርባሪ ባለቤትነት ወደ ክልል ትግራይ ምክርቤት እንዴት ይሸጋገርሩ የሚል የተቀመጠ እና የርክክብ ህግና ደንብ ኣሳራር ኣልተቀመጠም ነበር ። በኣሁኑ የክልል ትግራይ ኣመታዊ ግምገማም የኤፈርት ኣጀንደ ተነስቶ የደረሱት ውሳኔ ኣሁንም የኤፈርት ኩባንያዎች በትግራይ ክልል ምክርቤት ባለቤትነ መሆኑ ተወስኗል ተባለ ።

የትግራይ ህዝብ ኣስተውለው የኤፈርት ኩባንያዎች ከተቋቋሙ 27 ኣመታት ኣስቆጥረዋል ። በስምህም ተነግዶባቸዋል ።እነዚህ ኩባንያዎች ቀደምሲል በስብሀት ነጋ ፣ኣባዲ ዞሞ፣ስዬ ኣብርሀ፣ በኣርከበ ዕቁባይ ፣ ሙሉጌታ ገብሪሂወት(ጫልቱ) ፣በኣባይ ጸሀዬ ፣ በርድና በሁሉም ማእከላይ ኮሚቴ ባለቤትነት ሆነው ኖረዋል ፣በመጨረሻም መለስ በበላይነት በኣዜብ መስፍን ፈላጭ ቆራጭነት ተይዘዋል ፣ኣሁንም የነስብሀት ፍጹም ታማኝ የሆነ ተድሮስ ሀጎስ እንደፈለገ እያደረገው ያለው ነው ።

እነዚህ ኩባንያዎች ከተመሰረቱ ጀምረው ከኣንዱ ባለቤትነት ወደ ሌላ ባለቤትነት ሲዛወሩ ኦዲት ተደርገው ሀላፊነት ባለበት ርክክብ ተደርጎው ኣያውቁም ።እጅጉን እሚገርመው ስማቸው ኣልጠቅሰውም በኣሁነ ጊዜ መቐለ ኣሉ እጅግ የታወቁ ከፍተኛ የኦዲት ሙያና ተመኩሮ ያላቸው 2 ከፍተኛ ኦዲቶሮች በኤፈርት የሁሉም ኩባንያዎች የውስጥ ኦዲቶሮች ሆነው ሲሰሩ እያሉ በዛ የኦዲተር ሀቀኛ ኣሳራር ተከትለው በሚሰሩበት ጊዜ ኣጭበርባሪ የሆነ የሸፍጥ እዲት ስሩ ተብለው ሙሁራዊ ህሊናቸው ሊቀበለው ባለመቻሉ ከነስብሀትና ፣ኣባዲ፣ ዞሞ ፣ኣርከበ ዕቑባ ፣ቴድሮስ ሓጎስ ባለመስማማታቸው ስራው ጥለውት ወጡ! ስለሆነ የኤፈርት ኩባንያዎች ባለቤቶች የህዋሓት ኣማራር በሙሉ ከጀምር እስከ ኣሁን የኤፈርት መነሻ ካፒታል ፣የ27 ኣመት ሙሉ ትረፍና ኪሳራ ለህዝብ ይፋ ኣድርገውት ኣያውቁም ።

የኣሁኑ በደኩተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የሚመራ የትግራይ ምክርቤትም የኤፈርት ኩባንያዎች ከዛሬ ጀምሮ የተግራይ ክል ምክርቤት ተረክቦዋቸዋል ሲለን በቅንነት ቢሆን ንሮ ኤፈርት በውጭና በውስጥ ኦዲቶሮች የተረጋገጠ የሀፍት ርክክብ ኣድርጎ መረከብ ሲገባው ፣ኣሁንም ለነዛ ካሁን በፊት ኤፈርትን እያጭበረበሩ ሲመዘብሩ የመጡ መሪዎች እንደ እንቁላል ጉዳቸውን ሸፍኖ ማለፍ ኣልበቃም ብሎት ኣሁንም ለ 7 ሚሊዮን የሚሆን የትግራይ ህዝብ በሚዲያ ኣውጆና ኣጭበርብሮ ማለፉ የትግራይ ምክር ቤት ገና ከጅምሩ ረጅም ሳይጓዝ ሲያጭበረብር ይታያል ።

የኤፈርት ኩባንያዎች የትግራይ ክልል ምክር ቤት ተረከባቸው ብሎ ህዝብ ሊቀበላቹህ ከሆነ ኤፈርት ከቦርድ ጀምሮ እስከታች ያለ የህወሓት ባለስልጣን በፖለቲካ ( የህዋሓት )ኣባልነት ታማኜነት ተገን ተደርጎ ምንም ሙያ የለለው የተሰገሰገው ጠራርጎ ኩባንያዎች ነጳ በሆኑ በሙያ የተካኑ ሙሁራኖች ተክቶ መዋቅሩም ጭምር ኦዲት ኣድርጎ ሲረከብ ብቻ ነው ።ካለበለዚያ በሸፍን ሸፍን የምታውጁት ግን ትርጉም ኣይሰጥም ።የትግራይ ህዝብ እንደሀነ ከእንግዲህ ወዲ ነቅቷል ለሆነ ኣጭበርባሪ መሪ ኣይቀበልም ።

በመሆኑም ኣሁን የኤፈርት ኩበንያዎች ከህወሓት መሪዎች ነጻ ኣልወጡም ።የትግራ ምክርቤት እኮ 100 % የህዋሓት ኣባላት ናቸው ።ኢፈርት እየመሩ ያሉም የህወሓት ኣባላትና መሪዎች ናቸው ።ስለሆነ በእኔ እምነት ትእም ወደ ህዝብ ባለቤትነት ተዛውረዋል ብለን ልንቀበላችሁ ከሆነ ከሁሉም ነጻ የሆኑ ስቢል ቡቁ ሙሁራን ይምሯቸው ! ! ምክርቤት ቁጥጥርን የፈርት ሁኔታ ለህዝብ ይፋ ማድረግ ብቻ መሆን ኣለበት ።
ከድሮ ጀምረው ኤፈርት ሲመሩ የነበሩ ኣሁንም ያሉ እኮ በፎቶዎ ያሉ ናቸው ።

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *