የእርቅና ሰላም አባት በሚል ስያሜ የሚታወቁት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ካውንስል ሊቀመንበር እና የዑለማ መሪ ሀጂ ሙፍቲ ሼክ ዑመር እድሪስ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሊሰጣቸው መሆኑ ታወቀ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ ለሆኑት ለአቶ ተወልደ ገብረማርያምም አሉበት።

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር የሰላም ጠበቃ፣ የመካም መንገድ አመላካች፣ ደግ ደጉን መካሪ፣ ተከፋፍለው የነበሩትን የሙስሊም ወንድሞችን ልዩነት ለማርገብ ታትረው የሰሩና የተሳካላቸው፣ እርጋታ ልዩ መለያቸው የሆነ፣ በአገራችን በታላቅ ስፍራ ስማቸው ከሚጠራ እጅግ ውሱን አባቶች አንዱ መሆን የቻሉና የሚወደዱ ናቸው። የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለእኝህ መልካም አባት ይህንን ታላቅ ክብር ለመስጠት መወሰኑ ከወዲሁ ምስጋና እንዲሰጠው አድርጎታል። እኚሁ አባት ወሎ ለጋምቦ ወረዳ፣ ገነቴ በምትባል መንደር በግንቦት 21ቀን 1929 መወለዳቸውን ግለ ታሪካቸው ያስረዳል።

Image result for አቶ ተወልደ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ጉባኤ በትናትናው ዕለት ባካሄደው ስብስባ የክብር ዶክትሬት ዲግሪው እንዲሰጣቸው ውሳኔ አሳልፏል፡፡በዚሁ መሰረት እሳቸውና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ ለሆኑት ለአቶ ተወልደ ገብረማርያም የክብር ዶክትሬት ድግሪው በነገው ዕለት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምረቃ ስነስርዓት በሚካሄድበት በሚሊኒየም አዳራሽ ይሰጣቸዋል።

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   አስከሬን እንዲለቀም ታዘዘ - ትህነግ የአጽም ፖለትካ ድራማ ይፋ ሆነ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *