ከትግራይ መለሶ ማቋቋም ኩባንያዎች ናቸው ከሚባሉት መካከል ትራንስ፣ መሶበ ሲሚንቶና ሱር ኮንስትራክሽን በአክሲዮን ለመሸጥ የቀረበውን ጥያቄ ተከትሎ ቅድሚያ ኦዲት መቅደም አለበት የሚል ጥያቄ መነሳቱን የአሜሪካ ድምጽ የመቀሌ ሪፖርተር አመለከተ። አቶ ስብሃት ነጋ ከአፍሪካ በሃብት ቀዳሚ ነው ያሉት ኤፈርት ንብረቱ ኦዲት ሊደረግ እንደሚገባውና አሰራሩ ግልጽነት የጎደለው መሆን በተደጋጋሚ ሲገለጽ መቆየቱ የሚታወስ ነው።

በምክትል ርዕሠ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ሃላፊ ዶክተር አብርሃም ተከስተን በመጥቀስ የተሰራጨው ዜና እንዳመለከተው ሃላፊው ጥሪ ያቀረቡት በውጭ አገር ያሉ ባለሃብት የትግራይ ተወላጆች ተደራጅተው አክሲዮን እንዲገዙ ነው።

ትምዕት ኩባንያዎችን በአክሲዮን ለመሸጥ የሚያስችለውን ጥሪ ከማቅረቡ በፊት በገለልተኛ ወገኖች ኦዲት ሊደረግ እንደሚገባ ተወላጆች ጥያቄ መሰንዘራቸውን አስመልክቶ ዘጋቢው ሃላፊዎቹን ጠይቆ ያለው ነገር የለም። 

የትምዕት ንብረት እጅግ ግዙፍ የመሆኑንን ያህልና ከፈተኛ ሃብት እንደማንቀሳቀሱ የግልጽነት ችግር የሚከተለ መሆኑ በተደጋጋሚ የሚገለጽና በየመድረኩ የሚነሳ ጉዳይ ቢሆንም የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር አመራሮች የጠራ ምላሽ ሰጥተውበት አያውቁም። አሁን የቀረበውን የአክሲዮን ሽያጭ ጥሪ አስመልክቶ የቀረበው የኦዲት ጥያቄም ይህንኑ ያገናዘበ እንደሆነ በማህበራዊ ገጾች የተሰራጩ መረጃዎች ያመለክታሉ።

ድርጅቶቹ ከባንክ ያለባቸው ብድርና የእዳቸው አከፋፈል ከአክሲዮን ሽያጩ በፊት ይፋ መሆን አለበት ሲል የጠየቀ እንዳለው አክሲዮን የሚገዙ ወገኖች የጠራ መረጃ ሊሰታቸው እንደሚገባ ጠቁሟል። በይፋ የጠራ አሃዝ ባይቀርብም በቢሊዮን የሚቆጠር እዳ እንዳለባቸው ግን የተለያዩ መገናናዎች የባንክ ምንጮችን እየጠቀሱ መዘጋባቸው አይዘነጋም።

ከዚህም በተጨማሪ በመላው አገሪቱ በጅምላ ተይዘው የነበሩ የንግድ ዓይነቶች እንደ ቀድሞው የሚሰሩ አለመሆናቸው በድርጅቶቹ የወደፊት ትርፋማነት ላይ ጥርጣሬ የሚያስነሱ ሆነዋል። 

ኩባንያዎቹ ቀደምሲል ስብሀት ነጋ ፣ኣባዲ ዘሙ፣ስዬ ኣብርሀ፣ ኣርከበ ዕቁባይ ፣ ሙሉጌታ ገብሪሂወት(ጫልቱ) ፣ኣባይ ጸሀዬ ፣ በቦርድና በሁሉም ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ስር ሲተዳደሩ እንደነበር ፣በመጨረሻም መለስ ዜናዊ በባለቤታቸው  ኣዜብ መስፍን አማካይነት ማስተዳደራቸውን ፣ ኣሁንም የእነ ስብሀት ታማኝ ናቸው በሚባሉት ቴዎድሮስ  ሀጎስ  እንደሚተዳደር አቶ አስገድ ከቀናት በፊት ባሰራጩት ጽሁፍ አመልክተዋል።

“የኤፈርት የባለቤትነት መብት ገና ኣልጠራም ?” በሚል ርዕስ አቶ አስገደ የግል መረጃቸውን አስፍረዋል። ይህንን ብመጫን ያንብቡ

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *