የምሥራቅ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ / ኢመደኤ ዋና ዳይሬክተር እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት ጉዳዮች አማካሪ ሆነው ያገለገሉት አቶ ተመስገን የአማራ ክልልን እንዲመሩ ታጩ። ልክ ዶክተር አምባቸው ላይ እንደሆነው ሁሉ የጭፍን ተቃውሞ ይጠበቃል።

አቶ ዮሐንስ ቧያለውን የፓርቲው ምክትል ሊቀ-መንበር አድርጎ የሰየመው የአዴፓ ማእከላዊ ኮሚቴ፣ አቶ ተመስገን ጥሩነህና አቶ አገኘው ተሻገር የአዴፓና የኢህአዴግ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አድርጎ መመረጡን የክክሉ መገናና ብዙሃን ይፋ አድርጓል።

Related stories   ብርሃኑ ነጋ አቋማቸውን ቀየሩ፤ ኢዜማ ደርግ በግፍ የዘረፈውን የግል ሃብት ለተከራይ እንደሚሸጥ ይፋ አደረገ፤ የኢዜማ የ ” ፍትህ” ሩጫ

አቶ አገኘሁ ተሻገር ደግሞ የቀድሞው ሰሜን ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ፣ የአማራ ሥራ አመራር አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር፣ የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ያገለገሉ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ደግሞ የክልሉ ሕዝብ ሠላምና ደኅንነት ቢሮ ኃላፊ ናቸው።

የማዕከላዊ ኮሚቴውን ውስኔ ተከትሎ ቀደም ሲል በዶክተር አምባቸው ላይ እንደሆነው በተቃውሞ የተለከፈው የተቃውሞ ፖለቲካ አሁንም በስፋት እንደሚጠበቅ ከወዲሁ አስተያየት እየተሰጠ ነው። ክልሉ አሁን ባለበት ችግር ወቅት እንዲህ ያለውን የቀድሞውን ጥፋት ከመድገም ድጋፍ መስጠት አግባብ እንደሆነ የሚጠቁሙ ወገኖች ይህ አጋጣሚ እንዳይባክን ያሳስባሉ። ሲያስረዱም የአማራ ክልል ወደ አንድነት የሚመጣበት እንዲሆን ይህንን ክፉ ጊዜ መጠቀም ግድ መሆኑንና ሌላ አማራጭም አለመንሮሩን ያሰምሩበታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *