አሜሪካ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከተለያዩ አገራት ጋር የምታደርገው ወታደራዊ ስልጠና በተለይም በአሁኑ ወቅት መሆኑ ልዩ መልዕት እንዳለው ተጠቆመ። የዘወትር የዛጎል የዲፕሎማቲክ መረጃ  እንዳሉት በ1997 ጭንቀት ወቅት አሜሪካ በስልጠና ሰበብ ኢህአዴግን መታደጓን ያስታውሳሉ።

ምንም እንኳን ስልጠናው በኢትዮጵያና በአሜሪካ መካከል የተደረሰው ስምምነት አካል ቢሆንም፣ አሁን ላይ መደረጉ አሜሪካ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ያላትን ድጋፍ ሙሉ በሙሉ እንደሚያረጋግጠው አመላክች ሲሆን በተጻራሪው ስርዓቱን ለሚገዘግዙ መርዶ መሆኑንን ነው መረጃ ሰጪው ያስታወቁት።

ኔቪይ ሲል የሚባል የመጨረሻ ሃይል አካላት ስልጠናው ላይ መካተታቸውን የጠቆሙት እኚሁ ሰው ፣ ” ስልጠናው ጀበና ሰበሩ አይነት ስልጠና አይደለም። አሜሪካኖች ዝም ብለው ምንም ነገር አይደርጉም ” ሲሉ አክለዋል። ምርጫ መቃረቡንም አስምረውበታል።

The Navy’s Sea, Air and Land Forces – commonly known as SEALs – are expertly trained to deliver highly specialized, intensely challenging warfare capabilities that are beyond the means of standard military forces.

Related stories   ብርሃኑ ነጋ አቋማቸውን ቀየሩ፤ ኢዜማ ደርግ በግፍ የዘረፈውን የግል ሃብት ለተከራይ እንደሚሸጥ ይፋ አደረገ፤ የኢዜማ የ ” ፍትህ” ሩጫ

Their missions include: direct action warfare; special reconnaissance; counterterrorism; and foreign internal defense. When there’s nowhere else to turn, Navy SEALs achieve the impossible through critical thinking, sheer willpower and absolute dedication to their training, their missions and their fellow Special Operations team members.

አልሸባብን በአየር ጥቃት አራውጠው ወደ ተራ ፈንጂ ወርዋሪነት እንዳዛወሩት በማስታወስ የስልጠናው ትኩረት አልሸባብ ይሆናል ብለው እንደማያምኑ አመልክተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ወደ ስልታን በመጡ ማግስት አሜሪካ በድህንነትና በመከላከያ ሪፎርም ጉዳይ አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረጓን ያመለከቱት እኚሁ ሰው፣ የአሁኑ ልምምድ ፊትለፊት ከሚነገረው በላይ በርካታ ተግዳሮቶች ያሉት መሆኑንን አክለው ገልጸዋል። ፋና  “ኢትዮጵያ እና አሜሪካ የሚያደርጉትን አመታዊ ወታደራዊ ልምምድ ጀመሩ” ሲል የሚከተለውን 

ልምምዱ አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ወታደራዊ ልምምድ ለማድረግ የደረሰችው ስምምነት ሲሆን፥ በዛሬው እለትም የአሜሪካ መከላከያ አባላት ከኢትዮጵያ መከላከያ ሃይል ጋር በጥምረት ልምምድ ማድረግ ጀምረዋል።

ልምምዱ በሶማሊያ በተሰማራው የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ሃይል (አሚሶም) አባላትን አቅም ማሳደግ ላይ ያተኮረ ሲሆን፥ ወደ 1 ሺህ 100 የሚጠጉ ወታደራዊና የመንግስት ሃላፊዎች ይሳተፉበታል።

ልምምዱ የመከላከያ አባላትን ዝግጁነትና አቅም በማሳደግ ሰላምን ለማስከበር የሚደረገውን ጥረት እንዲደግፉና በቀጠናው ሰላምን ለማስፈን እንደሚያግዝም ታምኖበታል።

ከዚህ ባለፈም ሽብርተኝነትና የእርስ በርስ ግጭቶችን ቀድሞ ለመከላከል እንደሚያስችልም ተገልጿል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ፍስሃ ወልደሰንበት፥ ልምምዱ በቀጠናው የተሻለ መረጋጋት ለመፍጠር እንደሚያግዝ ተናግረዋል።

የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ዓለም አቀፋዊ ጉዳይ በመሆኑ በመሰል ስልጠናዎች አቅምን ማሳደግ እንደሚገባ የልምምዱን መጀመር አስመልከቶ በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተነስቷል።

ዛሬን ጨምሮ ለ16 ቀናት በሚቆየው ልምምድ፥ ከብራዚል፣ ብሩንዲ፣ ካናዳ፣ ጂቡቲ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ጣሊያን፣ ኬንያ፣ ኔዘርላንድስ፣ ሩዋንዳ፣ ሶማሊያ፣ ኡጋንዳ እና ዩናይትድ ኪንግደም የተውጣጡ ወታደሮች ይሳተፋሉ።

ከዚህ ባለፈም እንደ አፍሪካ ህብረትና እና የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት፣ የአሜሪካ የሰላም ተቋምና ከዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ማህበር የተውጣጡ ባለሙያዎችም ይሳተፋሉ ነው የተባለው።

በተያያዘም ኢትዮጵያና አሜሪካ በህክምና ዝግጁነት ላይ ያተኮረ ልምምድ እያደረጉ ነው።

ይህ ልምምድ ወታደራዊና መደበኛ የህክምና አባላት የሚሳተፉበት ሲሆን፥ የልምድ ልውውጥ ለማድረግና የሚሰጠውን የህክምና ክትትል አቅም ለማሳደግ ያስችላል ነው የተባለው።

በመንግስታቱ ድርጅት እና በአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ውስጥ የጎላ ድርሻ ያላት ኢትዮጵያ ከሁለት አመት በፊት ከአሜሪካ ጋር መሰል ወታደራዊ ልምምድ ማድረጓ ይታወሳል።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *