የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) ማዕከላዊ ኮሚቴ ልዩ ስብሰባ ተጠናቀቀ ፡፡ ማዕከላዊ ኮሚቴው ባለፉት 10 ቀናት በሀገራዊና ክልላዊ ወቅታዊ የፖለቲካና የጸጥታ ሁኔታዎች እንዲሁም አዳዲስ ክልል ሆኖ የመደራጀት ጥያቄዎች ላይ ሲያካሄድ የነበረውን ስብስባው ማጠናቀቁን አስታውቋል፡፡ፓርቲው የኢትዮጵያዊ አንድነት አጠናክሮ የማስቀጠል፣ የተጀመሩ የለውጥ እንቅስቃሴዎችንና ውጤታቸው ተጠናክረው እንዲቀጥሉ እንዲሁም የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በጽናትና በመርህ ላይ ቆሞ በመታገል ለላቀ ስኬት እንዲበቃ ሙሉ በሙሉ ተስማምቷል።

ማእከላዊ ኮሚቴው ኢትዮጵያ አሁን ያለችበትን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ በጥልቀት ተወያይቶ የተጀመረው ሀገራዊ ለውጥ ተጠናክሮ በሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ መክሮ አቋም ወስዷል፡፡

ክልላዊ አደራጃጀቱን በተመለከተ ዝርዝር ሳይንሳዊ ጥናት ተደርጎ የቀረበ ሲሆን ጊዜ ወስዶ በሳል ውይይት የተካሄደበት ሲሆን የቀጣይ አቅጣጫም ተቀምጧል ፡፡

እንዲሁም የክልሉን ሰላምና ደህንነት አስተማማኝ ማድረግ እና የህግ የበላይነትን ማስከበር ላይ ጥልቅ ውይይት ተካሂዶ ጠንካራ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

የደኢህዴን ማእከላዊ ኮሚቴ የኢትዮጵያዊ አንድነት አጠናክሮ የማስቀጠል፣ የተጀመሩ የለውጥ እንቅስቃሴዎችንና ውጤታቸው ተጠናክረው እንዲሁም የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በጽናትና በመርህ ላይ ቆሞ በመታገል ለላቀ ስኬት እንዲበቃ ማእከላዊ ኮሚቴው በሙሉ መግባባብት ላይ በመድረስ ለቀጣይ ተልእኮም በቁርጠኝነት መዘጋጀቱን አረጋግጧል፡፡

 ማዕከላዊ ኮሚቴው የሚያወጣውን ዝርዝር መረጃ በተከታይ ይቀርባል።

FBC

Related stories   ብርሃኑ ነጋ አቋማቸውን ቀየሩ፤ ኢዜማ ደርግ በግፍ የዘረፈውን የግል ሃብት ለተከራይ እንደሚሸጥ ይፋ አደረገ፤ የኢዜማ የ ” ፍትህ” ሩጫ

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *