የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚያስገነባው የአድዋ ማዕከል ግንባታ ተጀምሯል። ማዕከሉ የአድዋ ጀግኖችን ለመዘከር እና የታሪካዊ ድሉን ሁለንተናዊ ይዘት ለትውልድ ለማሻገር በማሰብ የሚገነባ ነው።

የማዕከሉ ግንባታ ለረዥም ጊዜ ሳይለማ በቆየው እና ከሜድሮክ ተመላሽ በተደረገው ቦታ ላይ የሚካሄድ ሲሆን፥ የግንባታው ሙሉ ወጪ በከተማ አስተዳደሩ የሚሸፈን ይሆናል።

ግንባታው በቻይናው ጂያንግሱ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ እና ቴክኒካል ትብብር ግሩፕ የሚከናወን ሲሆን፥ በሁለት አመታት ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

Related stories   የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት “ህወሓት” እና “ሸኔ” በሽብርተኝነት እንዲሰየሙ ወሰነ

የዓድዋ ማዕከል ግንባታ ሲጠናቀቅ ከሚሰጠው ማህበራዊና ታሪካዊ ፋይዳ በተጨማሪ በውስጡ የአድዋ ሙዚየምን ጨምሮ ከ2 ሺህ ሰው በላይ የሚይዝ የዓድዋ አዳራሽ ይኖረዋል።

ከዚህ ባለፈም እያንዳንዳቸው 400 ሰው የመያዝ አቅም ያላቸው ሶስት አዳራሾች፣ የሲኒማ አዳራሽ፣ ቤተ መጽሃፍት፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መስሪያ፣ የህፃናት መጫወቻ እና የማቆያ ስፍራዎችን ያካትታል።

በተጨማሪም አረንጓዴ ስፍራን ጨምሮ ካፌ እና ምግብ ቤቶች እንዲሁም ዘመናዊ ፓርኪንግ ያካተተ መሆኑን ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

Related stories   አቡነ ማቲያስ መነጋገሪያ ሆነዋል - ኢትዮጵያ ላይ ዘመቻው እንዲከር ጥሪ አቅርበዋል

ፋና

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *