ዓላማው ሃዋሳን ማንደድና በሃዋሳ የሚገኙ የሌሎች ብሄረሰቦችን ንብረት መዝረፍ ብሎም ማቃጥል ነበር። ይህ አስቀድሞ በመታወቁና በበቂ ዝግጅት የተፈራው ጉዳት ሳይደርስ በቁጥጥር ስር ውሏል። የማተራመሱ ድራማ አቀነባባሪዎች እየተለቀሙ ነው። የሲዳማን ክልል የመሆን ጥያቄ ሰፊ ሽፋን በመስጠት ሲያበረታታ የነበረው  ጃዋር ከደረሰው ጭፍጨፋ ጋር በተያያዘ ይሁን በሌላ በውል ባይታወቅም በድንገት ወደ ሜኖሶታ መመለሱ ታውቋል። አሁን እያነጋገረ ያለው በኦሮሞ ስም በሲዳማ የክልልነት ጥያቄ ላይ ቤኒዚን ሲርከፈከፍ ፍትህ ወዳድ የኦሮሞ ልሂቃን ዝም ማለታቸው ነው።

በሃዋሳ በ11.11.11 የክልልነት አዋጅን ህጉ ከሚፈቅደው ውጪ ለማወጅ ሲደረግ የነበረው ሩጫ ጋብ እንዲል፣ በዞን፣ በክልልና በፊደራል መንግስት በኩል ቀና ምላሽ በመሰጠቱ፣ በትዕግስት አፈጻጸሙን እንዲደግፉ፣ አስተዳደሩ፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ ምሁራን፣ መንግስት በፓርላማ ደረጃ ምልጃ ቢያቀርቡም ኤጄቶ የተባለው ሃይል ከቶውንም ሊቀበል አለመቻሉ የዚህ ቡድንና ከጀርባ ያሉት ክፍሎች ፍላጎት ምን እንደሆነ በይፋ መረዳት አልተቻለም።

ላለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት እንደ አሁኑ አይነት ቀና ምላሽ ሳይሰጥ ሲገረፉ፣ ሲታሰሩ፣ ሲሰደዱ የነበሩ ለዝርዝር አፈጻጸሙ እስከ አምስት ወር እንዲታገሱ ቢለመኑም እምቢተኛነታቸው መሰረታዊ መነሻና ድጋፍ ያለው ሴራ እንደሆነ አሁን የታየውን ቅሚያ፣ ዘረፋና ዘርን የለየ ጭፍጨፋ ያዩ እየመሰከሩ ነው። በዚሁ ሴራ መሰረት ህጻናትን፣ ወጣቶችን በማሰለፍ በትዕቢት ለማተራመስ የተነሱት ክፍሎች ከዚህ መሰሉ ጭፍን ጭፍጨፋ ምን ያተርፋሉ ለሚለው ምላሽ የሚሰጥ አካል ባይኖርም ዳር ሆነው ሲገፉ የነበሩ አካላት ድርጊቱን አለማውገዛቸው የድራማው አብይ ዓላማ አገሪቱን ማተራመስ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሃቅ ነው።

በዚሁ መነሻ ይህ ቀውስ የተመረጠበት ምክንያት

1፣ ላለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት በውክልና ሲዘርፍ የነበረው አንሶት፣ ለምን የክልልነት ጥያቄ አነሳችሁ በሚል ሲገርፍ፣ ሲገድል፣ ሲያስርና ሲያሳድድ የነበረው የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ቡድን ውስጥ ውስጡን ባደራጃቸውና በገንዘብ በሚደልላቸው የክልሉ ተወላጅ ቅጥረኞች አማካይነት እየተካሄደ መሆኑ

2፣ የአዲስ አበባን ምድር ከረገጠበት ጊዜ አንስቶ የሲዳማ ልዩ ተቆርቋሪ በመሆን በይፋ ከኤጄቶ አደራጆች ጋር በመዶለት፣ በሰፊው የኦሮሞ ህዝብ ስም በተደራጀው የኦሮሞ ሚዲያ ኔት ዎርክ አማካይነት ሲቀሰቀስና ሲያስቀሰቅስ፣ በጀርባ ከሚያደርገው ግፊት በዘለለ በይፋ የሲዳማ ክልል ህዝብ እንዲያምጽ፣ እንዲነሳና በመጤዎች ላይ እጁን እንዲያነሳ የተዘራው ዘር የፈጠረው ስሜትና የደቡብ ክልልን የማሽመድመድ ሴራ በተገዙ ወገኖች በተባለው ቀን ለመፈጸም በተቀመጠ ቀመር ሳቢያ እንዲከናውን መደረጉ

3፣ ሕዝብ ከቶቆጠረ፣ በክልሉ ያሉት ነዋሪዎች ስለ ጉዳዩ በቂ ግንዛቤ እንዲያገኙ ከተደረገና የኤጄቶ የግዢ ድራማ ስለሚከስም ያ ከመሆኑ በፊት በጥድፊያ አገር የማፈራረሱ ጅማሮ ስር እንዲተክል ለማድረግ ሲባል

4፣ ከፍተኛ በጀትና የቆየ ስትራቴጂ ተነድፎለት ሲጎነጎን የነበረው ኢትዮጵያን ከምስራቅ ሶማሌ ክልል በኩል አቃጥሎ የማፈራረስ እቅድ  በአስገራሚ ጥበብ እና በፈጣሪ እርዳታ አቶ ሙስጣፋን የመሰለ መሪ በመገኘቱ መምከኑ የፈጠረው የእልህ ስሜት፣ ሲዳማ ላይ ለመድገም የተያዘው እቅድ ጊዜ ካገኘ ያለ አንዳች መተራመስ በሰላማዊ መንገድ እንዳይከናወን ካለው ፍርሃቻ፣ እንዲሁም ጥያቄው በሰላማዊ መንገድ ከተመለሰ የታሰበው ዓላማ ግቡን ስለማይመታ

Related stories   መከላከያ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ “ጁንታውን” ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታወቀ! በርካታ በቁጥጥር ስር ውለዋል

5፣ አሁን የተዘጋውና በሃዋሳ ከተማ ሲተላለፍ የነበረው የሲዳምኛ ሬዲዮ ፕሮግራም በበታኞች አማካይነት የዘራው የቀውስ ዘር በዚህ ጊዜ ምርቱ ካልተሰበሰበ ለበታኞች ችግር ስለሚሆንባቸው፣

6፣ ከሁሉም በላይ በክልሉ በርካታ ብሄር ብሄረሰቦች ስለሚገኙ እነሱ እርስ በእርስ በቂም ወደ ማያባራ ግጭት እንዲገቡና አገሪቱን ለማፈራረስ  በምስራቅ አቅጣጫ አልሳካ ያለውን ቀውስ በደቡብ በኩል እንድታስተናግድ መፈለጉ፣ ይህ ሲሳካ የመጨረሻውን የቀውስ ካርድ በጋንቤላ በኩል ለመጠቀም የተያዘውን እቅድ ለመተግበር ይቻል ዘንድ ቁልፍ ስትራቴጂ በመሆኑ

እነዚህ ዋናዎቹ ጉዳዮች ቢሆኑም በርካታ ፍላጎቶች ስለመኖራቸው ጥርጥር የለም። ሃያ ሰባት ዓመት ሲቀጠቀጥ የኖረ ትውልድ አምስት ወር ታገስ ሲባል ለመቀበል ፈቃደኛ የማይሆንበት፣ የጸጥታ መዋቅሩን የሚመሩ ፖሊሶች፣ የአካባቢ ታጣቂዎችና የአስተዳደሩ አካላት በከፊልና ባብዛኛው የማተራመሱ ተባባሪ የሆኑበት ምክንያት ለበርካቶች ግልጽ አይደለም።

ሪፈረንደም ለማካሄድ የራሱ ህጋዊ ሂደቶች እንዳሉት አለመረዳት ሆን ብሎ አገር ለማተራመስ ከማለም ውጪ ሌላ ትርጉም ስለሌለው ሰፊው የሲዳማ ህዝብ ድርጊቱን ሊቃወምና ሊኮንን እንደሚገባ በርካቶች ያምናሉ። ይሁን እንጂ ገንዘብ በመርጨት፣ ያልተገባ ቅስቀሳ በማሰራጨት ህጻናትንና ወጣቶችን ከፊት ያሰለፉት አውሪዎች ላይ መንግስት የማያዳግም እርምጃ እንዲወስድ፣ ሃይሉን እንዲጠቀም በዚሁ ምድር ላይ ባለ እውነት መነሻ ዜጎች እየወተወቱ ነው።

በንጹሃን ደም፣ እምባ፣ ስቃይ የሚደሰቱ ክፍሎች ከዳር ሆነው አዛውንቶች፣ እናቶች፣ ህጻናት፣ ሜዳ እንዲጣሉ የሚያደርጋቸውን፣ አስከሬናቸው በየጥጉ እንዲወረወር በማድርገና ይህንኑ አውሬ ተግባር አዛኝ መስለው በማህበራዊ ገጾች በማሰራጨት ግጭቱን ለማስፋት እየሮጡ ያሉት የውጥኑ ባለቤቶችን ናቸው። እሳቱን ጭረውና ቤንዚን አርከፍክፈው የሸሹትን ህዝብ ሊኮንናቸው፣ ምሁራን ሊተቿቸው ሲገባ ዝም ማለታቸው ሃዘኑን ድርብ ያደርገዋል።

የኦሮሞ ልሂቃን ዝምታ 

ፐሮፌሰር ሕዝቄል ሰሞኑንን ትግራይ ሄደው ወዳጅነታቸውን ሲያውጁና በትግራይ ሚዲያዎች አማካይነት አገር የማፍረስ ቅስቀሳቸውን ሲያሰራጩ የኦሮሞ ልሂቃን፣ የኦሮሞ ህዝብ የት ናቸው? ለምን ዝምታን መረጡ? የዛሬን አያድርገውና

– በወለጋ እናት የተገደለ ልጇ አስከሬን ጀርባ ላይ በግድ ተቀምጣ የተገረፈችው በማን ነው?

– እስር ቤት መደበኛ ቋንቋው ኦሮምኛ እስከመሆን ደርሶ የነበረው ለምንድን ነው? 40 ሺህ የሚሆኑ የኦሮሞ ልጆችን አስሮ ሲያሰቃይ፣ አስገድዶ ሲደፍርና ጥፍራቸውን ሲነቅል የነበረው ማን ነው?

– እግራቸውን የተቆረጡ፣ ብልታቸው የተኮላሸ፣ ሰውነታቸው የተበሳሳ፣ እንደ ውሻ በየቦታው ተገድለው የተጣሉ፣ አሁን ድረስ የት እንደደረሱ የማይታወቁትን የኦሮሞና የኢትዮጵያ ልጆች መከራ ማን ፈጸመው?

– የሰዎችን ልጆች በአራዊት ያስበላው፣ በጨለማ ቤት ውስጥ ቶርቸር ሲያደርግ የነበረው፣ በብልት ውስጥ ባዕድ ነገር እየከተተ ግፍ ሲፈጽም የነብረው ማን ነው?

– የኦሮሞ ባለሃብቶችን ንብረት ሲቀማና በምድራቸው እንዳይነግዱ፣ እንዳይሰሩ፣ እንዳያተርፉ አግዶ የአገሪቱን ንብረት ሲዘርፍ የነበረው ማን ነው?

– በቅርቡ እግራቸው የተቆረጠ፣ አይናቸው የጠፋ፣ ሽባ የሆኑ፣ አደባባይ ቀርበው ሲናገሩ የነበሩትና እንባችንን እየረጨን የሰማናቸው ወገኖቻችን ሁሉ ምን ምስክር ሰጡ? ማን እንዲህ አደረገን አሉ?

– በደደር ለሰላማዊ ሰልፍ የወጣ ህዝብ ላይ ማን የጅምላ ጭፍጨፋ አካሄደ? ጨለንቆ፣ ዋተር ….

Related stories   አስከሬን እንዲለቀም ታዘዘ - ትህነግ የአጽም ፖለትካ ድራማ ይፋ ሆነ

– የድህንነት ድር አድርቶ ህዝብ ሲያመነዥግ፣ በተለይም የኦሮሞ ወጣቶችን፣ ምሁራንን፣ አዛውንቶችን፣ ታጋዮችን ሲበላ የነበረውን አውሬ ጉያቸው ስር ቀርቅረው አናስረክብም፣ እኔ እገሌ ነኝ እያሉ በሌሎች ሃዘን የሚደንሱ እነማን ናቸው?…

ብዙ ማለት ይቻላል። ይህንን ሁሉ ሲያደርጉ የነበሩት፣ በሰዎች ልጆች ስቃይንና በቤተሰብ ጣር ሲዝናኑ፣ ሲናኙ፣ ከዚያም አልፈው አልኮል እየተጋቱ ሲዝናኑ የነበሩት የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር አመራሮችና ቡችሎቻቸው መሆናቸው ለኦሮሞ ልሂቃን የሚረሳ ነው? የአንድ ዘመን የቀትር ድራማ ነው? ካልሆነ ዝምታችህ ምንድን ነው? ከምን መነሻ ነው? የኦሮሞ ለሂቃን ይህንን ጥያቄ በርጋታ ሊያዩት ይገባል። ምልሻ ሊሰጡበትም ግድ ነው። ዛሬ በኦሮሞ ሰማዕታትና በወንድም ህዝብ ትግል ነጻነት አግኝተው አገር ቤት የገቡ እንደ ሕዝቄል ገቢሳ ያሉ ከሃጂዎች ትግራይ ከወያኔ ባለስልጣናት ጋር ሲሞዳሞዱና ዶከተር አብይን ለማስወገድ ሲዶሉቱ ቄሮ መልስህ ዝምታ ነው? ይህ ለኦሮሞ ዳግም ሞት አይደለም? ኦሮሞ ማስተዳደር አይችልም በሚል በድንቁርና ጉድጓድ ውስጥ ቀርቀረውህ ከሚንቁህ ገዳዮችህ ጋር የሚያብሩ ይወክሉሃል? ጥያቄው ይህ ነው!!

ይህ ሁሉ የግፍ መአት ተዘንግቶ ሕዝቅኤል ትግራይ ሄዶ በትግራይ ሚዲያ አገር እንዲፈርስና የሞተው ህወሃት ለዘረጋው ሌሎችን አባልቶ የመዳን ስልት በኦሮሞ ህዝብ ስም መጠቀሚያ ሲሆን በዝምታ ማየት ምን የሚሉት ቸልተኛነት ነው? ለመሆኑ ለኦሮሞ ህዝብ ከህወሃት በላይ ጠላት አለው? ኦሮሞዎች ወደ ወጡበት ዋሻ ካልተመለሱ አገር ትፈርሳለች በሚል ዋሻ ለሚመኝላቹህ ድርጅት መጠቀሚያ ከመሆን በላይ ምን አሳፍሪና አንገት የሚያስደፋ ጉዳይ አለ?

ቄሮ ቢሊሱማ፣ ቄሮ ኦሮሚያ

አምቦ ልጆችሽ በህወሃት አልሞ ተኳሾች እየተቀነደቡ ሲደፉ አላየሽም? ግንደበረት፣ አስጎሪ፣ ጊንጪ፣ ሆለታ፣ ወሎንኮሚ፣ አርሲ፣ ባሌ፣ ወለጋ፣ ደምቢ ዶሎ፣ ጅማ፣ አጋሮ፣ ሻምቡ፣ ወለንጪቲ፣ ሃረርጌ፣ አወዳይ፣ አሰበ ተፈሪ፣ ሃብሮ፣ መኢሶ፣ አፍደም፣ አዳማ፣ ዝዋይ፣ ሻሸመኔ… ልጆችሽ በወያኔ የቀትር መርገምቶች እየተደፉ አስከሬናቸው ሲጣል አላያችሁም?

ቄሮ ለመብት ብለህ ስትነሳ ስንት ወንድምና እህቶችህ ተደፉ? ቄሮ እናቶች አይናቸውን እያጡ፣ እጃቸው እየተቆረጠ ዋይ ዋይ እያሉ ያነቡትን ረሳህ? የሞትከው ህወሃት በሚሰራው ድራማ ለሚነዱ መርዛማ ከሃጂዎች  ስትል ነው? ቄሮ ሃዋሳም ሆነ ሲዳማ አካባቢ የሚኖሩ ወገኖች ምን አደረጉህ? ባንተ ስም፣ አንተን ተገን አድረገው የፖለቲካ ቁማር ለሚጫወቱ መጠቀሚያ ለመሆን ነው ወንድምና እህቶችህን የገበረከው? ታዲያ ለምንድን ነው? ያ – ቄሮ እምነትህና ግብህ ይህ ነበር? የፈሰሰው ደም ሌሎችን ለማባለት የሚሆን ሜዳና የፖለቲካ ቁማር ለሚጫወቱ ስውር ውጥን ነበር? ካልሆነ መልስህን መልስ!! ምልሻህ ምንድን ነው?

ቄሮ አንተ ከጥይትና ከወያኔ ነብሰ በላዎች ጋር የተናነቅከው ሌሎች ንጽሃን እንዲገደሉ ሌት ተቀን እሳት ለሚለኩሱ፣ ለሚዘርፉ፣ እሳት ለኩሰው ለሚሸሹ ስትል ነው? ቄሮ – ረጋ በልና መርምር። በስምህ ምን እንደሚሰራ እወቅ!! ሲዳማ ላይ እሳት እንዲቀጣጠል ለምን ይቀሰቀሳል ብልህ አጣራ፤ ደምህን ትግራይ ወስደው ከወያኔ ጀሌዎች ጋር ሊወዳጁበት የሚሯሯጡትን ለይተህ ተቃወም። ነገ ላለመሸጥህ ዋስትና የለህምና ንቃ!! ቄሮ ላንተና ለኦሮሚያ ከዶክተር አብይ፣ ከኦቦ ለማ መገርሳ ይልቅ ሲጨፈጭፉህ የኖሩር ገዳዮች ይበልጡብሃል? ዳግም ሞት!!

Related stories   Ethiopia’s transition misrepresented. Reply to Obang Metho

ቄሮ ነገ ከአማራ የሚወለደውን የናትህን ልጅ ልታርድ ነው? አባትህ ከወላይታ የወለዳትን እህትህን ለታፈናቅል ነው? ቂሮ እናትህ ትዳር መስርታ በፍቅር እየኖረች ካለችው አማራ ፣ ጉራጌ፣ ወላይታ፣ ከንባታ… ባለዋ ልትለያት ነው? ግማሽ ደምህ የሆነውን ወገንህን ሊያስጨፈጭፉህ  ነው? ስንት ሚሊዮን ወንድምና እህቶችህንስ ነው የሚያስጨፈጭፉህ? ሲዳማ ላይ ያደረጉት ይህንን ነው!!

ሲዳማዎች

ሲዳማዎች አስቡ። ጥያቄያችሁን አፈነው ሲገርፏችሁና ሲያሳድዱዋችሁ፣ እንዲሁም ሲገድሏቹህ ለነበሩ ሰው በላዎች እንዴት መጠቀሚያ ትሆናላችሁ? አምስት ወር እሩቅ ነው? ስለምን አብሮ የኖረ፣ አገር ሲተብቅ የቆየ ሰላማዊ ህዝብ ትነካልቹህ? ዓላማቹህ ዝርፊያ ነው? ሰው መግደል ነው? ህጻናትን መበተን ነው? ንብረት ማቃጥል ነው? ታገሱ መባል እንዴት ምንም የማያገባቸውን ንጹሃን እንድትገድሉ ምክንያት ይሆናችኋል? ታገሱ መባል እንዴትና በምን መስፈርት የንጹሃንን ንብረት እንድታቃጥሉ ምክንያት ይሆናችኋል? ታገሱ መባሉ ሌሎችን በምን ጉዳይ ይመለክታል? በዚህ መልኩስ መዝለቅ ይቻላል? ነገ እናንተን ተደራጅቶ የምያጠቃ የለም?

የምትገድሉት ኦሮሞ ነው። የምትዘርፉት አማራ፣ ጉራጌ፣ ወላይታ … በተለያየ ስፍራ ዘር ያለውን ኢትዮጵያዊ ነው። እናም ምስኪኑን ሕዝብ በጠላት አታስከብቡት። እነ ጃዋር ለምን እንደሚገፉዋቹህ ቀስ በሉና መርምሩ። ስታንሱ ወደፊት የሚመጣውን መዘዝ ከወዲሁ ምሁራኖች ሲነግሯቹህ አድምጡ። አትግለብለቡ። እስከ አፍንጫው ከታተቀ ሃይል ጋር ገጥማቹህ ህጻናትን አታስጨርሱ። በማንኛውም መስፈርት በሰላማዊ መንገድ መስመር የያዘውን ጉዳያችሁን ከማስፈጸመ ወደሁዋላ አትበሉ።

ዛሬ ይህ ሆኗል ነገስ ጀርመን ሬዲዮ ከዚህ በታች ያለውን ዘግቧል።

በደቡብ ክልል በሲዳማ ዞን የገጠር ከተሞች በተከሰቱ ግጭቶች የሰዎች ህይወት ማለፉን እና ንብረትም መውደሙን የዓይን ምስክሮች ተናገሩ። የዓይን ምስክሮቹ በተለይ በሞሮቾ በሃገረ ሰላም፣ በአለታ ወንዶ እና በይርጋለም ከተሞች የሲዳማ ክልልነት በይፋ እንዲታወጅ በሚጠይቁ ወጣቶች እና በፀጥታ አስከባሪዎች መካከል በተፈጠሩ ግጭቶች ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች ሞተዋል ሲሉ ለዶቼቬለ ተናግረዋል።

ከትናንት ጀምሮ በተፈጠረው በዚሁ ግጭት በተለይ በሞርቾ እና በሃገረ ሰላም ከተሞች ከሞቱት መካከል አብዛኛዎቹ ታዳጊ ወጣቶች መሆናቸውንም ገልጸዋል።በግጭቱ የግለሰቦች እና የመንግሥት መኪናዎች መቃጠላቸውንም ተናግረዋል። እንደ ዓይን እማኞቹ በተለይ በሞሮቾ አውራ ጎዳናዎች በድንጋይ በመዘጋታቸው ከሃዋሳ ወደ ይርጋለም ፣አለታ ወንዶ እና ሃገረ ሰላም የሚያገናኙ የትራንስፖርት አገልግሎቶች መቋረጣቸውንም የዓይን እማኞች ገልጸዋል።

በሃገረ ሰላም ከተማም ወጣቶች የግለሰቦች እና የመንግሥት ንብረት ሲሰብሩ እና ሲቃጥሉ እንደነበርም እነዚሁ የዓይን ምስክሮች ለዶቼቬለ ተናግረዋል።አለመረጋጋቱ በተስፋፋባቸው የሲዳማ ዞን የገጠር ከተሞች እስካሁን በሰው እና በንብረት ላይ ስለደረሰው ጉዳት መጠን ከክልሉም ሆነ ከሲዳማ ዞን የፀጥታ አካላት ማረጋገጥ አልተቻለም። ዶቼቬለ DW ያነጋገራቸው የሲዳማ ዞን የስራ ሃላፊዎች በከተሞቹ ሰዎች መሞታቸውን እና ንብረት መውደሙን ቢያረጋግጡም ዝርዝር መረጃ እየጠበቁ መሆናቸውን እንደተናገሩት የሃዋሳው ዘጋቢያችን ሸዋንግዛው ወጋየሁ ዘግቧል።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *