የአማራ ፖለቲካ ከስደተኛ (ጥቂቶችን አይመለከትም)፤ ከቀን ሰራተኛ፤ ከ 10ኛ ክፍል ባግባቡ ካልጨረሱ፤ ካልተማሩ፤ ከጎጠኛ፤ ከአሉባልተኛ፤ ከሸረኛ፤ እራሱን መሪ አድርጎ ከሾመ፤ ከስቶር ሰራተኛ እጅ ፈልቅቀን አዉጥተን የአማራን ህዝብ አጀንዳ 1፣ 2፣ 3 ብሎ ቆጥሮ ተጨባጭ ለዉጥ በሚያመጡ ሰዎች ካልተያዘ ነገሩ ሁሉ ከባድ ነዉ፡፡ በተለይ በተለይ ፖለቲካዉን ከህጻናት እጅ እና ከሰነፍ ፖለቲከኞች ቀስ አድርጎ አታሎ መቀማት ያስፈልጋል፡፡ የአማራን ህዝብ ተስፋ በሚሰጥ መልኩ፤ በስትራቴጅ የታጀበ፤ ራእይ ባላቸዉ ሰወች እና ራቅ አድርገዉ በሚያስቡ ጊዚያዊ ወጀብ በማያንገዳግዳቸዉ ሰወች ካልተያዘ የካብነዉ ካብ ሁሉ እየፈረሰ ጭራሽ ወደማንወጣዉ አዘቅት ዉስጥ እንገባለን እየገባንም ነዉ፡፡


ትዝብት – Miky Amhara

ሰዕሉን የተጠቀምነው ከፋይል ነው፤ ርዕሱን የመረጥነው እኛ ነን

የሶማሌዉ ክልል ፕሬዝደንት ሙስጠፋ እጅግ ጥሩ ሰዉ ነዉ፡፡ ፕሮግረሲቭ እና ጤናማ የሆነ የፖለቲካ ስርአት አራማጅ ለመሆኑ ከሚናገራቸዉ ንግግሮች ማየት ይቻላል፡፡ ይህ ምናልባትም ወደ ዳር ተገፍቶ ለነበረዉ ለሶማሌ ህዝብ ትልቅ እድል ነዉ፡፡ ከዛም አልፎ ለኢትዮጵያ ህዝብም እንደዚህ ሁሉን በእኩልነት የሚያይ ሰዉ አስፈላጊ ነዉ፡፡ ሰሞኑን ባህርዳር መጥቶ ስለ አማራ ህዝብ የተናገረዉ ነገርም አስደሳች ነዉ፡፡ በዚህም ብዙ አክቲቪስቶች ሲያሞግሱት አይቻለዉ ሰዉየዉም ይገባዋል፡፡

ነገር ግን እኒህ አክቲቪስት ተብየወች ዶ/ር አምባቸዉ የመሰለ ሰዉ መሪ ሁኖ ወደ አማራ ክልል ሲመጣ ያዙኝ ልቀቁኝ ይሉ ነበር፡፡ ዶ/ር አምባቸዉ የአማራ ህዝብ በሃገሩ ላይ ቀና ብሎ እንዲሄድ ሁሉንም መስዋትነት እንከፍላለን፡፡ ህዝብን በጅምላ እየፈረጀ የሚሄድ ፖለቲካ ድርጅትም ሆነ ግለሰብ ከዚህ ሊቆጠብ እንደሚገባ እና የአማራ ህዝብ ለኢትዮጵያ የዋለዉን ዉለታ ማስታወስ ሲገባ ባላደረዉ ነገር የዉሸት ትርክት እየተነዛ የሚሄድ ፖለቲካ እዚህ ላይ ያበቃል፡፡ ህገመንግስት የሚባለዉ መስተካከል ግዴታ ነዉ፡፡ ከዚህ በኋላ የአማራን ህዝብ የሚጎዳ አንዳች ነገር ካደረግን ጠይቁን ልጆቻችሁ ነን፡፡ ያለፈዉ ይበቃል እያለ እንኳን እኒህ በስሜት የፏለሉ ተከታይ ስላገኙ ብቻ በፊስቡክ የአማራ ህዝብ መሪ ነን ብለዉ የሚያስቡ ጮርቃ ልጆች ህዝቡን ሲያወናብዱበት ነበር፡፡ በእኛ ፖለቲካ ዉስጥ ትልቁ ችግሩ የራስህን መሪ ማጣጣል እና ከፍ ሲልም ማጠጥፋት ዋነኛ ተግባር ሁኗል፡፡ እኔ እንደሚመስለኝ እኒህ አክቲቪስት ተብየወች ሳያስቡት መሪ የሆኑ መስላቸዉ እና ከአማራ ዉስጥ አንድ ደህና መሪ ሲመጣ እነሱን የሚገዳደር የሚመስላቸዉ ሰወች ናቸዉ፡፡ ትቂት እስክታድግ የኔ ጀግና የኔ መሪ ይሉህ እና እየበለጥካቸዉ የሄድክ የመሰላቸዉ ጊዜ ሰይፋቸዉን ይመዙብሃል፤ አሉባልታ ያስወሩብሃል፤ አዲስ አካዉንት ከፍተዉ አንተ ላይ ይዘምታሉ፡፡ ይህ የሚደረገዉ በፖለቲካ መሪዎች ብቻ አይደለም በዚሁ በፌስቡክ ጓደኞቻቸዉ ላይ ሁሉ ነዉ፡፡ እኒህ ሰዎች አእምሯቸዉ የሚነግራቸዉ የአማራ ህዝብ መሪ እንደሆኑ እና ተሰሚነት ይቀንስብናል ብለዉ የሚያስቡትን ደህና ሰዉ እንዲጠፋ ይጥራሉ፡፡ በሚጽፉት እና በሚያደርጉት ነገር ሰፊዉን የአማራ ህዝብ እንዴት እንደሚጎዳ አያስቡም፡፡ ቢያዉቁትም እራሱ የግልፍላጎታቸዉን ከሟላላቸዉ የአማራ ህዝብ ጉዳያቸዉ አይደለም፡፡ ፐርፌከት መሪ እንደማይገኝ ነገር ግን የተገኘዉን መሪ እያገዙ ጠንካራ መሪ ማድረግ እንደሚቻል ብዙ ጊዜ እዚህ ፕላትፎርም ላይ ተነጋግረናል፡፡

የአማራ ፖለተካ የቀን ተቀን ለቅሶ፤ የአሉባልታ፤ የስድብ፤ እና ከእዉቀት ነጻ በሆነ መንገድ እንዲጓዝ ያበረከትን ብዙ ሰዉች አለን፡፡ አንዳንድ ሰወች የአማራን ፖለቲካ እንዲመሩ ታግለዉ እንዲያታግሉ እድሉ ተሰቷቸዉ ሚዲያ ሁሉ አግኝተዉ ነገር ግን አቅም አጥሯቸዉ ፖለቲካችን እንኳን ሊመሩት በጥባጭ ሆኑ፡፡ ሰወች የሚናገሯትን ወይም ከሚጽፉት ዉስጥ ሁለት ዘለላ በማዉጣት በእርሷ ላይ አንድ እና ሁለት መጽሃፍ እየጠቀስክ ክሪቲሳይዝ ከማድረግ የዘለለ አንዳች የአማራን ህዝብ ወደፊት የሚያራምድ እና የኢኮኖሚ እና ፖለቲካዊ ጥቅሙን የሚያስጠብቅ ስትራቴጅ ወይም ከቀዉስ መዉጫ መንገድ ሲናገሩ እና ሲጽፉ አታዩም (deliver የማያደርጉ ፖለቲከኞች እና አክቲቪስቶች). የሚገርመዉ ተከታዮቻቸዉ የኔ ጀግና እያሉ የሚያሞግሷቸዉ ናቸዉ፡፡

ሌሎች ትቂቶች በባለፉት 4 እና 5 አመታት ስለ አማራ ፖለቲካ ስንጮህ የባለሃብት ስም እያነሳን እከሌን እንዲህ አድርጉ ወይም እንዲህ አታድርጉ ያልነበት ወቅት ትዝ አይለኝም፡፡ በቅርብ ጊዜ ግን የአማራ ህዝብን ዋና ዋና አጀንዳ ትተን በአክቲቪዝሙ ዉስጥ ስለባለሃብት የምንጽፍ እና የምንናገር ሞልተናል፡፡ በእርግጥ በእነዚህ ሰወች ገንዘብ እርዳታ የሚኖሩ እናዉቃለን፡፡ እነሱ ባካባቢዉ ባይኖሩ እንኳን ቤተሰቦቻቸዉን እንደሚደጉሙ እናዉቃለን፡፡ አንዳንዱ አክቲቪዝሙን ቢዝነስ አድርጎት የአማራን ህዝብ አጀንዳ ትቶ ሲለምንበት፤ ሲጋበዝበት እናያለን፡፡ እኒህንም ጭፍን ተከታዩ የኔ ጅግና ይላቸዋል፡፡

አንዳንዶቻችን ስለ ፖለቲካ አንዳች ነገር የማናዉቅ ነገር ግን ከእኛ በላይ ፖለቲካ ላሳር ነዉ ብለን የአማራ ፖለቲካ ቅርጽ አልባ እና የተወላገደ አካሄድ እንዲሄድ አድርጎታል፡፡ ትምህርቱን ሳይጨርስ በሞያሌ፤ በጅቡቲ፤በሊቢያ አድርጎ አዉሮፓ፤ የአረብ ሀገራት ካናዳ እና አሜሪካ ሁኖ ራሱን ሳያበቃ የቀን ስራ እና የቤት ስራ እየሰራ የአማራን ህዝብ ፖለቲካ እመራለዉ የሚል ብዙ ሰዉ ነዉ ያለዉ፡፡ ፖለቲካ የሚመራዉ በኢሊቶች ኢኮኖሚክስ ባጠኑ፤ ህግ ባጠኑ፤ ህክምና ባጠኑ፤ ፖሊሲ ባጠኑ፤ ሶስዮሎጅ ባጠኑ፤ ኢንጅነሪንግ ባጠኑ፤ ባዮ ሜዲካል ሳይነስ ባጠኑ፤ አንትሮፖሎጅ ባጠኑ፤ ስነ መንግስት ባጠኑ እና በመሳሰሉት ኢሊቶች ይመራል እንጅ ገና አይደለም ትልቁን የአማራን ህዝብ ፖለቲካ እና ታሪክ ሊሸከም ገና እራሱን ለመለወጥ በእየ ስቶሩ የሚሰራ፤ የሰዉ ቤት ዉስጥ የሚያገለግል፤ አጠቃላይ እራሱን ባልቻለ ግለሰብ የአማራ ህዝብ ፖለቲካ ቅርጽ አግኝቶ ወደፊት መራመድ አይችልም፡፡ በነገራችን ላይ እድሜህ 25 አመት እና ከዚያ በላይ ሁኖህ የሰዉ ቤት የምትጠርግ ከሆነ፤ የቀን ስራ የምትሰራ ከሆነ እራስህን አለወጥክም ማለት ነዉ፡፡ እራሱን ያልቻለ እና እራሱን ያላበለጸገ ወይም ያለወጠ ሰዉ ደግሞ እነ አጼ ፋሲል፤አጼ ምኒልክ፤ እነ አጼ ቴወድሮስ፤ እነ አክሊሉ ሀባተወልድ፤ እቴጌ ጣይቱ የመሩትን ፖለቲካ መምራት አይደለም ማሰቡ እራሱ ሃጢያት ነዉ፡፡ መጀመሪያ እራስህን ለዉጥ፡፡

አንዳንዶች ደግሞ በስድብ ለዉጥ ይመጣ ይመስል ኢንተርኔት ዉስጥ ገብቶ ሲሰዳደቡ መዋልን ስራየ ብለዉ የያዙ አሉ፡፡ እኒህ ሰወች ልጆቻችን ወይም ቤተሰቦቻችን አንኳን ምን ይሉን አይሉም፡፡ አንዳንዶች በሚገርም ሁኔታ የዩኒቨርስቲ አስተማሪዎች ናቸዉ እዚህ ሶሻል ሚዲያ ላይ በሚያሳፍር ሁኔታ ሲሳደቡ የሚዉሉት፡፡ እንደ ሙሁር የአማራን ፖለቲካ መስመሩን የማስያዝ ስራ ከመስራት ይልቅ በሚያሸማቅቅ መልኩ እርስ በርስም ሆነ ሌላዉ ጋር ወረደዉ ሲሰዳደቡ ይታያሉ፡፡ እኒህ ሰዎች አንዲት መጽሃፍ እንኳን አለማንበባቸዉ የሚታወቀዉ የሚጽፉት እና የሚናገሩት SHALLOW ሃሳብ ዋና ምስክር ነዉ፡፡ አንዳንዱ ለጠላት ዱላ በመሆን የአማራን ህዝብ በማወናበድ የተጠመዱ ናቸዉ፡፡ አንዳንዶቹ የአማራ ህዝብ አክቲቪስቶች ሳይሆኑ የግለሰቦች፤ የሆነች ጎጥ፤ የሆነ ባለሃብት አክቲቪስቶች ናቸዉ፡፡ እኒህም ጀግኖች ሁነዉ ይወደሳሉ፡፡

እንዲህ ዉጥንቅጡ በወጣ ፖለቲካ ዉስጥ ስንነሳ ይዘናቸዉ የተነሳናቸዉ ዋና ዋና የአማራ ፖለቲካ አጀንዳወች አሁን እንኳን ልናስታዉሳቸዉ ጭራሽ በራሳችን ህዝብ ላይ አዳዲስ አጀንዳ በመክፈት አንድነቱን በመፈታተን ያለንንም ልናጣዉ ምንም አልቀረንም፡፡ ሰሞኑን የምናየዉ የሄን ነዉ፡፡ የወያኔን የመከፋፈል አባዜ ሲቃዎም ለኖረ ሰዉ እስኪ ወርዶ በጎጥ እና በጥቅም ሲናቆሩ መዋል ምን ይባላል??

የአማራ ፖለቲካ ከስደተኛ (ጥቂቶችን አይመለከትም)፤ ከቀን ሰራተኛ፤ ከ 10ኛ ክፍል ባግባቡ ካልጨረሱ፤ ካልተማሩ፤ ከጎጠኛ፤ ከአሉባልተኛ፤ ከሸረኛ፤ እራሱን መሪ አድርጎ ከሾመ፤ ከስቶር ሰራተኛ እጅ ፈልቅቀን አዉጥተን የአማራን ህዝብ አጀንዳ 1፣ 2፣ 3 ብሎ ቆጥሮ ተጨባጭ ለዉጥ በሚያመጡ ሰዎች ካልተያዘ ነገሩ ሁሉ ከባድ ነዉ፡፡ በተለይ በተለይ ፖለቲካዉን ከህጻናት እጅ እና ከሰነፍ ፖለቲከኞች ቀስ አድርጎ አታሎ መቀማት ያስፈልጋል፡፡ የአማራን ህዝብ ተስፋ በሚሰጥ መልኩ፤ በስትራቴጅ የታጀበ፤ ራእይ ባላቸዉ ሰወች እና ራቅ አድርገዉ በሚያስቡ ጊዚያዊ ወጀብ በማያንገዳግዳቸዉ ሰወች ካልተያዘ የካብነዉ ካብ ሁሉ እየፈረሰ ጭራሽ ወደማንወጣዉ አዘቅት ዉስጥ እንገባለን እየገባንም ነዉ፡፡ ቢሰቀጥጥህም ይሄን ትዝብት ዋጥ ከማድረግ ዉጭ ሌላ አማራጭ የለህም፡፡ ዝም እየተባለ የህዝባችን ህለዉና አደጋ ዉስጥ እየገባ ነዉ፡፡

በተለይ በተግደርዳሪ የፖለቲካ ሃይሎች ዘንድ ያለዉ ዝግጁነት እና የፖለቲካ አጀንዳ የበላይነት ከእኛ ድክመት የመጣ መሆኑ እና አሁንም በዚሁ ድክመት ከቀጠልን በህዝባችን ላይ ከፍተኛ አደጋ የምንደቀን መሆኑ ታዉቆበት ፖለቲካዉን እንዘዉራለን የምትሉ ሰዎችም እራሳችሁን ገምግሙ ፡፡ተከታይ የሆናችሁ ሰዎችም የእዉነት እኒህ ሰዎች ከአንዱ የፖለቲካ ምእራፍ ወደ ሌላኛዉ የሚያሻግር ስብእና፤ ክህሎት፤ ዝግጁነት እና ቁርጠኝነት አላቸዉ ወይ ብሎ መገምገም ወሳንኝነት አለዉ፡፡ ዝምብሎ እንደ በግ መንጋ መግተልተልን ማቆም አለብን፡፡ የራሳችን ሰወች እንደ ሽንኩርት በጎጥ ሳይሸነሽኑን ሃይ ልንላቸዉ ይገባል፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *