“Our true nationality is mankind.”H.G.

በሶማሌ ክልል የተፈጸመ ኢሰብአዊ ወንጀል ለዓለም ዓቀፍ ወንጀለኞች ችሎት ሊቀርብ ነው፤ ዓለም ዓቀፍ ድጋፍም አለ!

በቅርቡ በባህር ዳር ተገኝተው ላለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት ብቻ ከሃያ ሺህ በላይ የሶማሌ ዜጎች በክልልሉ መገደላቸውን፣ በማስታወስ በየትኛውም መንግስት ክልሉ ላይ ከተፈጸመው የአስተዳደር ጥፋት በላይ በደል መድረሱን ያስታወቁት አቶ ሙስጠፋ ሞሃመድ ኦማር  የወንጀል ድርጊቱን እያስመረመሩ መሆኑ ተሰማ። ምርመራው ዓለም ዓቀፍ ተቋማት እውቅናና  ድጋፍ እያደረጉለት ነው። በተቃራኒ ዶክተር አብይ ላይ እንደሚደረገው የስም ማጠልሸቱ ሴራ እሳቸው ላይም እንደሚያነጣጥር ተሰማ።

በሚኖሴታ የሚኖሩና ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ አክቲቪስት ለዛጎል እንደተናገሩት እሳቸው በሚኖሩበት አካባቢ የህግ ባለሙያዎችን ድጋፍ በመጠየቅ በጉዳዩ ዙሪያ ስራ እየተሰራ ነው። ከዚህ በላይ ግን የክልሉ መሪ አቶ ሙስጣፋ ቀጥተኛ ተሳታፊና ተቆጣጣሪ የሆኑበት የምርመራ ስራ እየተሰራ መሆኑን እንደሚያውቁ አመልክተዋል።

በህግ ባለሙያዎች እየተካሄደ ያለው ምርመራ ባለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት ክልሉን ነጻና ገለልተኛ ሚዲያዎች እንዳያዩት ተደርጎ የተፈጸመውን ኢሰብአዊ ድርጊት እየመረመሩት ነው። እንደ እሳቸው ገለጻ እስካሁን ከተነገረውና ይፋ ከሆነው በላይ በርካታ የወንጀል መረጃዎች እየተገኙ ናቸው።

ኦጋዴን፤ የኢትዮጵያ [የህወሃት] ድብቅ ኃፍረት” በሚል ርዕስ ጋዜጠኛ ግራሃም ፔብልስ በኦጋዴን የሚካሄደውን የሚዘገንን ግፍ ሰኔ 15፤ 2008ዓም (June 22, 2016) ዩትዩብ ይፋ አድርጎታል፡፡ (ዘጋቢ ፊልሙ እዚህ ላይ ይገኛል) በዚህ ዘጋቢ ፊልም ከስቃይና ከሞት አምልጠው ወደ ኬንያ የስደተኞች ማረፊያ ደዳብ የገቡትን ዜጎች ስቃይ መስማት እስከሚያገፈግፍ ድረስ አስፍሮታል።

Ogaden 11ለምሳሌ አናብ “መረጃ እንድንሰጣቸው በየጊዜው ይመረምሩን ነበር፤ ሴቶችን ‘አስገድደን እንደፍራችኋለን’ እያሉ ያስፈራራሉ፤ ‘አንደፈርም’ ብለው አሻፈረን የሚሉትን ደግሞ ያንቋቸዋል፤ ሴቶቹ ራሳቸውን ስተው ባሉበት ወቅት እንኳን ይደፍሯቸዋል … እኔ የታሰርኩበት ትንሽ ክፍል ውስጥ ሰባት ሴቶች ነበሩ፤ ከዚያ ክፍል ነጻ የተለቀቀ የለም ማለት ይቻላል፤ ከእኛ በፊት እዚያ ክፍል የነበሩት ታርደዋል፤ ሌሎቹም በረሃብ እንዲሞቱ ተደርገዋል፤ ሬሣቸውንም በየጉድጓዱ ወርውረውታል፤ እኛ የነበርንበት ክፍል ሬሣ ነበር፤ የክፍሉን ሁኔታ ማንም ሊገምት የሚችል አይደልም (መግለጽ አይቻልም)፤ በክፍሉ የነበረው ሬሣ ባብዛኛው የወጣት ወንዶች ነው፤ እስከ አራት ቀናት ሬሣው በክፍሉ እንዲቆይ ይደረጋል፤ ከዚያ አውጥተው በየቦታው፤ በየመንገዱ ይወረውሩታል፤ …”  ስትል ግራሃም ባዘጋጀው ቪዲዮ ስትናገር እንደምትድመጥ ያስታወሱት አክቲቪስት ” ማንም ይሁን ማን በስማሌ ክልል የተፈጸመውን ወንጀልና ዘግናኝ ግፍ ሊቃወም፣ ፍትህና ርትዕ እንዲበየን ሊተባበር ይገባል” ብለዋል። 

 

ሁለት መቶ ሰዎች በጅምላ የተቀበሩበት መቃብር በኦሮሚያና ሶማሌ ክልል  አዋሳኝ አካባቢ ነው። ፖሊስ በቁጥጥር ስር ባሉት የቀድሞ የሶማሌ ክልል መሪ አቶ አብዲ ኢሌ ላይ የሚያደርገውን ምርመራ ተከትሎ በጥቆማ መገኘቱን ያወሱት እኚሁ የክልሉ ተወላጅ የሆንት አክቲቪስት ” ይህንን አይነት በርካታ ወንጀሎችን የፈጸሙ አካላትን በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ተጠያቂ የማድረጉ ስራ እንዳይሳካ በአቶ ሙስጣፋ ላይ የስም ማተልሸት ዘመቻ እንዲከፈት ዝግጅት እየተደረገ ነው። ምልክቶችም እየታዩ ነው” ብለዋል።

የክልሉ የለውጥ ደጋፊዎችና ምሁራን ይህንን ዘመቻ ለማምከን እንደራለን ካሉ በሁዋላ የአቶ ሙስጣፋ አማራ ክልል ሄዶ የቀደመውን የፈጠራ ትርክት መቃወማቸው የህወት ሰዎችን እንዳስቆጣ መረጃው እንዳላቸው አመልክተዋል። 

ogaden -the tplf shame

በሚከተሉት መርህና በአስተዳደር ዘቢያቸው፣ ከዚህ ባህሪያቸው በመነሳት በሚያቀርቡት ንግግር ከክልላቸው አልፈው በአገር ደረጃ ቀልብ የሳቡት አቶ ሙስጠፋ እሳቸው በሚመሩት ክልል ሁሉም ብሄረሰብ በስላም መኖር ካልቻሉ ስርዓቱ አፓርታይድ እንደሚሆን ይፋ መናገራቸው  ጨምሮ በተለያዩ ወቅቶች የሰጡዋቸው መግለጫዎች ተክትሎ ክልሉን በአዲስ ለማተራመስና እሳቸውን ነጥሎ የማጠልሸት ስራ ሲሰራ አገር ወዳድና፣ ፍትህ ወዳድ ሃይሎች እንዲቃወሙና እንዲያወግዙ ጠይቀዋል።

በኦሮሚያና በስማሌ ክልል አጎራባች ቀበሌዎች ዙሪያ ተመሳሳይ የቀድሞው ዓይነት ረብሻና ሁከት ለማስነሳት ገንዘብ የሚረጩ ሃይሎች በሚያሰራጩት የማህበራዊ ሚዲያዎች ዘመቻ መወሰድና መጠለፍ አግባብ እንዳልሆነም አመልክተዋል።

እነ ጃዋር መሀመድ በማይመለክታቸው የክልል ጉዳዮች ገብተው ከሚፈተፍቱ ወደ እርቅ የሚወስደውንና በኦሮሞ ማህበረሰብ ላይ የተፈጸመውን ኢሰብአዊ ድርጊት አስጠንተው ወደ ህግ እንዲቀርብ ቢሰሩ እንደሚሻልም ምክር ሰጥተዋል።

0Shares
0