ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአቶ በረከት ስምዖንና አቶ ታደሰ ካሳ ጉዳይ ላይ ብይን ለመስጠት ለመስከረም 30 ቀን 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ፍርድ ቤቱ ሐምሌ 5 ቀን 2011 ዓ.ም በዋለው ችሎት አቃቤ ህግ በአቶ በረከት ስምዖንና አቶ ታደሰ ካሳ ላይ ያቀረባቸውን የሰነድ ማስረጃዎች መርመሮ ብይን ለመስጠት ለሐምሌ 18 ቀን 2011 ዓ.ም ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሰል።

ፍርድ ቤቱ በዛሬው ዕለት በዋለው ችሎትም አቃቤ ህግ ያቀረባቸው የሰነድ ማስረጃዎች በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረቡ መሆናቸውን በመግለፅ፥ አቃቤ ህግ ማስረጃዎችን እስከ መስከረም 22 ቀን 2012 ዓ.ም በአማርኛ ቋንቋ አስተርጉሞ እንዲያቀርብ ትዕዛዝ አስተላልፏል።

ፍርድ ቤቱ የሚቀርቡትን የሰነድ ማስረጃዎች መርምሮ ብይን ለመስጠትም ለመስከረም 30 ቀን 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በጥረት ኮርፖሬት የሀብት ምዝበራ ተጠርጥረው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙት አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሳ በሙስና እና ስራን ባመቺ ሁኔታ ባለመስራት ወንጀሎች አራት ክሶች የተመሰረቱባቸው መሆኑ ይታወሳል።

በናትናኤል ጥጋቡ – ፋና

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   በሙስና ወንጀል የተገኘን ንብረት ማሳገድ ፤ ማስመለስ፡ ማስወረስ እና ማካካስ በፀረ ሙስና ህጎች

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *