የፌዴራል እና የክልሎች የሥራ ዕድል ፈጠራ 2ኛ መደበኛ መደረክ በዛሬው ዕለት በባሕር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው። በመድረኩ የተገኙት የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ኤፍሬም ተክሌ በኢትዮጵያ በተያዘው የበጀት ዓመት 3 ሚሊየን ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ዕቅድ ተይዟል ብለዋል።

እንዲሁም እስከ 2017 ዓ.ም ለ14 ሚሊየን ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዷል ያሉት ኮሚሽነሩ ፥ እስከ 2022ዓ.ም ደግሞ ለ20 ሚሊየን የሀገሪቱ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር መታቀዱን ጠቁመዋል።

በተየዘው በጀት ዓመት የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካትም ከፌዴራል እስከ ታች የነበረውን የቅንጅታዊ አሠራር ክፍተት ለመቀነስ ስምምነት ላይ ተደርሷል ተብሏል።

በ2012 የበጀት ዓመት ለሚደረገው የሥራ ዕድል ፈጠራ የክልል መሪዎች አምነውበት እንደተቀበሉት ተነግሯል። ለ3 ሚሊየን ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ዋነኛ የሥራ ዕድል ማነቆዎችን መፍታት እና ጥቅም ላይ ያልዋሉ ዕድሎችን ለመጠቀም ሦስት ዘዴዎችን መቀረፃቸውን አብመድ ዘግቧል።

የመጀመሪያው የሥራ ዕድሎችን ስብጥር በዓይነት እና በየክልሎች ፀጋ ማስፋፋት፣ የዜጎችን የሥራ ዝግጅት ማበልጸግ እና የሥራ ማገናኘት ሥራዎችን መሥራት እና የፖሊስ ማሻሻያዎችን ማድረግና መተግበር ላይ እንደሚሠራም ተብራርቷል፡፡

ባለፈው የበጀት ዓመት በከተማ የሥራ ዕድል ፈጠራ ለ1 ነጥብ 6 ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ የተሳካው ግን ለ1 ነጥብ 3 ዜጎች ብቻ ነው፡፡

በከተማ የሥራ ዕደል ፈጠራ ባለፉት አራት ዓመታት ለ8 ነጥብ 5 ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ዕቅድ ተይዞ ለ6 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል፤ ይኼም 79 በመቶ ነው። በፌዴራል ደረጃ ደግሞ ለ1 ነጥብ 3 ሚሊየን ዜጎች የሥራ ዕድል የተፈጠረ ሲሆን ፥ የዕቅዱ 81 በመቶ መሳካቱም ታውቋል።

ፍና

Related stories   የ80ኛው የኢትዮጵያ አርበኞች ቀን በአዲስ አበባ ተከበረ

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *