“Our true nationality is mankind.”H.G.

መዓዛ አሸናፊ ማስፈራሪያ እየተሰነዘረባቸው ነው!! ” ትግራይ ላይ ውታደር [የመከላከያ ሰራዊት] ከዘመተ ለዜና ሳይበቃ በቅሌት ይጠናቀቃል”

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ወ/ሮ መዓዛ  አሸናፊ ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው ነው። የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር በበላይነት እንደሚመራው በሚታወቀው ዲጂታል ወያኔ ማህበራዊ ገጽ ሳይቀር ወይዘሮዋ ዛቻ እየበረታባቸው መሆኑ ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎችን እያስቆጣም ይገኛል። በተለይ የኦሮሞና የአማራ ተወላጆች ሲጨፈጨፉ ዝምታን መርጠው የነበሩ የትግራይ አክቲቪስቶች ወይዘሮዋ ለይተው ትግራይን ሳይናገሩ ጉዳዩን ወደ ትግራይ በመጎተት ” ለዜና ሳይበቃ የኢትዮጵያን ሰራዊት እንደመስሳለን”  ማለታቸው አስገራሚ ተደርጎ ተወስዷል።

በህይወት ተሞክሯቸው የጦርነትንም ሆነ ሃይል አዘል ጉዳይ ሲናገሩ ተሰምተው የማያውቁት ወይዘሮ መዓዛ ፣ ማስፈራሪያ የበዛባቸው  አንድ ክልል የፍርድ ቤት ውሳኔ አላከብርም ካለ እንዴት መንግስት በሃይል ህግ ሊያስከበር እንደሚገባው ለማመላከት በአሜሪካ በ1950ዎቹ የነጮችና የጥቁሮች የትምህርት እድልን አስመልክቶ ከጥቁሮች የቀረበውንና በፍርድ ቤት የተወሰነውን ውሳኔ አልቀበልም ባለች ግዛት ገጠመኝ በማንሳታቸው ነው። በወቅቱ አገሪቷን ያስተዳድሩ የነበሩት ፕሬዚደንት ድዋይት አይዘንአወር ውሳኔውን ለማስፈፀም ኃይል ተጠቅመው እንደነበር ማመልከታቸው በተለይ ለትግራይ ክልል የተጠራ የክተት ጥሪ ተደርጎ መወሰዱ ነው።

የፕሬዚደንቷ ንግግር በተለይ የትግራይ ክልል ላይ ያነጣጠረ ተደርጎ የተወሰደበት ምክንያት ባይገለጽም ዲጂታል ወያኔ የሚባለውና ሰፊ ድርጅታዊ መዋቅር የተበጀለት የፕሮፓጋንዳ ማምረቻና ማከፋፈያ ገጽ ” በፍርድ ቤት ጣልቃ እንደማንገባ ሁሉ እሳቸውም በእኛ ጉዳይ  ጣልቃ ባይገቡ ይመረጣል።” ሲሉ አቶ ጌታቸው ረዳ መናገራቸውን በፊት ገጹ አስፍሯል። 

” … አብይ ለአገራችን ብቻ ሳይሆን ለቀጣናው ስጋት የሆነ አደገኛ አሸባሪ ” ሲል በገሃድ የሚሳደበው በህወሃት በጀትና አመራር ሰጪነት የሚተዳደረው ዲጂታል ወያኔ ብቻ ሳይሆነ የዚሁ ክንፍ አውራ እንደሆነ የሚነገርለት ዳኔል ብርሃኔም ወደ ትግራይ የሚላክ ጦር ካላ ለዜና ሳይበቃ የሚጠናቀቅ የቅሌት ድራማ እንደሚሆን በኢትዮጵያ መከላከያ ላይ ተሳልቆ ማስፈራሪያውን አስፍሯል።

በከፍተኛ ደረጃ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የሚመራውን መንግስት በማጠልሸት የተጠመደውና ከፍተኛ የበጀት ድጎማ የተቆረጠበት የዲጂታል ወያኔ ጠርናፊ ዳንኤል ብርሃኔ  መንግስትን “ጁንታ” በማለትና በትግራይ ላይ ጦር የማዝመት እቅድ እንዳለ በማስመሰል  ” የፌዴራል መንግስት ተብየው ጁንታ በትግራይ ላይ ወታደር ለማዝመት ፈጽሞ አይሞክርም። ቢሞክርም ከሁለት ወይም ሶስት ቀን የማያልፍ የቅሌት ድራማ ይሆናል። መከሰቱን ሳንሰማ፣ ለዜና ሳይበቃ፣ የሚጠናቀቅ ትንሽ ክስተት ነው የሚሆነው። ቁም ነገሩ እሱ አይደለም።የመዓዛ አሸናፊ መዘባረቅ አጀንዳ የሆነው፤ እሷ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት በመሆኗ እና በትግራይ ህዝብ ላይ በዚህ ደረጃ ዛቻ መደረጉ ከመርህ ሆነ ከሀገራዊ አንድነት አንጻር ትክክል ስላልሆነ ነው። እንዲህ አይነት ጸረ-ትግራይ ፉከራ እና ቀረርቶ የሚቀበል እና የማያወግዝ ህዝብ ጋር አብሮ መኖር ፋይዳው ምንድን ነው ነው ጥያቄው! ትግራይ በጀግኖች ልጆቿ ታፍራና ተከብራ ትኖራለች” ሲል እብሪቱን እተደበቀበት ትግራይ ሆኖ ጽፏል። የእሱ አላማ አራማጆችና ተከታዮችም በማስፈራሪያ ኢትዮጵያ ላይ ሳይነኩ ጦር ሰብቀዋል።

በዋናው ተፈላጊ የቀድሞው የድህንነት አዛዥ ጌታቸው አሰፋ ትዕዛዝ ከፍተኛ በጀት ከመንግስት የለማት ድርጅቶች ይከፈለው የነበረው ዳንኤል ” መዓዛ አሸናፊ ለፍትህ መዋቅሩ እና ለፌዴሬሽኑ ውርደት ሆናለች። ትግራዋይ የፖለቲካ እስረኞችን ለሚዳኙ ዳኞች መጥፎ ሲግናል ሰጥታለች። በነሱ ላይ እየደረሰ ላለው የተዛባ ዳኝነት ሂደት ሁሉ በግል ተጠያቂ ትሆናለች። ለራሷ ክብር ካላት በአስቸኳይ ትልቀቅ እና ኢዜማ ትግባ ” ሲል ተዛልፏል። በጉዳዩ ምንም የሌለበትን አዜማን አንስቶ ለማጣጣል ደክሟል።

ቢቢሲ መርጦ ያናገራቸው የትግራይ ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ አቶ አማኑዔል አሰፋ “መልዕክቱ ለማንም ይሁን ለማን፤ በኢትዮጵያ ያሉ ችግሮች መፈታት ያለባቸው ሕገ መንግሥቱን መሰረት በማድረግ መሆን አለበት፤ ካልሆነ አገሪቷን ወደ ሌላ አቅጣጫ ሊያመራት ይችላል” ሲሉ አስፈራርተዋል። አክለውም “ሃሳቡ ከፍተኛ አደጋ የሚያስከትል፣ ተገቢነት የሌለው፣ ሕገ መንግሥታዊ ያልሆነ፣ ገለልተኛ በሆነው የፌደራል ፍርድ ቤት መነሳት ያልነበረበት ነው” ብለዋል። ይህንን ይበሉ እንጂ ወይዘሮ መዓዛ የትኛውን ክልል ለይተውና መርጠው በዚህ ምሳሌያቸው እንዳመለከቱ ያሉት ነገር የለም። ቢቢሲም የወይዘሮ መዓዛ ለይተው የትግራይ ክልል ስለማለታቸው አልጠየቀም። ሪፖርቱንም ሲያዘጋጅ ክብርት መዓዛ በተለይ የትግራይ ክልል ላይ አነጣጥረው ስለመናገራቸው ያለው ነገር የለም።

የፌደራል ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሰለሞን እጅጉ “የትኛውም የፍርድ ቤት ውሳኔ የማይፈፀም ከሆነ ፍርድ ቤት የለም ማለት ነው፤ አስፈፃሚው አካል የፍርድ ቤት ውሳኔን የማስፈፀም ኃላፊነቱን መወጣት አለበት” ያላሉ። 

አቶ ሰለሞን እንደሚሉትም ምሳሌው የፍርድ ቤት ውሳኔዎች በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ተፈፃሚ መሆን አለባቸው፤ እንዲፈፀሙ የሁሉም አካላት ተሳትፎ እንደሚያስፈልግ ለመናገር የመዘዙት ምሳሌ ነው- የአሜሪካው ተሞክሮ። መንግሥታት የፍርድ ቤት ውሳኔዎችን ለማስፈፀም እስከምን ድረስ መሄድ እንደሚችሉ ፕሬዝዳንቷ በምሳሌው ለማስረዳት መሞከራቸውን ይናገራሉ።

ንግግራቸው ትግራይ ክልል ላይ ያነጣጠረ ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ለሚሰጡ ሰዎችም “ንግግሩ ሌሎችንም የተመለከተ ነበር” ሲሉ ምላሽ ሰጥተውናል። በንግግራቸውም በተለያዩ ክልሎች እየተፈፀሙ ያሉ ድርጊቶችን ሲያነሱ እንደነበርም ገልፀዋል።

የምሳሌው አግባብነትን በተመለከተ ያነሳንላቸው አቶ ሰለሞን “የፍርድ ቤት ትዕዛዝና ውሳኔን ለማስፈፀም ሊደረጉ ከሚገባቸው ነገሮች መካከል አንዱ ማሳያ ተደርጎ ነው የተወሰደው፤ ዲሞክራሲያዊ የሆነ የፍትህ ሥርዓት ሰፍኖባቸው የሚታዩ አገራት በእንደዚህ ዓይነት ተግዳሮት ውስጥ አልፈው ነው እዚህ የደረሱት ለማለት እንደማሳያነት መጠቀሱ አግባብነት የለውም የሚል ሃሳብም አቋምም የለኝም” ሲሉ የግል አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

“የትኛውም የፍርድ ቤት ውሳኔ የማይፈፀም ከሆነ ፍርድ ቤት የለም ማለት ነው” የሚሉት አቶ ሰለሞን አስፈፃሚው አካል የፍርድ ቤት ውሳኔን የማስፈፀም ኃላፊነቱን መወጣት አለበት ይላሉ።

ይህ ካልሆነ ግን ትርጉም እንደሌለው ከማስረዳት በዘለለ ፕሬዝዳንቷ ያነሱት ምሳሌ እንዲህ ዓይነት ውዝግብ ያመጣል ብለው እንደማያምኑ ለቢቢሲ አስታውቀዋል። 

በከፍተኛ ወንጀልና ሙስና የሚፈለጉት የህወሃት መሪዎች ማንኛውንም ጉዳይ ለትግራይ ህዝብ የተወረወረ በማስመሰል የትግራይን ህዝብ መመሸጊያ ማድረጋቸውን፣ አማራጭ እንዳይሰማ መደረጉን፣ የተለየ ሃሳብ እንዳይሰማ መታፈኑን፣ የተለየ አመለካከት ማራመድ ከሃጂ የሚያሰኝና ከማህበራዊ ጉዳዮች እንዲያስገልል መደረጉን የአረና ትግራይ አመራሮች መናገራቸውን የጠቆሙ፣ ” ችግሩ ህዝቡ እውነቱን እንዳይሰማ መታፈኑ ነው”፡ ሲሉ መናገራቸው

Related stories   “ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን በአንድነት በመከባበር፤ በመተሳሰብ እና በመረዳዳት ሊያከብር ይገባል”

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0