ZAGGOLE – ዛጎል

“Our true nationality is mankind.”H.G.

የምፅዓት ቀን ምልክቶች….

Dejene Assefa

... የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ትላንት ሃምሌ 27 አንድ ወሳኝ ጥያቄ ቀረበላቸው…

<< በህግ መጠየቅ ያለባቸው ተጠርጣሪ ግለሰቦች በተለያዩ ክልሎች ተደብቀው መኖራቸውን እያወቃችሁ ፍትህ በሃገሪቱ ማስፈን እንዴት ይቻላል?” የሚል ጥያቄ። 
.
ክብርት ወ/ሮ መዓዛም…

“አይዘንሃወር የሚባል ፕሬዚደንት በኖረበት ዘመን የአሜሪካን አንድ ስቴት (ክልል) ዛሬ በኛ ሃገር እንደሚታየው አስቸገሯቸው ነበር። ቀጥታ የአገሪቱን ጦር ልኮ ክልሏን በቁጥጥሩ ስር ካደረገ በኋላ ነው ህግ ማስከበር የቻሉት። እኛም ለፍትህ ስንል ተመሣሣይ ነገር ማድረግ ይገባናል እላለሁ። አሁን የረቀቀውን ህግ አልፈርምም ያለው አንድ ክልል ብቻ ነው።” የሚል ምላሽ ሰጡ።
.
ይህን ተከትሎም ከፍተኛ ጩኸት ፣ ድንጋጤ ፣ ዋይታ ፣ ለቅሶ ፣ ፊት መንጨት ፣ ጥርስ ማፋጨት ፣ ወዘተ የመሳሰሉ በፍካሬ እየሱስ የተጠቀሱ ሁሉም የምፅዓት ቀን ምልክቶች ከዚያ መንደር ብቻ እየተሰሙ ነው። በዚያ ላይ የፈሪ ዛቻ የሚሉት ዓይነት ወይ ዛቻ አይሉት ወይ ፍርሃት መላ ቅጡ የጠፋው የበሰበሰ ቀረርቶ ነገርም ያንቋርራሉ። በወ/ሮ መዓዛ እና በሁሉም ሴቶች ላይ ያነጣጠር ፆታን ማዕከል ያደረገ ዘለፋ ስድብ እና የማጥላላት ዘመቻም ከፍተዋል። ወደፊት በሚጠየቁት ይጠየቃሉ።
.
የዛ ሰፈር ልጆች ይህን ሁሉ እያደረጉ ያሉት፡ በህግ ይፈለጋል የተባለን ሰው ለዚያውም በፍርድ ቤት የመጥሪያ ትዕዛዝ ወጥቶበት ያለ ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነት (ቢያንስ በሚመስል) የህግ አግባብ በፖሊስ ተይዞ ወደ ፍትህ አደባባይ እንዲቀርብ የታዘዘን ተጠርጣሪ ግለሰብን አሳልፈን አንሰጥም በሚል አሳፋሪና የበሸቀጠ ምክንያት ነው። እነዚህ ሰዎች ናቸው እንግዲህ ስለ “ሞራል” የሚያወሩት። ጉድ ነው! ለነገሩ “ፍትህ ለአብዲ ኢሌ” ብለውስ የለ ራሱ አብዲ ኢሌ ይቅርታ እየጠየቀ?! ችግሩ ክፉ ልምድ ቶሎ አለመልቀቁ ነው! 
.
ሌላው እኔን የገረመኝ በራያ ህዝብ ላይ በአስር ሺህ የሚቆጠር የትህነግ ልዩ ሃይል ሲዘምት ምንም አላሉም። ምክንያቱም የራያ ህዝብ ትግሬ ባለመሆኑ ቢገደል ቢታፈን ደንታቸው አይደለምና። በጣም ያስደነቀኝ ግን የራያ ህዝብ ያ ሁሉ ሲሆንበት አሁን እነሱ እየጮሁ ያሉትን ያህል እንኳን አልጮኸም። ለነገሩ “ፉከራ” Vs “እውነተኛ ጀግንነት” ልዩነቱ ግልፅ ነው! ለማንኛውም የራያ ህዝብ ትግሉን ያጠናክር። ድሉ እየቀረበ ነው።

.
ብቻ ከጌታቸው አሰፋና ጓዶቹ ጋር በተያያዘ ከዚህ ቀደም ተጠርጣሪዎችን ይዞ ለህግ እንዲያቀርብ የፌደራል ፖሊስ ከፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ተቀብሏል። የፌደራል ፖሊስ አባላትም መጥሪያውን ለማድረስ መቀሌ ድረስ በተደጋጋሚ ሄደው የደረሰባቸው ነገር የሚታወቅ ነው። በርግጥ የደረሰባቸውን ነገር በፌዴራል ፖሊስ አባላቱ ብቻ እንደደረሰ ውርደት አድርጎ ማሰብ አይቻልም። ምክንያቱም ትርጉሙ ሃገራዊ አንድምታ ያለው ፣ የህግ የበላይነትን ጥያቄ ውስጥ የሚጥል ፣ በአንድ ሃገር ስንት መንግስት አለ የሚል ጥያቄን እና ጥርጣሬን የሚጭር ጉዳይና ዘርፈ ብዙ ምልከታ ያለው በመሆኑ ነው። 
.
የተከበሩ ወ/ሮ መዓዛም የተናገሩት ከዚህ አንፃር ነው። ህግን ለማስከበር በሚደረግ ወሳኝ የሃገር ኩነት ላይ አስቸጋሪ እክል እየፈጠረ ያለን አካል ለህግ ተገዥ እንዲሆን ማድረግ የመንግስት ግዴታ መሆኑን ነው። ለዚህ ደግሞ ለህገ መንግስቱ መከበር ዘብ የቆመው የሃገር መከላከያ ሰራዊት እና የፌደራል ፖሊስ የሚሰጠውን ሃገራዊ ተልእኮ መወጣት ግድ ይለዋል። 
.
ጉዳዩ በዚህ አግባብ ተነጥሎ ሊታይ ሲገባው ወፈፌዎቹ ግን ነገሩን “በትግራይ ህዝብ ላይ እንደታወጀ ጦርነት” አስመስለው እየታተሩ ይገኛል። በዚህም ምንም የሚፈይዱት ነገር ባይኖርም የትግራይን ህዝብ ግን ምን ያህል እንደሚጠሉትና ጦርነትን እንዴት እንደሚናፍቁ በግልፅ አስመስክረዋል። ህዝቡን ምሽግ (human shield) ለማድረግ የሚታትሩ ክፉዎች ናቸው። ለነሱ የግል ጥቅም ሲባል የትግራይን ህዝብ ባልዋለበት ሊጥዱት የሚጣደፉ አርዮሳዊያን!!!
.
መንግስት ግን የነዚህን የቁራ ጩኸት ወደ ጎን በመተው ህግን እና ህግን ብቻ ተከትሎ የህግ የበላይነትን ያስከብር!!! በቂ መረጃም ለትግራይ ህዝብ ይስጥ። ስለ አንድ ወንጀለኛ ብሎ የትግራይ ህዝብ አላስፈላጊ ዋጋ መክፈል እንደሌለበት የማንቃት ስራ ይሰራ። ጉዳዩ ተጠርጣሪን በህግ ለመጠየቅ ያለመ እንጅ ከህዝቡ ጋር የተያያዘ አለመሆኑን ያስረዳ። አስፈፃሚው አካልም የታዘዘውን በሚገባ ይፈፅም። ያኔ ሃገር እንዳለን ፣ መንግስትም እየሰራ እንደሆነ ፍንጭ እናግኝ። ከዚያም ወደሚቀጥሉት የፍትህ ጥያቄዎች እንሸጋገራለን። ገና ብዙ ሃገራዊ ጥያቄዎች ያሉብንና መስተካከል አለባቸው ብለን የምናስባቸው አያሌ ጉዳዬች አሉንና!!!
.
ፍትህ ለፍትህ!!

Related stories   የአውሮፓ ህብረት የይስሙላ ምርጫዎች ሲታዘብ ቆይቶ አሁን አልታዘብም ያለበትን ምክንያት ለኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያሳውቅ ተጠየቀ