የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶክተር) የዴንማርኩን ዓለማቀፍ የልማት እና ትብብር ሚኒስትር ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

የዴንማርኩን ዓለማቀፍ የልማት እና ትብብር ሚኒስትር ራስመስ ፕሬህን ከውይይታቸው በኋላ ለአብመድ እንደገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እየሠሩት ባለው የዴሞክራሲ እና ሀገራዊ ለውጥ ማሻሻያ መንግሥታቸው ደስተኛ ነው፡፡ በተለይ ኢትዮጵያ እየተገበረች ያለችውን የአረንጓዴ ልማት መርሀ ግብር ለመደገፍ የዴንማርክ መንግሥት ቁርጠኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

Related stories   የኮቪድ ጽኑ ታማሚዎች ቁጥር መብዛቱ በዲላ ሆስፒታል አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ጫና አስከትሏል

ወደ ኢትዮጵያ ከመምጣታቸው በፊት ኢትዮጵያ እየተገበረች ስላለችው የአረንጓዴ ልማት ሥራ መስማታቸውን ተናግረው ይህን ሥራ ለማዬት እና የመንግሥታቸውን ድጋፍ ለመግለጽ መምጣታቸውን አስታውቀዋል፡፡ በተመለከቱት የአረንጓዴ ልማት ሥራ መደሰታቸውንም ተናግረዋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ፕረስ ሴክሬተሪ ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ዴንማርክ የኢትዮጵያ አጋር ናት ብለዋል። ወደፊት የሁለቱ ሀገራት ትብብር በሚጠናከርበት ጉዳይና ኢትዮጵያ እያካሄደች ባለችው ሁለንተናዊ ለውጥ ላይም ውይይት ተደርጓል ነው ያሉት፡፡

Related stories   የኮቪድ ጽኑ ታማሚዎች ቁጥር መብዛቱ በዲላ ሆስፒታል አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ጫና አስከትሏል

ዘጋቢ፡-አንዷለም መናን -ከአዲስ አበባ

ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 01/2011 ዓ.ም (አብመድ)

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *