“Our true nationality is mankind.”H.G.

መዓዛ አሸናፊ ማንም ሰው ምንም ዓይነት ስልጣን ቢኖረው ከሕግ በላይ ሊሆን እንደማይገባው መልእክት አስተላለፉ

የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝደንት ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ማንም ሰው ምንም ዓይነት ስልጣን ቢኖረው ከሕግ በላይ መሆን እንደማይገባው የፌዴራል ፍትህ አካላት ዓብይ ኮሚቴ የፍትህ ወር በሚል ስያሜ በሚያድገው እንቅሰቃሴ ሐምሌ 26 ቀን 2011 ዓ.ም በስካይ ላይት ሆቴል በተከሄደ የመጀመሪያ የውይይት መድረክ ላይ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ፕሬዝደንቷ የፍትህ አካላቱ ጥምረት አብይ ኮሚቴ ከባፉት ዓመታት ለየት ባለ ሁኔታና ይዘት የፍትህ ወር በሚልስ ስያሜ የጀመሩት እንቅስቃሴ በሃገራችን ከለውጡ ጋር በተያያዘ በተከሰተው የሰላም መረበሽና የህግ መደፈር ሳቢያ በየደረጃው ሕዝቡ እያቀረበ ያለውን የህግ የበላይነት ጥሪ የማዳመጥና የማስተናገድ ዋናው ኃላፊነት የፍትህ አካላቱ እንደሆነ በማመን የህግ ተገዢ የመሆን ንቅናቁ መፍጠር ነው ብለዋል፡፡

የህግ ተገዢ ነኝ በሚል መሪ ቃል በተጀመረው የፍትህ አካላት የአንደ ወር እንቅስቃሴ የሚተላፉ መልእክቶች ማንም ሰው ለተግባሩ ተጠያቂ የማይሆንበት ምክንያት አይኖርም፤ ሰዎች ሁሉ በሕግ ፊት እኩል መሆናቸው መረጋገጥ አለበት፤ እና ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ተቋም ወደ ተገቢው የስልጣን አካል በመቅረብ ለደረሰበት ችግር ፍትህ መጠየቅ እና ማግኘት ይችላል/ትችላች ላይ እንደሚያተኩሩ የገለጹት ክብርት ወ/ሮ መዓዛ እነዚህን መብቶች ግደታዎች የሚደነግጉ አገር አቀር ህጎችም ሆኑ ዓለም አቀፍ ቃልኪዳኖች ጥረት እንደሌለ ጠቁመዋል፡፡

በህግና ስርዓት ካልተመራ፤ ሕብረተሰባችን እርስ በእርሱ እንዲሁም በመንግስት ላይ ያለው መተማመን ከተዳከመ፤ በየእለቱ በሰላም ለመኖርም ሆነ ከፍ ያትን የዲሞክራሲ እና የልማት ሕልሞቻችንን ለማሳካት አንችልም ያሉት ክብርት ወ/ሮ መዓዛ በህግና በስርዓት መመራት፤ ህብረተሰባችን እርስ በእርሱ እንዲሁም መንግስት ላይ ያለው መተማን እዲዳብር ለልጆቻችን ይህንን እውነታ ደግመን ደጋግመን ማስተማር እንዳለብን መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንቷ ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አያይዘውም ለውጥ ውስብስብ እና ውጣ ውረዶች የበዙበት ጊዜ እ የጋራ ተልዕኮ መገንባት የሚጠይቅ ሂደት በመሆኑ ሕግን በማስከበር ረገድ የተፈጠሩ ክፍተቶችና ተግዳሮቶች መኖራቸውን መቁመው በሂደቱ አላስፈላጊ ዋጋ እንዳያስከፍል መጠንቀቅ ተገቢ መሆኑን መክረዋል፡፡ የመደበኛ የፍትህ አካላት በተወሰነ የሰው ሃይል፣ በውስን እውቀትና ክህሎት እንዲሁም በውስን ቁሳዊ ግብአት ስራቸውን ለማሳካት የሚጣጣሩ ናቸውና ተከታታይ የችግር ጎርፍ ለመቋቋም ሊያዳግታቸው ይችላል ስለሆነም ከመደበኛ የፍትህ ስርዓት በተጓዳኝ በአጠቃላይ የሰላምና መረጋጋት ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡

በመጨረሻም የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንትና የፍትህ አካላት ጥምረት አቢይ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክብርት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ሃገራችን ካለችበት አሳሳቢ ሁኔታ ወደተሻለና ተስፋሰጪ ሁኔታ ፈጥና እንድትሸጋገር የፖለቲካና የሃሳብ መሪዎች በሁሉም ጉዳይ ባይስማሙ እንኳን የዕለቱን ሳይሆን የታሪክ አደራን ከግምት ውስጥ በማስገባት ዋና ዋና የጋራ መግባቢያ አጀንዳዎች (Main common Agenda) ሊኖራቸው እንደሚገባ መክረዋል፡፡

በሽግግር ወቅት የመደበኛ ፍትህ ስርዓት እድሎች እና ተግዳሮቶች በሚል ርዕስ በተዘጋጀ የውይይት መድረክ የሰላምና የእርቅ ኮሚሽን ተልዕኮና እቅድ በካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስ ደምረው ቀርቧል፡፡ የእርቀ ሰላም ኮሚሽን አባል የሆኑት ዶ/ር ሰለሞን አየለ በኮሚሽኑ ማቋቋሚያ ዓዋጅ ላይ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በቅርቡ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው የተሾሙት ዶ/ር ዳንኤል በቀለ በእርቀ ሰላም ኮሚሽን መቋቋም፤ ዓላማና ተግባራ ላይ አለም አቀፍ ተሞክሮ ጋር በማነጻጸር የምልከታ ሃሳብ አቅበዋል፡፡ የእርቅ ተሞክሮዎች በኢትዮጵያ ታሪክ በሚል ርዕስም የውይይት ሃሳብ በዶ/ር የራስወርቅ አድማሴ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

Share and Enjoy !

0Shares
0
0Shares
0