“Our true nationality is mankind.”H.G.

የመለስና የትሕነግ ሌጋሲ – እያደር እየተገለጠ ነው !! የካፍ መስራች አገርና ሕዝብ መሳቂያ ተደረጉ

ላለፉት 26 ዓመታት የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር በበላይነት ሲመራት የነበረችው ኢትዮጵያ አንድም ዓለም  ዓቀፍ መስፈር የሚያሟላ ስታዲየም እንደሌላትና ኢትዮጵያ ዓለም ዓቀፍ ውድድሮቿን በሌሎች አገራት እንድታካሂድ ካፍ መወሰኑን ተከትሎ የዚሁ ተገንጣይ ቡድን ደጋፊዎች የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መንግስትን ተወቃሽ አድርገው እየተሳለቁ መሆናቸው አስገራሚ እንደሆነባቸው በዜናው ያዘኑ ለዛጎል ተናገሩ።

“የካፍ መስራች አገር አንድም ዘመናዊና ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም እንደሌላት ይፋ ማድረጉ የብሄራዊ ውርደት ያህል ነው” ያሉ ወገኖች “ለስታዲየም ግንባታ ገንዘብ አናወጣም” ሲሉ የነበሩት የመለስ ዜናዊ አንዱና ትልቁ ሌጋሲ ተደርጎ ሊወሰደ እንደሚገባው ተቁመዋል።

በግል እሳቸውን የሚያመልኩና ድርጅታቸውን የሚደግፉ በዚህ የውርደት ሌጋሲ ከማፈር ይልቅ ከሴራ ፖለቲካው ጋር ግብ ግብ ገጥመው ላለፉት አንድ ዓመት አገሪቱን እየመሩ ካሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጋር ማገናኘት ” እረኛውን ምታ በጎቹ ይበተናሉ” የሚለው የሴራው ፖለቲካው አንዱ አካል በመሆኑ እንደማያስገርም ነው አስተያየት የሰጡት። አያይዘውም ለማፈር እንኳን የሚያፍር ስነ ልቦና ስለሚያስፈልግ ይህ እንደማይታሰብ አመልክተዋል። የሌጋሲው ውርደት ገና ይቀጥላልም ብለዋል። ለሚያስቡ ግን ሌጋሲው በዘር እያባላ የሚጠጠው ደም ለማፈርና ለመጠየፈ ከበቂ በላይ እንደነበረም ጠቁመዋል። ፋና ይህንን ብሏል።

Related stories   እስራኤል አልጃዚራ ቴሊቪዥን፣ አሶሲየትድ ፕሬስና ሌሎች ሚዲያዎች የሚጠቀሙበትን ህንጻ አወደመች

ሁሉም የኢትዮጵያ ስታዲየሞች የካፍን ዝቅተኛ የጥራት መስፈርት እንደማያሟሉ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።

የካፍ ልኡክ ከጅቡቲ ጋር ለተደረገው የቻን ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ስታዲየሞችን ከገመገመ በኋላ በደረሰበት ድምዳሜ አንድም የሀገሪቱ ስታዲየሞች ካፍ የሚጠይቀውን መስፈርት አያሟላም ብሏል ።

የመቐለ፣ የሃዋሳ፣ የባህርዳር፣ የድሬዳዋ እንዲሁም በግንባታ ላይ የሚገኘው የአዲስ አበባው አደይ አበባና አንጋፋው የአዲስ አበባ ስታድየም ከደረጃ በታች መሆን በደብዳቤው የጠቀሰው ካፍ በተለይ የአዲስ አበባ ስታዲየም ሙሉ እድሳት ካልተደረገለት በምንም ሁኔታ የካፍ ጨዋታዋችን እንደማያስተናግድ አስታውቋል።

ኢትዮጵያ ስታድየሞቿን የማታስተካክል ከሆነ የብሄራዊ ቡድኑን ጨዋታን በሌሎች ሀገራት ለማድረግ እንደምትገደድ አስታውቋል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከካፍ የደረሰውን ደብዳቤ በማስመልከት ለስፖርት ኮሚሽን በጻፈው ደብዳቤ የካፍን መስፈርት ለማሟላት መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ ትኩረትና ክትትል እንዲያደርግ ጠይቋል።

በ27 ቀናት ውስጥ ለ2022 አለም ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ሌሴቶን በሜዳቸው የሚገጥሙት ዋልያዎቹና በ20 ቀናት ውስጥ ለ2020 ቶኪዮ ኦሊምፒክ ማጣሪያ ካሜሩንን የሚያስተናግዱት ሉሲዎቹ ጨዋታ እጣ ፈንታ አልለየለትም።

ካፍ አንድ ቡድን ጨዋታ ከማድረጉ ከ45 ቀን በፊት ሜዳውን ማስገምገም እንዳለበት የሚያስቀምጥ ሲሆን የብሄራዊ ቡድኖቹ ቀጣይ ጨዋታዎች የት እንደሚደረጉ አልታወቀም።ይህ ከተወሰነ በሁዋላ ካፍ ለመቀሌና ባህር ዳር ስታዲየሞች ጊዜያዊ ፈቃድ ሰጥቷል።

የትግራይ እና ባህርዳር ስታዲየሞች የካፍ ውድድሮችን እንዲያካሂዱ ጊዜያዊ ፈቃድ ማግኘታቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡

የትግራይ፣ የሃዋሳ፣ የባህርዳር፣ የድሬዳዋ እንዲሁም በግንባታ ላይ የሚገኘው የአዲስ አበባው አደይ አበባና አንጋፋው የአዲስ አበባ ስታድየም ከደረጃ በታች መሆናቸውን ካፍ ማስታወቁ የሚታወስ ነው፡፡

ይህንንም ተከትሎ ፌዴሬሽኑ መቐለ 70 እንደርታ በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ እና ፋሲል ከነማ በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የሚያደርጓቸውን ጨዋታዎች በትግራይ እና ባህርዳር አለም አቀፍ ስታዲየሞች ማካሄድ እንዲችሉ ጥያቄ አቅርቦ ነበር፡፡

ጥያቄውን የተመለከተው ካፍም ስታድየሞቹ የካፍ ዝቅተኛውን መስፈርት በሁለት ወራት እንዲያሟሉ በማሳሰብ የክለቦቹና የብሄራዊ ቡድኑ የካፍ ውድድሮች በሁለቱ ስታድየሞች እንዲካሄዱ በጊዜያዊነት ፈቅዷል፡፡

ካፍ የትግራይ እና ባህርዳር ስታዲየሞች ከዛሬ ነሃሴ 1 ቀን 2011 እስከ ጥቅምት 1 ቀን 2012 ያሉ ጊዜያትን ነው የፈቀደው፡፡ በእነዚህ ሁለት ወራት ስታድየሞቹ ያላሟሏቸውን ግብዓቶች እንዲያሟሉ እና የሌላ ስታድየም ግምገማ እንዲካሄድ ፌዴሬሽኑ እንዲጠይቅ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል፡፡

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0