ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ብሄራዊ የኢንቨስትመንት እና የስራ እድል ፈጠራ መሪ ኮሚቴን ስራ አስጀመሩ። የብሄራዊ ኮሚቴው መቋቋም ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የክልል ርእሳነ መስተዳድሮች እና ሚኒስትሮች በተገኙበት ይፋ ሆኗል። በዓመት እስከ ሶስት ሚሊዮን ዜጎች ስራ ያገኛሉ።

በዚህ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዘላቂ እና አስተማማኝ የስራ እድል ለመፍጠር ኢትዮጵያ የግሉ ዘርፍ ያለውን አቅም አሟጣ መጠቀም እንዳለባት ነው ያመለከቱት።

በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራው ይህ ብሄራዊ ኮሚቴ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርን ጨምሮ የዘጠኝ ክልሎች ርእሳነ መስዳድርች፣ የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ከንቲባዎች፣ ሁለት የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ተወካዮች እና 10 የፌደራል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችን ያካተተ ነው።

ኮሚቴው የፖሊሲ እና ተቋማዊ ስርዓትን በአንድ ላይ በማዋሃድ ዘላቂ የስራ አድል መፍጠረን ለማረጋገጥ ይሰራል ተብሏል። ኢንቨስትመንትን በመጨመር የስራ አድል እንዲፈጠር ለኢንቨስትመንት መስፋፋትም ግንባር ቀደም ሚና እንደሚጫወትም መገለፁን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

በዚህም ሂደት ለኢንቨስትመንት አመቺ ሁኔታ እንዲፈጠርም የፌደራል እና የክልል መንግስታት እንዲሁም ባለ ድርሻ አካላት እንዲሰሩ የማስተባበር ሚና አለው ነው የተባለው። እንደ ፅህፈት ቤቱ መረጃ በየዓመቱ ከ2 እስከ 3 ሚሊየን የሚጠጉ ወጣቶች ስራ ፈላጊውን የእድሜ ክልል ይቀላቀላሉ።

የሀገሪቱ ምጣኔ ሀብት ወደፊት እየተራመደ ቢሆንም፥ ይህንን ስራ ፈላጊ ቁጥር የሚመጥን የስራ አድል ግን ለመፍጠር ተጨማሪ ስራ እንደሚጠይቅ ነው የተመለከተው።

ቢዝነስን በቀላሉ ለማከናወን የሚያስችል ምህዳር ለመፍጠር የተቋቋመው ሌላኛው ኮሚቴ የግሉ ዘርፍ የስራ እድል በመፍጠሩ ረገድ ቁልፍ ሚና እንዲጫወት የሚያደርግ ምቹ ምህዳር በማምጣት ጠቃሚ አስተዋፅኦ እያበረከተ መምጣቱ ተገልጿል።

እነዚህ ሁለቱ ኮሚቴዎች በቅንጅት በመስራትም እስከ 2012 በጀት ዓመት ማብቂያ ድረስ በግብርና፣ ማዕድን፣ ቱሪዝምና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች 3 ሚሊየን የስራ እድል ይፈጥራሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው።

 (ኤፍ ቢ ሲ) 

Related stories   ሽፈራው ሽጉጤ መጡ - ተወዳዳሪዎቹ ተለዩ፤ የኦህዴድና ብአዴን ክንድ አብዛኛው የሸንጎው ይዞ ኢህአዴግን መለየት ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *