በዘመነ ኢህአዴግ የፀደቀ የኢትዮጵያ ህገመንግስት የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች የስልጣን ባለቤት እንደሆኑ ይገልፃል።ይህ አገላለጽ በቀጥታ ሲታይ ጥሩ አገላለጽ ይመሰላል።ሆኖምየኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች የኢትዮጵያ ዜጐች ለመሆናቸው የህገመንግስት እውቅና ዋስትና የለም።በዚሀ ሁኔታ ሲታይ የኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል እንጂ አገር የላቸውም።አለፍሲልም የብሔር ክልላዊ መጠሪያ እንጂ የዜግነት መጠሪያ አገር የላቸውም።

በኢትዮጵያ የስልጣን ባለቤት የኢትዮጵያ ዜጎች መሆን ሲገባ አገር እና ዜግነት አልባየብሔር ፖለቲካ መከተል ተራማጅ ሀሳብ አልነበረም።ሁሉም ለማለት በሚያስችል መልኩ የብሔር አቀንቃኝ በመሆን በአገር እና በዜጐች ላይ ከፍተኛ የአስተሳሰብ ውድቀት አስከትሏል።ብሔሬ እንጂ አገሬ የሚል ዜጋ ቁጥር ተመናምኖሰንብቷል።በመሆኑም ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ፣እናፖለቲካዊ ችግሮች ከመቀነስ ይልቅ እየተባባሱ መጥቷል።

ዜጎች በአገራቸው ተረጋግቶና ሰርቶ እንዳይኖሩ የብሔር አሰተሳሰብ መሠረታዊ ችግር ሆኖ ቆይቷል። የኢህአዴግ ሥርአት ከኢትዮጵያ ዜጎች ይልቅ ለውጭ አለም ገፅታ ብዙ ይጨነቅ ነበር ።የአለም አቀፍ ስብሰባ አዲስ አበባ በሚሆንበት ወቅት ማደሪያ ቤት የሌላቸው ዜጎች እንዲሁም በሴተኛ አዳሪ የሚሰሩ ሴቶች ከያሉበት እየታፈሱ የትም ቦታ ይጣሉ ነበር ። ይህ ለዜጎች ያለመቆርቆር ከማሳየቱም በላይ በሐሰት ድህነት እንደቀነሰ ለማሳየት ይሰራ የነበረ የሞኞች ተግባር ነበር ።የዜጎች መሠረታዊ ፍላጎት በአግባቡ ተጠንቶ መፍትሔ ከማበጀት ይልቅ ይበልጥ ለባሰ ችግር እንዲዳረጉ ማድረግ ከአንድ አገር የሚያስተዳድር የፖለቲካ ሥርአት የማይጠብቅ ጉድለት ነበር ። ዜጋ የሚረሳ ሥርአት ልማታዊ ሥርአት ሊሆን የሚችልበት አሳማኝ ምክንያት አይኖረውም ።

በዜግነት የተበተነ ዜጋ አንድ ማህበረ-ኢኮኖሚ ማህበረሰብ መፍጠር አይደለም ለማሰብ ያስቸግራል።በብሔር አሰተሳሰብ የተበተ ነህዝብ በምን የፖለቲካ ስልት ናጥበብ አንድየኢኮኖሚ ማህበረሰብ ማድረግ ይቻላል? ።የኢህአዴግአብዮታዊ ሰርአት አገራዊ መሠረት እና ቅርጽ አልባ በመኖሩ በቀላሉ በራሱ ውስጣዊ የአመለካከት ለውጥ ባላቸው ካድሬዎች እንዲሁም በሰፊው ህዝብ የለውጥ ጥያቄ መሠረት ሊዳከም ችሏል ። የኢህአዴግ ሥርአት ለኢትዮጵያ ለዜጐችየደህንነት ስጋት ሆኖ ዘልቋል ።የማይቋረጥ የዜጎች ውስጣዊ መፈናቀል ፣ ህገ -መንግሰታዊ የዜጎች ሰብዓዊ ጥሰት ፣ ያለፍርድ ትዕዛዝ ዜጎች ለእስር መዳረግ ፣ የዲሞክራሲ መርሆዎች ያለማክበር ፣ ያለአግባብ በስልጣን መበልጸግ ፣ ህገ ወጥ የዜጎች ስደት ፣ ስርአቱ የሚቃወሙ ዜጎች በሽብርተኝነት መፈረጅ የኢትዮጵያ ህዝብ በኢህአዴግ ሥርአት ላይ እምነት እንዲያጣ አብይ ምክንያት ሆነዋል ። በዚህ የተነሳ የኢህአዴግ መንግስት ህዝብ እና አገር በህግና ሥርአት ከማስተዳደር ይልቅ ህዝብ እየተማፀነ እንዲገዛ የመርህ ለውጥ አድርጎ ነበር ። የኢህአዴግሥርአት ገና በጥዋቱ የዲሞክራሲ እና የዜግነት ጥያቄዎች ፈተና ያላለፈ ስለነበር የኢትዮጵያ ህዝብ በሐይል እንጂ በህግ ልዕልና ሆነ በዲሞክራሲ አገር ሆነ ህዝብ ሲያሰተዳድር አልነበረም ።

የኢህአዴግ ሰርአት በደርግ ስርአት ላይ ጥላቻና ብቀላ ላይ ያተኮረ ስለነበር የአገር ሆነ የዲሞክራሲ ግንባታ ለማሳካት እምነት እና አቅም አንሶት ቆይቷል። ከዚያም በላይ ለኢትዮጵያ ዜጎች ደንታቢስ የነበረ ስርአት ነው ። ከሽግግር መንግስት ጀምሮ በዲሞክራሲ እጦት ክፉኛ የተጎዳ ይህ ሥርአት ዲሞክራሲ አራማጅ ሙህራን ዜጎች ሲያብጠለጥል እንዲሁም ሲያስር የነበረ ነው ። የኦሮሞ ነፃ አውጪ ድርጅት ጨምሮ በርካታ ከዲሞክራሲያዊ ሐይሎች ከዲሞክራሲያዊ መድረክ እንዲቀነሱ ተደርጎ ነበር ። ሆኖም ሁኔታው ዘላቂ አገራዊ መግባባት ማምጣት አልቻለም ። ዜጎች በጠላትነት የሚፈርጅ ሥርአትየዜጎች ደህንነት ሆነ ዘላቂ እድገት ለማሳካት የሚታሰብ አይሆንም። የኢህአዴግ ሥርአትግለሰብ ተኮር ጥቃት ይፈፅም የነበረ የበሰበሰ ሥርአት ነው ።ሥርአቱ መረን የለቀቀ ስለነበር መሪናተመሪ በአግባቡ ተለይቶ የማይታወቅበት ሥርአት ነበር ። በመሆኑም አሰሪና ፍርድ ሰጪ መለየት አይቻልም ነበር ። Collective Leadership was a factor to prompt social injustice in Ethiopia under the EPRDF ruling era. የኢህአዴግ ሥርአት ጥላቻ አራማጅ ስለነበር አገራዊ መግባባት መፈጠር ተስኖት ዘልቋል ። ለአብነት ያህል የደርግ መዋቅር ሙሉ በሙሉ እንዲፈርስ ተደርጓል ። ያ ድርጊት ታሪካዊ ስህተት ነበር ። ተቋማት ማሻሻል ሲቻል ማፍረስ ለምን ያስፈልግ ነበር ?።

የኢትዮጵያ ዜጎች በሐይማኖት እና ብሔር ተካፋፍሎ ለሐያ ሰባት አመታት ያህል እንዲያዘግሙ የኢህአዴግ ሥርአት ምክንያት ነበር ። የኢትዮጵያ ዜጎች ሊቢያ በረሐ ላይ በሰላማዊ አማፅያን አንገታቸው ሲቀላ በኢህአዴግ ሰርአት ምክንያት መሆኑ ማንም የሚዘነጋው ጉዳይ አይሆንም ። የአንድ አገር የእድገት መጀመሪያ የዜጎች መብት እና ደህንነት ማስጠበቅ ሲቻል ነው ። የኢህአዴግ ሰርአት በዜጋው ላይ ያተኮረ የውጭ ፖሊስ አልነበረውም ። በመሆኑም ሥርአቱ ከኢትዮጵያ ዜጎች በተግባር ከተለያየ በርካታ ግዚያት አስቆጥሯል ።የአንድ አገር ዜጎች በሚኖሩበት ቦታ ሆኖ ስለአገራቸው እንዲሁም ህዝባቸውመቆርቆር እና ማሰብ የማይቀር እውነታ ነው ። ነገር ግን የዜግነት ግዴታቸው በአግባቡ እንዲያከናውኑ የመንግሥት ስርአት ለዜጐች የሚያመች ሆኖ መቀረጽ ይኖርበታል ። ከጅምሩ አግላይ እና ከፋፋይ የብሔር ሰርአት ለኢትዮጵያ የሚመጥን አልነበረም ።ዜጎች በዘር የሚከፋፍል ሥርአት የህዝብ ተቀባይነት እንዲያገኝ መደረጉ ታሪካዊ ስህተት ነበር ። ዜጎች በዘር ተካልሎ እንዲኖሩ መፈቀድ በራሱ ለዘር ማጥፋት ወንጀል መነሻ ምክንያት ይሆናል ።በዘር ክፍፍል ምክንያት ጥቃት የዘር ጥቃት ያልደረሰበት ማህበረሰብ የለም ማለት ይቻላል ። በአራቱ የኢትዮጵያ ቦታዎች የሚሰሩ ዜጎች ከማፈናቀል እሰከ ነብስ ግድያ  ጥቃት ደርሶባቸዋል ። በርካቶች ሞቷል ። ሚሊዮኖች ከቦታቸው ተፈናቅሏል ። ሺዎች ለከፋ ድህነት ተዳርጓል ።የዜጎች መፈናቀል ከኢህአዴግ ህግና ሥርአት አልበኝነት የሚመነጭ ነው ። ተፈናቃይ ህዝብ እንጂ አፈናቃይ ማን እንደሆነ በቅጡ አይታወቅም ። ቢታወቅም በድርጅታዊ ግምገማ ሁኔታው ተድበስብሶ ይቀራል ። ግምገማ አንዱ የኢህአዴግ የንቅዘት ማባባሻ መሣሪያ ነበር ።

በኢህአዴግ ሥርአተ  ዘመን የተወለደ ዜጋ ስለአገር አንድነት እና መተሳሰብ በሚያስብበት ወቅት ሥርአቱ የለውጥ መሰመር ከመተለም ይልቅ በአብዮታዊ ፀበል የተባረከ ይመስል በተንኮልና ሴራ ሥርአቱ በፈጠረው ሥርአት አልበኝነት ምክንያት መገዳደልና መጠፋፋት ላይ ነው ። በልዩ ሐይል አማካይነት የኢትዮጵያ ከፍተኛ የጦር ኢታማዦር በአሳዛኝ ሁኔታ እርምጃ ተወስዶበታል ። ጀኔራል ሰአረ መኮነን ላይ የተፈፀመ ግድያ የአማራ ክልል ባለስልጣናት ግድያ ጋር መያያዙ የሚያረጋግጥ ገለልተኛ መረጃ እስከአሁን የለም ። ጉዳዩ በአስቸኳይ በገለልተኛ ወገን እንዲያጣ የኢትዮጵያ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አጣሪ ኮምሽን ማቋቋም ይኖርበታል ።የጄኔራል ሰአረ መኮነን ግድያ የተወሳሰበ እንደሆነ የሚገመት ሆኖ በማን ፣ ለምንና እንዴት እንደተገደለ በገለልተኛ አጣሪ አካል መታወቅ አለበት ። ዜጎች ለፖለቲካ ፍጆታ በከንቱ መገደል የለባቸውም ። የጄኔራል ሰአረ መኮነን ግድያ የፖለቲካ ሴራ ቅንብር እንደሆነ የሚናገሩ ዜጎች ቁጥር በርካታ ነው ።ኢትዮጵያ በፖለቲካ ሥርአት መዛባት ለዜጐች ህለፈተ ሞት ምክንያት የምትሆን አገር መሆን የለባትም ። ሁሉም በአገሩ ተከብሮ እና ሠርቶ የሚየፈኖርበት ምቹ የፖለቲካ ሥርአት መፈጠር አለበት ። ከመገዳደል መከባበር ፣ ከጥላቻ ይልቅ ፍቅርን ፣ ከመጎነታተል ይልቅ መተሳሰብ ፣ ከስሜት ይልቅ ምክንያታዊ መሆን ፣ በዘር ከማሰብ ይልቅ በአገር ስሜት መተሳሰር ለዘላቂ ሰላምና እድገት መሠረት ይሆናል ።የለውጥ ጮራ ሰንጣቂ በመባል የሚጠቀሱ የአማራ ክልላዊ መንግስት ለአራት ወራት የክልሉ ህዝብ እንዲመሩ እድል የነበራቸው ዶክተር አምባቸው መኮነን በሥርአት አልበኞች መገደል ለምን አስፈለገ ?። የጄኔራል ሰአረ መኮነን ሆነ የዶክተር አምባቸው ድንገተኛ ግድያ የፌዴራል መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትር አሰተዳደር ድክመት በመሆኑ ጠቅላይ ሚኒሰትሩ ላይ ከፍተኛ የወንጀል ምርመራ መከናወን ይኖርበታል ። የድርጊቱ እውነታ በገለልተኛ ምርመራ ካልታወቀ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አሰተዳደር ነፃነት የሚሰጥ ጉዳይ አይሆንም ።

በዜግነት ላይ የተመሠረተ ዲሞክራሲያዊ ሥርአት ለዜጐች አንድነት እና መተባበር የመሠረተ ድንጋይ  ሆኖ ያገለግላል ፣ የእኔነት ሰሜት ይቀንሳል ፣ መተሳሰብ ያጎለብታል ፣ የጋራ ችግር የጋራ ለመቋቋም ይረዳል ፣ የኢኮኖሚ ሆነ ማህበራዊ ትስስር ያሳድጋል ፣ የጋራ የሀብት አጠቃቀም የአስተሳሰብ ለውጥ ይፈጥራል ። Peoplestart to utilize National resources fairly as the perception of National feeling becomes unified regardless of their ethnic bond . ማህበረሰብ በፍትሐዊ የሐብት ክፍፍል አይጋጭም ። ለማህበራዊ ግጭት መነሻ ሆነ መድረሻ የፖለቲካ ሥርአት ነው ። በአንድ አገር የሚኖሩ ዜጎች የሚከፋፍል የፖለቲካ ሥርአት በአለም ፖለቲካዊ መርሆ ቢመዘን በምንም መለኪያ ሰላምና መረጋጋት ማስፈን አይቻልም ። ዜጎች የማይወክል የፖለቲካ ሥርአት በዜጎች መካከል መተማመን እንዳይኖር ምክንያት ይሆናል ። ይህ በኢህአዴግ ሥርአት የታየ አንድ ግዙፍ ችግር ነበር ። ምክንያቱም ሥርአቱ ለቡድን (ለብሔር ) መብት እንጂ ለግለሰብ ( ዜጋ)  መብት መከበር ጉዳዩ አልነበረም ። በመሆኑም በርካታ ኢትዮጵያውያን ዜጎች የሰብአዊ መብት ጥሰት ተፈፅሞባቸዋል ። በኢህአዴግ ሥርአት የግል መብት በጥርነፋ(በቡድን) ) እንጂለግልፍትህ የሚሰጥ  የፍትህ አካል እምብዛም አልነበረም ። የኢትዮጵያ ህገ መንግስት የግለሰብ መብት በሚያስከብር መልኩ መሻሻል ይኖርበታል ። የብሔር ሰብሰብ የግለሰቦች ሰብሰብ መሆኑ የግል መብት ሲከበር የሁሉም መብት ይከበራል ። የብሔር መብት መከበር የግለሰብ መብት መከበር ማለት አይደለም ። በመሆኑም ለዜጎች መብትና ፍትህ የሚታገል ሥርአት መመሥረት ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም ።

በኢህአዴግ ሥርአት ቀና መልካም ተግባር የሚፈፅሙ ካድሬዎች አልነበሩም ብሎ መዝጋት ያስቸግራል ። በሐሳብ አፍላቂነት ይታወቁ የነበሩ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒሰትር ክቡር አቶ መለሰ ዜናዊ በርካታ የአገር ልማት ንድፍ እቅዶች ያቀዱ ታላቅ መሪ የነበሩ ሲሆን በዲሞክራሲ ግንባታ እንዲሁም ለአገር ተግባቦት ብዙም የሠሩት አጥጋቢ ሥራ አልነበረም ።በዚህ የተነሳ በምርጫ 97 ማግስት ለመጀመሪያ ጊዜ የመንግስት አስቸኳይ አዋጅ የታወጀው በጠቅላይ ሚኒሰትር መለስ ዜናዊ የስልጣን ዘመን ነበር ።ምርጫ 97 ከሁለት መቶ በላይ ንፁሃን ዜጎች ላይ በመንግስት ፀጥታ ሐይሎች አማካይነት አሳዛኝ እርምጃ ተወስዷል ። በዚህ የተነሳ የኢህአዴግ ሥርአት ለሁለተኛ ጊዜ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ቅሬ ውሰጥ ገባ ። የኢትዮጵያ ህዝብም በኢህአዴግ ሥርአት ላይ የመጨረሻ እምነት አጣ ። የኢህአዴግ ሥርአትም የዜጎች ነፃነት የሚጋፋ አፋኝ ህጎች በማውጣት ዜጎች ላይበስፋት የመብት ጥሰቶች ተፈፅሟል ። በኢህአዴግ ሥርአት የፈፀሙት የመብት ጥሰቶች በገለልተኛ አጣሪ ኮምሽን መጣራት ይኖርባቸዋል ። በዜጎች ላይ በደል የፈፀመ የፖለቲካ ሥርአት በህግ መጠየቅ አለበት ።

በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሥርአት እኔ ካልገዛሁ አገር ይፈርሳል ፣ ህዝብ ይበተናል የሚል ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ አዘል የፖለቲከኞች አሰተያየት መሰማት የተለመደ ቢሆንም አስተያየቱ ግን እርባናየለሽ አሰተያየት ነው ። አገር የአንድ የፖለቲካ ድርጅት አልያም የቡድን ሰብሰብ አልያም የአንድ ግለሰብ ውጤት አይደለም ። የሚፈርስ አገር የሚበታተን ህዝብ የለም ። ለአንድ አገር ህዝብ ከፖለቲካ ባሻገር የሚተሳሰሩበት የማህበራዊ ዘይቤ ግንኙነት አላቸው ። ሐዘንና ደሰታ አንድ የማህበራዊ ግንኙነት አካል ነው ።በ ባህልና ቋንቋ ፣ በጋብቻና ግብይት የቆየ ትስስር ያዳበረ ህዝብ የአንድነት ገመዱ በፖለቲካ ሥርአት መዛባት ፈፅሞ ሊበጠሰ አይችልም ። አገር ይፈርሳል ፣ ህዝብ ይበተናል ለሚሉ የመንደር ፖለቲከኞች ራሳቸው ሲፈርሱና ሲበታተኑ ማየቱ ለምን ተሞክሮ እንደማይሆን በሚገባ የተረዱት አይመስልም ።የፖለቲካ ሥርአት ጭቆና በዜጎች አንድነት ፣ በህግ ልዕልና በጊዜ ሒደት ይፈታል ። ለዜጎች የሚያገለግል የፖለቲካ አሰተዳደር በዜጎች መሠረታዊ ፍላጎት ላይ የተመሠረተ እንጂ በፖለቲካ አሰተዳደር ጭቆና ላይ ያተኮረ አይደለም ። ለዜጎች የማይሆን ሥርአት የዜጎች መሠረታዊ ፍላጎት የሚፃረር ከመሆኑም በላይ የሰላምና ኢኮኖሚ ለውጥ እንቅፋት እንዲሁም የሰበአዊ መብት ጥሰት ምክንያት ይሆናል። የፖለቲካ አምባገነን ሥርአትበወታደራዊ ሐይል እንዲሁም በኢኮኖሚ ሀብት ምዝበራ ላይ የቆመ የውሰን አምባገነን መሪዎች ሰብሰብ ነው ። በመሆኑም የፖለቲካ ሥርአቱ ዘላቂነት የለውም ።

    በኢህአዴግ ሥርአት ዋልታ ረገጥ የብሔር አክራሪነት እንዲሰፋፋ አንዱ ምክንያት ህገ መንግሥቱ ነው ። ዜጎች በብሔር የሚለያይ ህገ መንግስት ገዢ ህገ መንግስት ሊሆን አይችልም ። በኢህአዴግ ሥርአት የፀደቀው የኢትዮጵያ ህገ መንግስት የኢትዮጵያ ዜጎች ህልውና የሚፈታተን ነው ። በመሆኑም በዚህ ህገ መንግስት ኢትዮጵያ ብሔር እንጂ ዜጋ የላትም ። ህገ መንግሰቱ የኢትዮጵያ ዜጎች የሚል መግቢያ ሐረግ ሆነ ሐተታ የለውም ። በመሆኑም የኢትዮጵያ ህዝቦች ዜግነታቸውበአሁኑ የኢትዮጵያ ህገ መንግስት በውል አይታወቅም ። የኢትዮጵያዊነት እሴት በኢህአዴግ አገዛዝ ሥርአት ምክንያት አደጋ ላ ወድቆ ቆይቷል። ክልሌ እንጂ አገሬ የሚል ዜጋ እየቀነሰ መጥቷል ። ይህ የተሳሳተ አመለካከት ለዜጐች መፈናቀልና ሞት ምክንያት ሆኗል ። የኢትዮጵያ ዜጎች በአገራቸው በሰላም እንዳይኖርበኢህአዴግ ሥርአት ተነፍጓል ። በኢህአዴግ ሥርአት ኢትዮጵያ ለዜጎቿ ባዕድ አገር ሆና ቆይቷለች። በአንድ አገር እየኖሩ በብሔር መከፋፈል የፖለቲካ ብስለት ሳይሆን ውድቀት አመላካች ነው ። የአንድ ማህበረሰብ ማንነት በፖለቲካ አመለካከትና አገዛዝ የሚወስን ሳይሆን የማህበረሰቡ ብቸኛ ንብረቱ ነው ። ማንም አይነፍገውም ማንም አይወስደውም ። የብሔር ማንነት የፖለቲካ ሥርአት አጀንዳ አይደለም ። የማንነት ፖለቲካ ( Identity politics ) የፖለቲካ ሥርአት ጤናማ አመለካከትና አሰተሳሰብ አይደለም ። የብሔር ሥርአት የፖለቲካ ነጋዴዎች ጥሬ ውንብድና ከመሆን ያለፈ አይደለም ። የብሔር ፖለቲካ ለማስቀረት የህገ መንግስት ማሻሻያ ማድረግ አስፈላጊነቱ የላቀ ነው ። ብሔር ላይ ያተኮረ ፖለቲካ እጅግ ሲበዛ ሗላ ቀር አሰተሳሰብ ነው ። የኢኮኖሚ ሆነ የማህበራዊ ለውጥ አያመጣም ። የኢህአዴግ ሥርአት በታኝ አይሏቸው ተንታኝ አክራሪ የብሔር ፖለቲከኞች ያፈራ ዘረኛ ሥርአት ነው ።

የኢህአዴግ ሥርአት ከዜጎች ጭቆና ባላነሰ ራሱ እየጨቆነ እንዲሁም ራሱ እያጠፋ(self suicide ) ይገኛል ። ሥርአቱ የኢትዮጵያ ዜጎች የጠየቁት ለውጥ ለማሳካት መፍጨርጨር ቢታይበትም የጠራ የለውጥ መሥመር ድህነት ላይ ነው ። ለውጥ ከየት ወደየት እንደሆነ ለመገንዘብ ያዳግታል ። አሁን የኢህአዴግ ሥርአት የነጠረ የለውጥ ሀሳብ የለውም ። በመሆኑም የኢኮኖሚ ማሽቆልቆል እየታየ ነው ። የሥራ አጥር ቁጥር ከመቀነስ ይልቅ እየናረ ይገኛል ። አሁንም ዜጎች በህገ ወጥ እየታሰሩ ነው ። የፖለቲካ መተማመን በሴራ እየተጠቃ ነው ። ከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎች ሳይቀር ግድያ እየተፈጸመባቸው ይገኛል ። የኢህአዴግ ሥርአት አባል ድርጅቶች የመጠቃቃት ፣ የመበቃቀል ፣ እንዲሁም የመገዳደል ፖለቲካ ቅኝት ውስጥ ገብቷል ።ከዚህ ሁኔታ የሚወጡት የመውጫ ሀሳብ የላቸውም ። አሁን ተያይዞ መቀመቅ መግባት ይሆናል ። የኢህአዴግ አንዱ አባል ድርጅት በሌላ አባል ድርጅት የህልውና ጥቃት እየደረሰበት በመንኮታኮት ላይ ነው ። የቆየ የድርጅት ሚስጥር ጭምር በገሀድ እያወጣ ይገኛል ። የኢህአዴግ ሥርአት በዚህ ሁኔታ ይፈርሳል ብሎ የጠበቀ ጥቂት ቢሆን ነው ። የኢህአዴግ ሥርአት ለለውጥ ሁሌም ዝግጁ አልነበረም ። ይህ ሥርአት ከለውጥ ይልቅ የሀይል እርምጃ ያበዛ ነበር ። ተደጋጋሚ መልካም የመሥራት እድሎች ሳይጠቀምባቸው ቀርቷል ። የኢህአዴግ ሥርአት ከምስጋና ይልቅ የህዝብ ውግዘት የተቻረው ሥርአት ሆኗል ።የኢህአዴግ ሥርአት የህግ በላይነት የጣሰ ፣ የዜጎች ሰብአዊ መብት የረገጠ ፣ የዜጎች ነፃነት ያፈነ ፣ የአገር ሀብት ምዝበራ ያሰፋፋ ሥርአት ነበር ።

   ሁለቱ የኢህአዴግ አዋራ አጋር ድርጅት የነበሩ ማለትም የአማራ ዲሞክራሲያዊ ፖርቲ እና ሕ.ወ.ሓ.ት ላይሰማሙ በአላማ ተለያይቷል። ሆኖም ከመዘላለፍ በፖለቲካ የሀሳብ ብቃት መወያየት ሲቻል አንዱ ንፁህ ሌላው ታታሪና ሐቀኛ የህዝብ አገልጋይ አድርጎ ማየቱ ተገቢ አይደለም ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ አሰተሳሰብ ክስረት ጭምር ነው ። መቀሌ የመሸገው ማን ነው? ባህርዳር የመሸገውሰ ማን ነው? ። መቀሌ ያለው ዘራፊ ባህርዳር ያለው ንፁህ ያደረገው ማን ነው ? ። መቀሌ ያለው ሲዘርፍ ባህርዳር ያለው የት ነበር ? ። መቀሌ ያለው ሰብአዊ መብት ሲጥስ ባህርዳር ያለው ምን ያድርግ ነበር ? ። ይህ ማይ (ውሃ )ከማይቋጥር የመንደር ፖለቲካ በፍጥነት መላቀቅ ያሰፈልጋል ። የፖለቲካ ጥላቻ ማህበረሰብ ዘንድ ይደርሳል ። በመሆኑም የትግራይ ክልል የፖለቲካ መሪዎች ከአማራ ክልል አመራር ጋር ብስለት የታከለበት እውነተኛ የፖለቲካ ውይይት ማካሄድ ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም ። ፋይዳ ከሌለው የቂም ፖለቲካ በሽታ መላቀቅ ያሰፈልጋል ። ከሐይል እርምጃ ውይይት  ይቅደም ። መወነጃጀል የፖለቲካ ምጥቀት አሰተሳሰብ ምልክት አይደለም ። በኢትዮጵያ በዘመነ ኢህአዴግ ለተፈፀሙት ወንጀል ነክ ጉዳዮች ሁለም የኢህአዴግ አባልና አጋር ድርጅቶች ከህግ ተጠያቂነት ውጭ አይሆኑም ።የፖለቲካ ድርጅት ራሱ በዳይ ራሱ ፈራጅ ሊሆን የሚችልበት የመርህ አሰራር አለም ላይ የለም ። የጥፋት ፍርዱ ለህግ ልዕልና መተው ለሁሉም ጠቃሚ ነው ።በሌለ ጉዳይ ላይ ደግሞ ጊዜ ማቃጠል አያስፈልግም ። የህዝብ መገናኛ መንገድ የሚዘጋ የክልል አሰተዳደር ኢትዮጵያዊ ለመሆኑ በበኩሌ እጠራጠራለሁ ።በኢትዮጵያ ምድር በጋራ ተስማምቶና ተከባብሮ የመሬት ግዛት በሐይል አስመልሳለሁ የሚል የክልል አሰተዳደር የጤናው ሁኔታ ያሰጋል ። በኢትዮጵያ የአማራ መሬት ፣ የትግራይ መሬት ፣ የኦሮሞ መሬት ወዘተረፈ የሚባል ጉዳይ የለም ። የሚሻለው በሁሉም ቦታዎች በጋራ መኖር ብቻ ነው ። በሒደት የሚሆነውም ያ ነው ።

   ኢህአዴግ ከአብዮታዊ አሰተሳሰብ መላቀቅ ያልቻለው የለውጥ ሀሳብ አፍላቂ ካድሬዎች በሀሳብ ጤዛ መሸፈናቸው ሊሆን እንደሚችል እገምታለሁ ። የኢህአዴግ አጋር ድርጅቶች አካትቶ ተራማጅ ለመሆን የፖለቲካ አመራር ብቃት ይጠይቃል ። ተግባራዊ ውህደት መፈጠር አልተቻለም ። ያልሆነበት ምክንያትም ግልጽ አይደለም ። ለውጥ ማለት ሕ.ወ.ሓ.ት ማውገዝ አይመስለኝም ። በእኔ አረዳድ ሕ.ወ.ሓ.ት በመርህ ደረጃ የለውጥ አደናቃፊ አልያም ተቃዋሚ አይመስለኝም ። ሕ.ወ.ሓ.ት ከለውጥ ሜዳ ማስወጣት ግን የፖለቲካ ኪሳራ እንጂ ትርፍ አያስገኝም ።ይህ ስል ግን  ሕ.ወ.ሓ.ት ለዜጐች ዲሞክራሲያዊ መብትና ጥቅም የሚታገል የፀዳ የፖለቲካ ድርጅት ነው ማለቴ እንዳልሆነ ግንዛቤ እንዲወሰድ እፈልጋለሁ ። ሕ.ወ.ሓ.ት ከዲሞክራሲ መርህ ጋር የተጣላ የነቀዘ ድርጅት ነው ። ሆኖም ንቅዘቱ በኢትዮጵያ የጎላ የፖለቲካ ተሳትፎ ከማድረግ የሚያግደው በቂ እናአሳማኝአመክንዮ እስከአሁን የለም ።ሕ.ወ.ሓ.ት የለውጥ አካል ማደረጉ ብሰለታዊ የፖለቲካ አካሔድ ይመስለኛል ። ምክንያቱም ሕ.ወ.ሓ.ት ራሱ ያልተቻለ በህዝብ ትከሻ ሥር ያለወ እና የአቋም ለውጥ ያላደረገ ለዘብተኛ የፖለቲካ ድርጅት ነው ። ዜጋ ተኮር የልማትና የዲሞክራሲ ግንባታ የህ.ወ.ሓ.ት. አሰተዋጽኦ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል የሚል የፀና አመለካከት አለኝ ።

      የኢህአዴግ ሥርአት በህገ መንግስት መሠረት ለሚቀርቡ የክልል እንሁን ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት ሲቸገር ማየት ከማሳዘን ያለፈ ጉዳይ ነው ። የሲዳማ ሆነ የወላይታ ማህበረሰብ የክልል እንሁን የመብት ጥያቄ ማቅረባቸው እንዴት አገር የሚበትን ጥያቄ ተደርጎ ይፈረጃል ?። ዜጎች ለሚያነሱት ህገ መንግሰታዊ የመብት ጥያቄ መንግስት ጉዳይ አስፈፃሚ እንጂ እንቅፋት መሆን የለበትም ። መንግስት ህግ ማስፈፀም እንጂ ህግ አውጪ መሆን አይችልም ። በመሆኑም የሲዳማ ሆነ የሌሎች ማህበረሰብ ጥያቄዎች በህገ መንግሥቱ አዋጅ መሠረት እንዲከናወን መፍቀዱ ለአገር ደህንነትና ግንባታ ይጠቅማል እንጂ አይጎዳም ። የሲዳማ ህዝብ ክልል የመሆን የመብት ጠያቄ በማቅረቡ ኢትዮጵያዊነቱን ካደ ማለት አይመስለኝም ። የህዝብ ጥያቄዎች በሚገባ አጥንቶና መርምሮ አፋጣኝ መልሰ የማይጥስ የፖለቲካ ሥርአት ቤተመንግሥት ገብቶ ምን ይበጃል ? ። የፖለቲካ ሥርአት ለዜጎች ካልጠቀመ ምን ፋይዳ ይኖረዋል ?። በህገ መንግሰቱ መሠረት አንድ ህዝብ ክልል አይደለም ከኢትዮጵያ ልገንጠል ቢልም በፀጋ ማስተናገድ ህገመንግስታዊ ግዴታ ነው ። በመሆኑም የሲዳማ ህዝብ የክልል ጥያቄ ህጋዊ ጥያቄ ነው ። ክልል የመሆን ጥያቄ የፌደራሊዝም አንዱ የተግባር ምልከታ ነው ። በመሆኑም በበጎ ጎን መታየትና መተንተን አለበት ።የኢህአዴግ ሥርአት በቀላሉ ለችግሮች የቀረበ ሥርአት ነው ። ለዚህ ምክንያት ደግሞ በቡድን እንጂ በህግ ልዕልና ውሳኔዎች የሚወሰን የፖለቲካ ድርጅት አይደለም ። ይህ ችግር ለድርጅቱ ድክመት አንዱና ፈታኝ ችግር ሆኖ ዘልቋል ። በኢህአዴግ ሥርአት የህግ ልዕልና ከካድሬዎች በታች ነው ።

ልኡልገብረመድህን (ከአሜሪካ ) aiga forum

  ፍትህ ያለፍርድ ለታሰሩ የኢትዮጵያ ዜጎች !

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *