ስትራቴጂው ዘርፉን በእቅድ እና በሰርአት እንዲመራ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው በዛሬው እለት በተሰጠ ዛሬ በተሰው መግለጫ ተመልክቷል።

የንግድና ኢንዱሰትሪ ሚንስትር ድኤታው አቶ ተካ ገብረየሱስ፥ ስትራቴጂው መሬት ላይ ያሉ ችግሮችን በሚለይ እና ቀጣይ እርምጃዎቸን ለመውሰድ በሚያስችል ሁኔታ ለቀጣይ አምሰት አመታት የሚያገለግል ሆኖ መዘጋጀቱን ገልፀዋል።

የመንግስት ተቋማትን ጨምሮ በርካታ የልማት አጋሮች የተሳተፉበት ብሄራዊው የስራ ፈጠራው እስትራቴጂው በአለም አቀፍ እስታንዳርድ ደረጃ እንደተሰራ ተገልጿል።

ስትራቴጂው ተግባራዊ ሲደረግም ለኢኮኖሚው እና ለልማቱ ከሚኖረው ከፍተኛ አበርክቶ ባሻገር መሬት አውርዶ ለመተግበርም ከስፋቱ እና ከሚኖሩት በርካታ ተዋንያኖች አንጻር ተግበራዊነቱ ብዙ ፈተናዎች ሊኖሩት ይችላል ተብሏል።

ስለዚህም ይላሉ ሚንስትር ድኤታው አቶ ተካ ገብረየሱስ፥ ሁሉም ባለድርሻ አከላት በተግባራዊነቱ ላይ ንቁ ተሳትፎ ሊኖራቸው ይገባል።

በአጠቃላይ ከከፍተኛ ትምህት ተቋማት የሚወጣውን ጨምሮ በየአመቱ 2 ነጥብ 3 ሚሊየን አዳዲስ ለስራ የደረሱ ስራ ፈላጊ ዜጎቸን የምታመነጨው ኢትዮጵያ የስራ አጥነቱን ችግር ለመፍታት የስራ ፈጠራን እንደ አንድ አመራጭ የያዘች እንደመሆኗ አዲሱ የስራ ፈጠራ እስትራቴጂ ውጤታማ የደርጋል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል። ስትራቴጂው ከተያዘው የዘንድሮ በጀት ዓመት ጀምሮ ተግበራዊ መሆን እንደሚጀምም ለማወቅ ተችሏል።

በትእግስት አብረሃም

FBC

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *