ለውጡ እውን ከሆነ ማግስት ጀምሮ የሚሰማው የገንዘብ ማሸሽ ዜና በኢትዮጵያ የተለመደ ጉዳይ አይደለም። በኦሮሚያ ክልል አቶ ለማ መገርሳ በሰጡት ትዕዛዝ በየቀኑ ገንዝብ ይያዝ ነበር። የገቢዎች ሚኒስቴር ቅርጹን ቀይሮ መስራት ከጀመረ ወዲህ ይፋ እንደሚነገረው በየቀኑ የሚያዘው ኮንትሮባንድና ለማሸሽ ሲሞክረ የሚያዘው የገንዘብ ብዛት ከጉዳዩ ጀርባ እነማን አሉበት የሚለውን ጥያቄ ካስነሳ ሰንባብቷል።

ቀደም ሲል በአውሮፕላን ጣቢያና በኬላዎች ባለ ትሥሥር የሚካሄደው ኮንትሮባንድና የብር ዝውውር ከልካይ ስላልነበረው ከአገሪቱ የሚሸሸውን ሃብት የምንስማው በዓለም አቀፍ ተቋማት ሪፖርትና ዜና ነበር። ተዘርፎ እንደወጣ የሚነገረው የውጭ ምንዛሬ ብዛት ከገንዘብ ተቋማት ጋር ቀጥተና ግንኙነት ያላቸው  ተዓማኒ አካላት በመሆናቸው አገሪቱ መንግስት ነበራት ወይ እስከሚባል ዜጎችን ያንገብገበ ጉዳይ ሆኖ ቆይቷል። ይሁን እንጂ ዛሬ ላይ የተዘረፈውን ለማስመለስ ከሚደረግ ሩጫ በተጨማሪ በአገር ውስጥ ተያዘ የሚባለው ገንዘብና ኮንትሮባንድ ቀላል ቁጥር የሚገልጸው አይደለም።

Related stories   ደመቀ መኮንን በፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሚመራ የአውሮፓ ህብረት ልዑክ ጋር ተወያዩ

አገሪቱ ካለባት የውጭ ምንዛሬ አንጻር፣ ለመድሃኒትና ለቀን ተቀን ወጪ እንደልብ ለመሆን ካዝና በነጠፈበት ወቅት በጥቁር ገበያ አገሪቱ ላይ ያለውን የውጭ ምንዛሬ እየለቀሙ ወደ ውጭ ለማጓጓዝ የሚታትሩት ክፍሎች እነማን ናቸው የሚለው ጥያቄ ከየአቅጣጫው የሚነሳ ነው። የፍርድ ሂደቱን የሚከታተሉም በወጉ ይፋ አያደርጉትምና ነገሩ ምንድን ነው? የሚያሰኝ ሆኗል።

በኩንታል፣ በውሃ ታንከር፣ በመኪና ውስጠ ክፍል፣ በጎማ ከመነዳሪ ውስጥ፣ በእህል ውስጥ እንዲሁም በምግብ ዘይት ጀሪካንና በመሳሰሉት ቦታዎች እየታጨቀ ሲጓጓዝ ተያዘ የሚባለው ሃብት ማብቂያውስ መቼ ይሆን? የሚከተሉት ሁለት ዜናዎች በአንድ ቀን የተሰሙ ናቸው።

በጀሪካን ውስጥ በመደበቅ ከሀገር ለማስወጣት የተሞከረ ገንዘብ ተያዘ። በህገወጥ መንገድ ከሀገር ሊወጣ የነበረ የ2 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያለው የሦስት ሀገራት ገንዘብ ተያዘ።

በህገወጥ መንገድ ከሀገር ሊወጣ የነበረና ዛሬ ነሐሴ 10/2011 በዋለው የምንዛሬ ተመን የ2 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያለው 11 ሺህ 900 ድርሀም፣ 76 ሺህ 230 የአሜሪካን ዶላር እና 66 ሺህ 900 የሳውዲ ሪያል ዛሬ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

የብር ኖቶቹን ከሀገር ለማስወጣት የተሞከረው በባለአምስት ሊትር ጀሪካን ውስጥ በመደበቅ ነው ብሏል የገቢዎች ሚኒስቴር። የተያዘውም በቶጎጫሌ ሚሊሻና የጉምሩክ አባላት የተቀናጀ ጥረት እንደሆነ ታውቋል፡፡ ኅብረሰተቡ ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርን ለማስቆም ከዳር እስከ ዳር እንዲረባረብም የገቢዎች ሚኒስቴር ጥሪ አቅርቧል፡፡

Image may contain: 1 personNo photo description available.
ፎቶ አመብ- ከገቢዎችና ጉምሩክ መረጃ ገጽ የተወሰደ መሆኑ የተጠቀሰና እግዚቢት ሲያዝ የተነሳ

በሌላ ተመሳሳይ ዜና  ሁለት ተሽከርካሪን ጨምሮ ከ4 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ የተለያዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡መነሻው ኬንያ እንደሆነ የተገመተ 3 ሚሊዮን 251 ሺህ 800 ብር የሚያወጣ የብር ጌጣጌጥ ሞያሌ የመቆጣጠሪያ ጣቢያ ነሐሴ 8 ቀን 2011 ዓ.ም በፍተሻ እንደተያዘ የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የብር ጌጣጌጡ መጠኑ 65 ነጥብ 3 ኪ.ግ እንደሆነ የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡ የኮንትሮባንድ ዕቃው በተሽከርካሪ ወደ መሀል ሀገር በመጓጓዝ ላይ እያለ በቁጥጥር መዋሉ ነው የተገለጸው፡፡ በኮንትሮባንድ ድርጊቱ የተጠረጠረ አንድ ግለሰብም ተይዞ ምርመራ እየተደረገበት መሆኑ ታውቋል፡፡

ሲልቨር.png

ከነሐሴ 06-09/2011ዓ.ም በተለያዩ ኬላዎችና የመቆጣጠሪያ ጣቢያዎች የተለያዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዛቸውና ከእነዚህም ውስጥ ዋጋዉ 1ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የሚገመት ፓስታ አወበሬ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ላይ መያዙ ተመላክቷል፡፡ በሀሰተኛ የሰሌዳ ቁጥር ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ኮድ 3- 03068ድሬ ሃይሉክስ ተሽከርካሪ እና በቱሪስት መልክ በመተማ በኩል የገባ ኮድ2-07207 ኦሮ ተሽክርካሪዎች ጅግጅጋ እና በአዳማ ከተማ መያዛቸውም ተሰምቷል፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን ኅብረተሰቡ እያደረገ ያለውን አስተዋፅኦ እያድንቀው በቀጣይም ተሳትፎው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

አመብ – የተወሰደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *