“Our true nationality is mankind.”H.G.

በኦሮሚያ የጃዋር ተቀባይነት እየተሸረሸረ ነው፤ መረራ አቋማቸውን ግልጽ እንዲያደርጉ ግፊት አለ!!

የጊንጪው ልጅ ሽመልስ አብዲ የኦሮሚያ ክልል መሪ ከሆኑ በሁዋላ ጃዋር መሐመድ በኦሮሚያ መካከለኛው ክፍል ያለው ተቀባይነት መቀነሱን የአምቦ ነዋሪ የሆኑ ፖለቲከኞች ለዛጎል ገለጹ። አንጋፋው የትግል ሰው ፕሮፌሰር መረራ አቋማቸውን ግልጽ ሊያደርጉ እንደሚገባም በተለያዩ ወገኖች እየተጠየቁ መሆናቸውም ታውቋል።

ብሕዝብ ብዛት፣ በተማረ ሰው ሃይል፣ በኦሮሞ ትግል ጀማሪነት፣ አብዛናውን የኦሮሚያን ወረዳዎችና ቁልፍ የገቢ አውታሮች የያዘው የመካከለኛው ኦሮሚያ ወይም እምብርት ኦሮሞዎች በኔትዎርክ በሚያደርጉት ግንኙነት አማካይነት የጃዋር ተሰሚነት ሊቀንስ እንደቻለ ነው ሰዎቹ የተናገሩት።

በስፋት የኦሮሚኛ ሚዲያዎችን የመጠቀም እድል እንዳላገኙ የሚናገሩት እነዚሁ የኔትወርኩ አባላት፣ ጃዋር መሀመድ ላይ ከዚሁ ከሚዲያ አሰራርና አካሄድ የተነሳ ቅሬታቸው እያየለ መምጣቱንም አስረድተዋል። በዋናነት ግን ጉዳዩ ከዛም በላይ እንደሆነ ጠቁመዋል።

Related stories   ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ማጣራቱ ሱዳን የተሰደዱ ዜጎችን እንደሚያካትት አስታወቀ፤ መንግስትና አማራ ክልል በማይካድራ ጉዳይ ተኝተዋል

የአባ ነጋ እና የገላሳ ዲልቦ ሁለት የኦነግ ክንፎች መዋሃዳቸውን ተከትሎ በትውልድ ጥቁር ኢንጪኒ እንደሆነ የሚነገርለት የቄሮ መሪ  የጥምረቱ ምክትል ሊቀመንበር ሆኖ መመረጡ አንዱ ማሳያ እንደሆነ የኔትዎርኩ አባል ይናገራሉ።

አብሮ በመኖር የሚያምኑትና በኢትዮጵያ ጉዳይ ከሌላው ህዝብ የተለየ አቋም የሌላቸው ቱለማዎች የሚያደርጉት እንቅስቃሴ የዚሁ አካል ይሁን አይሁን ያላብራሩት የኔትወርኩ አባል፣ የኦሮሚያ ክልል በሚኒሶታ ሊከፍተው ያሰበው ሚዲያ መድረክ ያጡትን ወገኖች በማሳተፍ  የተላዘበ አማራጭ ሃሳብ እንዲያቀርቡ ያስችላቸዋል የሚል እምነት እንዳላቸው ተናግረዋል።

ካሁን በሁዋላ የኦሮሮሞ ልጆች ለጥይትና ለሁከት፣ እንዲሁም ለአድማና ክልላቸውን ለሚከፋፍል የጠበበ አመለካከት ሊኖራቸው እንደማይገባ፣ ልማትና እድገት ላይ እንደሚሰሩ፣ አብሮ ከተዋለዳቸው የአማራም ሆነ የሌሎች ህዝብረተሰብ ክፍሎች ጋር በሰላም መኖር ለጥያቄ የማይቀርብ ጉዳይ መሆኑ ከስምምነት ላይ መደረሱን ያመለቱት የኔትወርኩ ተገልጋይ፣ መላው የኢትዮጵያ ህዝብም ይህንኑ በመረዳት ድጋፍ እንደሚሰጥ ያምናሉ።

Related stories   አገርን የከዱ ተደመሰሱ፤ የሳተላይት መገናኛና መድሃኒት " ጁንታው" እጅ ሳይገባ ተያዘ

ከየአቅጣጫው ጽንፍ የወጣ አስተሳሰብ የሚያራምዱ ወገኖች ወደ ጥፋት ያመሩናል። አይጠቅሙንም። የሚል ግንዛቤ የተያዘበት የኔትወርክ የጎንዮሽ አደረጃጀት ካሁን በሁዋላ በስሜት የሚነዱ ወገኖች እንደማይኖሩ በቅርቡ ማረጋገጫ ይሰጣል። መጪው ምርጫ በሰላማዊ መንገድ እንዲከናወንም ድጋፍ ያደርጋል።

ተወዳጁ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ከዳውድ ኢብሳ ኦነግ ሸኔ ጋር ለመስራት መፈራረማቸው እያደር ጥያቄ እያስነሳና በድርጅታቸውም የወጣቶች ክንፍ ውስጥ መነጋገሪያ የሆነ አጀንዳ መሆኑንን የሚጠቁሙት የኔትወርኩ አባል፣ በሶስት የተከፈለው ኦነግ ሸኔና መረራ ተመሳሳይ ቅርጽ ስለሌላቸው አሰላለፋቸውን ከወዲሁ ሊያስተካከሉ ይገባል የሚል እምነት በሰፊው እንደሚሰማ አልሸሸጉም።

Related stories   ወደ ድርደር ? ከታንክ ወደ አህያ የወረደው ትህንግ በማን ሊወከል?

” ጦር አንስቶ የራሱን ህዝብ የሚወጋ፣ በውጪ አገር ሆኖ ለዚሁ እልቂት በጀት የሚቆርጥ፣ አዲስ አበባ ሆኖ በሰላማዊ መንገድ እታገላለሁ የሚለው ባለ ሶስት መልኩ ኦነግ ሸኔና መረር ሊያገናኛቸው የሚችል ጉዳይ የለም። ሊኖርም አይችልም” የሚሉ የጉደርና የአምቦ አካባቢ ነዋሪዎች መረራን በግልጽ ለማነጋገር እቅድ እንዳላቸው ለማወቅ ተችሏል።

ጃዋር የኦሮሚያ ክልል ሚዲያ እንደሚያቋቁም መሰማቱን ተከትሎ ሚኖሲታ የተመለሰ ሲሆን ወደፊት ምን አስተያየት እንደሚኖረው ከወዲሁ በጉጉት የሚጠበቅ ሆኗል። እንደቀድሞውስ የውጩን ሳያካትት “ከአገር ቤት”ከፍተኛ የገንዘብ ማሰባሰብ ይችል ይሆን የሚለው ጥያቄም አብሮ የሚታይ ይሆናል።

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0