አራት የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ከግል ኮሌጆች ጋር በትብብር የማስተርስ ድግሪ መርሃ ግብር እንዳይሰጡ ማገዱን የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

እገዳው የተጣለባቸው የጅማ ዩኒቨርሲቲ ABH ከሰተኘ ተቋም ጋር፣ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከዮም ኮሌጅ ጋር፣ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከናሽናል ኮሌጅና ሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ ከአዲስ ኮንቲነንታል የጤና ኢንስቲትዩት ጋር በትበብር ሲሰጡ በነበረው መርሀ ግብር ነው፡፡

ኤጀንሲው እርምጃውን የወሰደው የመንግሰት ዩኒቨርሲቲዎች ከግል ኮሌጆች ጋር በትብብር እንዲያስተምሩ የሚፈቅድ አሰራር አለመኖሩን ተከትሎ መሆኑን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አንዷለም አድማሴ ለኢቲቪ ተናግረዋል፡፡

እነዚህ ዩኒቨርሲቲዎችና የግል ኮሌጆች ከ2006 ጀምሮ የማስተርስ መርሃ ግብር በትብበር እንዳያስተምሩ ከሚመለከተው አካል ደብዳቤ ቢጻፍላቸውም አለመታዘዛቸውን ዶር. አንዷለም ገልጸዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲና ኮሌጆቹ እስካሁን ያስመረቋቸውንና በማስተማር ላይ ያሉትን ተማሪዎቻቸውን ዝርዝር በአስቸኳይ ለከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ እንዲያቀርቡም ተጠይቀዋል፡፡

ከዚህ በኋላ ምንም ዓይነት የተማሪ ምዝገባና ቅበላ እንዳያካሂዱም ደብዳቤ እንደተጻፈላቸው ኤጀንሲው አስተውቋል፡፡

እስካሁን በተቋማቱ አገልግሎት ያገኙ የነበሩ ተማሪዎችን በተመለከተ አግባብነት ካላቸው የመንግስት ተቋማት ውሳኔ እየተጠበቀ እንደሆነም ነው የተገለፀው፡፡

የትኛውም የመንግስትም ዩኒቨርሲቲ ሆነ የግል የትምህርት ተቋም አስፈላጊውን የፈቃድ መስፈርት እስካላሟሉ ድረስ የርቀት ትምህርት እንኳን ቢሆን መስጠት እንደማይችሉም ተመልክቷል፡፡

በተመሳሳይም የግል ኮሌጆችና የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በአዲስ አበባ ከሚገኙ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ጋር ተቀናጅተው የሚሰጡት የማታ ትምህርት መርሃ ግብርም ህገ ወጥ መሆኑን ኤጀንሲው አመልክቷል፡፡

ትምህርቱን በትብብር እየሰጡ ያሉ ተቋማት የተሟላ የትምህርት ቤተ ሙከራና መሰል ግብዓቶች ሳይኖሩ እንደሚያስተምሩም ኤጀንሲው ማረጋገጡን ገልጿል፡፡

ከውጭ አገራት የትምህርት ተቋማት ጋር የሚሰጡ የትብብር የትምህርት አሰጣጥ በሚመለከትም የተቀመጠውን መስፈርት ያሟሉ ብቻ እንደሚሰጡ ገልጸዋል፡፡

አማራ ክልል መገናኛ

Related stories   The Forces of Evil Arrayed Against Ethiopia ( (Part I of II)-By almariam

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *