ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሱዳን ተቃዋሚዎችና ወታደራዊ ሃይል በመሰረቱት የሽግግር መንግስት ዙሪያ የመጨረሻ የስምምነት ፈርማ ስነ ስርዓት አጠናቀው ሲመለሱ ነው ኢትዮጵያዊያኑን  አዲስ አበባ የገቡት፡፡

105 ኢትዮጵያኑ በተለያዩ ምክንያቶች በሱዳን እስር ቤቶች የነበሩ መሆናቸው ተነግሯል፡፡ ከእስር ተፈተው አዲስ አበባ ከገቡት መካከል በርካታዎቹ ሴቶች  መሆናቸው ነው የተገለፀው፡፡

በዛሬው ዕለት በተካሄደው የፊርማ ስነ ስርዓት በአዳራሹም ሆነ በጎዳናዎች የነበሩ ሱዳናዊያን ለኢትዮጵያና ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ምስጋና ሲያቀርቡ ነበር፡፡

የሱዳን የፓለቲካ ሀይሎች በደረሱት በስምምነቱ መሰረት የልዑላዊ ምክር ቤት የሚቋቋም ሲሆን ምክር ቤቱ ስድስት የሲቪል እና አምስት ወታዳዊ አመራሮችን በአባልነት ያካታል፡፡

የልዑላዊ ምክር ቤቱን ሁለቱ ወገኖች በየሶስት ዓመት እየተፈራረቁ የሚመሩት ሲሆን በዚህ መሰረት ለቀጣይ ሶስት ዓመታት የነፃነትና የለውጥ ሀይል ጠቅላይ ሚኒስትሩን የሚሾም ይሆናል፡፡

በዚህ ስምምነት ላይ ደግሞ ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትሯ በኩል ከፍተኛ ሚና እንደነበራት የገለፀ ሲሆን ለዚህም ሱዳናዊያኑ ምስጋና አቅርበዋል::

በምስክር ስናፍቅ FBC

Related stories   የባህር ዳር ነዋሪዎች " አደራጁን አካቢያችንን እንጥብቅ፤ ኮሽ የሚል ነገር አይሰማም" አሉ፤

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *