የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር እስከ ነሃሴ ወር መጨረሻ 4 ሚሊየን ኩንታል ስንዴ ወደ ሀገር ውስጥ እንደሚገባ የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የገንዘብ ሚኒስቴር የ 2011 በጀት አመት አፈፃፀሙን አስመልክቶ የሚኒስቴሩ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሀጅ ኢብሳ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸው የዋጋ ንረቱ እየጨመረ መምጣቱን የገለፁ ሲሆን የዋጋ ንረቱ በሰኔ ወር ላይ ምግብ ነክ 19 ነጥብ 6 እና ምግብ ነክ ያልሆኑት 10 ነጥብ 2 በመቶ ላይ ያሳያል ብለዋል፡፡ በአጠቃላይ በሰኔ ወር ላይ የዋጋ ግሽበቱ 15 ነጥብ 4 በመቶ ሆኖ መመዝገቡን አስታውቀዋል፡፡

Related stories   "ኢትዮጵያን የውስጥና የውጭ ጠላቶች ግንባር ፈጥረው ሊያጠፏት የተነሱበት ወቅት ላይ እንገኛለን፤ ሁሉም አንድ መሆን ይገባዋል – የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም

ዳይሬክተሩ በሀምሌ ወር ደግሞ የዋጋ ንረቱ በ0 ነጥብ 5 ከፍ ማለቱን የጠቆሙ ሲሆን ንረቱ ከፍ ካለባቸው ምርቶች ደግሞ 70 ከመቶ ያህሉ ስንዴ እና ተመሳሳይ ምርቶች መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡ ዘይት እና ስኳር ላይም የዋጋ ግሽበቱ የታየ መሆኑን ያነሱት ሀላፊው ከስንዴ አንፃር ሲታይ 30 ከመቶ ያህሉን የያዙ መሆናቸውን ነው የተናገሩት።

በአጠቃላይ ለዋጋ ንረቱ በሀገሪቱ ተከስተው የነበሩ አለመረጋጋቶች እና ምርታማነት ላይ ያሉ ክፍተቶች እንደ ምክንያት ተነስተዋል፡፡ አሁን ላይ በተለይም ስንዴ ላይ ያለውን የዋጋ ንረት ለመቀነስ የሚያስችሉ ሰራዎች እየተከወኑ ነው ብለዋል።

Related stories   የደህንነትና ፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል አገር ለማተራመስ በህቡዕ የተደራጁ በርካታ ግለሰቦችን ከነመዋቅራቸውና መስሪያዎቻቸው በቁጥጥር ስር አዋለ፤

በዚህም እስከ ነሃሴ ወር መጨረሻ ድረስ 4 ሚሊየን ኩንታል ሰንዴ ወደ ሀገር ወስጥ ይገባል ያሉት አቶ ሀጅ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታሉ ጅቡቲ እንደሚገኝም ተናገርዋል። በየወሩም 650 ሺህ ኩንታል ሰንዴ ለህብረተሰቡ እንዲደስ እየተሰራ ይገኛልም ብለዋል፡፡

ስንዴን ከውጭ እያስገቡ ከመደጎም ባለፈ በቀጣይ በጀት አመት መስኖ ላይ ትኩረት ለማድረግ እና ምርታመነትን ለመጨመር እየተሰራ እንደሆነም ገልፀዋል። ከስንዴ በተጨማሪ ሌሎች መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች ላይም መንግስት እየሰራ መሆኑን አቶ ሀጅ አንስተዋል።

Related stories   "የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለጀግኖች አርበኞች ነፃ ህክምና እንዲሰጥ ወሰነ

በተለይም ስኳር እና ዘይት ላይም ያሉትን የዋጋ ጭማሪዎች ሊያስቀሩ የሚችሉ ጥናቶች መጀመራቸውን እና በቅርቡም ይፋ አንደሚደረጉም ነው የተናገሩት። በቀጣይ አመትም የዋጋ ግሽበቱን በ 9 ነጥብ 6 በመቶ ለመቆጣጠርም እቅድ ተይዟል።

በዙፋን ካሳሁን

FBC

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *