የመተማ አካባቢ ወጣቶች በጥርጥር ያስቆሟቸውና መንገድ በመዝጋት እንዳያልፉ የከለከሏቸው አምስት ከባድ ተሽከርካሪዎች ጉዳይ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል። አምስት ሎቤድ ከፈተኛ የጭነት ተሽከርካሪዎች ሙሉ በሙሉ የጦር መሳሪያ ጭነው  ወደ መተማ ሲያቀኑ የአካባቢው የመከላከያ መኮንን፣ የክልሉ ጸጥታ፣ እንዲሁም በተለያዩ ደረጃ ያሉ ሃላፊዎች እውቀቱ እንደሌላቸው መሰማቱ ዜናውን አጉኖታል።

ከመከላከያ የሎጅስቲክስ ቋት እንደወጣ የተነገረለት ጥይት በአካባቢው ወጣቶች ዘንድ ጤናማ አለመሆኑ የተገመተው የተሽከርካሪዎቹ ሰሌዳ ሆን ተብሎ እንዳይታይ ግራሶና ጭቃ መቀባቱ እንደሆነ ቃላቸውን ለቪኦኤ የሰጡ ሃላፊ ተናግረዋል።

ሃላፊው እንዳሉት የአካባቢው ወጣቶች መንገድ ዘግተው ያስቆሟቸው ተሽከርካሪዎች በትክክል የጫኑትን ለማን እንደሚያስረክቡ ባይገለጽም በመተማ በኩል ድንበር ሊያሻግሩዋቸው እንደነበር ተረጋግጧል።

በአሁን ሰዓት የመከላከያ ሰራዊት፣ የክልሉ ልዩ ሃይልና ሚሊሺያዎች በሚገባ ጥበቃ እያደረጉና አግባብ ካላቸው ክፍሎች ጋር የማጣራት ስራ እየተሰራ እንደሆነ ነው የተገለጸው። ዝርዝሩን ከስር ያድምጡ

Related stories   ተጠርጣሪ ወንጀለኞች እንዳይያዙ ከለላ የሚሰጡ ክልሎች አሉ፤ ምክር ቤቱ አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድ አሳሰበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *