የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ  ከኳታር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሼክ መሐመድ ቢን አብዱልራሕማን ቢን ጃሲም አል ታኒ ጋር በጽህፈት ቢታቸው የፊት ለፊት ንግግር ማድረጋቸው ተገለጸ። በሆቴል፣ ስኳር ፋብሪካ፣ በቱሪዝም ልማትና በዘመናዊ ሆስፒታል ግንባታ የመሳተፍ እቅድ እንዳላቸው ተሰምቷል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው ሁለቱ የኳታር ከፍተኛ ባለስልጣናት አዲስ አበባ የመጡት ዶክተር አብይ በመጋቢት ወር በኳታር ይፋዊ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ተጀመሮ የነበረውን  ” ቁልፍ” የተባለ የሁለትዮሽ ትብብር አፈጻጸሞችና ተግባራት ላይ ለመነጋገርና ወደ ስምምነት ለመቃረብ ነው።

ሼክ መሐመድ ከዚህ ቀደም ስምምነት ላይ የተደረሰባቸው የኢንቨስትመንት ዘርፎችን የማስጀመር ዝግጁነት እንዳላቸው ያስታወቁ ሲሆን በዚህም መነሻ በሆቴል፣ ስኳር ፋብሪካ፣ በቱሪዝም ልማትና አዳዲስ የኩላሊት ሕክምና ማዕከላት ግንባታን የማስጀመር ዝግጁነት መኖሩን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ሚኒስትሩን ጠቅሶ ዜና አሰራጭቷል።

በሌላ ዜና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከሳዑዲ አረቢያው አልጋወራሽ ሞሃመድ ቢን ሳልማን ቢን አብዱላዚዝ ጋር በስልክ ተወያዩ።

በውይይታቸውም የሳዑዲ አረቢያው አልጋወራሽ ሞሃመድ ቢን ሳልማን ቢን አብዱላዚዝ ኢትዮጵያ የሱዳን የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደሰላም እንዲመጡ የነበራትን ሚና አድንቀዋል።

ኢትዮጵያ ለቀጠናው ሰላም እና መረጋጋት እያከናወነወች ያለውን ተግባር ሳኡዲ አረቢያ እንደምትደግፍም መናገራቸውን የሳዑዲ ፕሬስ ኤጀንሲ ዘግቧል።

የሱዳን ተቃዋሚዎችና ወታደራዊ ሃይል ስልጣን መጋራት የሚያስችላቸውን የመጨረሻ ስምምነት ባሳለፍነው ቅዳሜ መፈራረማቸው ይታወሳል።

የፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይም ጠቅላይ ዶክተር አብይ አህመድን ጨምሮ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፊኪ መሃመት እና የሌሎች ሀገራት መሪዎች በተገኙበት መካሄዱም ይታወሳል።

የሱዳን ተቀናቃኝ ኃይሎች ሉዓላዊ ምክር ቤት መመስረት መቻላቸውን ተከትሎ በርካታ ሱዳናውያን ለዶክተር ዐቢይ አህመድ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በካርቱም በተካሄደው የፊርማ ስነ ስርዓት ላይ የታደሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ወደ ሀጋራቸው ሲመለበሱም ከሱዳን እስር ቤቶ ከተለቀቁ በኋላ በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተጠልለው የቆዩ 105 ኢትዮጵያውያንን ይዘው መመለሳቸውን የመንግስት መገናኛዎች በትናንትናው እለት መዘገባቸው አይዘነጋም።

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ዶክተር አብራሃም በላይ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳድር ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሾሙ!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *