ZAGGOLE – ዛጎል

“Our true nationality is mankind.”H.G.

የኢትዮጵያ ጉዳይ ያሳሰባት ዩናይትድ ስቴትስን ሙሉ በሙሉ አለሁ እያለች ነው፤ የሴራ ፖለቲካው ጣጣ ወደ አሸባሪዎች ዛቻ ከፍ አለ!!

“አሜሪካ ከመቼውም ጊዜ ይልቅ አሁን በከፍተኛ ስጋት ላይ ነች። በዚህም የተነሳ ሙሉ ድጋፍ ለመስጠት ስምምነት ፈጽማለች” የሚሉት  ለዲሲ ዲፕሎማቶች ቅርብ የሆኑ የዘወትር የዛጎል አስተያት ሰጪ ሕዝብና ፖለቲከኞች በጥንቃቄ ሊራመዱ እንደሚገባ ያመለክታሉ። በሶማሌ የሚንቀሳቀሰው የሽብር ቡድን ያሰራጨው ማስጠንቀቂያም አሁን አገሪቱ በምትገኝበት ሁኔታ መነሻ መሆኑ አገር ወዳድ ለሆኑ ሁሉ የማስጠንቀቂያ ደወል ነው።

ኢትዮጵያና አሜሪካ የተፈራረሙት የሕግ ማስከበርና የወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ስምምነት የሰላም ሚኒስቴር ይፋ ካደረገ በሁዋላ ሁለቱ አገራት አሸባሪዎችን የመለየትና መረጃን የመለዋወጥ ሥምምንት መፈረማቸውን ተቀማጭነቱ አዲስ አበባ የሆነው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

በኢትዮጵያ የተጀመረውን ለውጥ ተከትሎ አኩራፊው ሃይል በበጀትና በሎጂስቲክ ድጋፍ የሚመራው አገሪቱን የማተራመስ እቅድ አሜሪካን ክፉኛ እንዳሳሰባት ከዲሲ ዲፕሎማቶችና ፖለቲከኞች ጋር ባላቸው ግንኙነቶች ሁሉ እንደሚሰሙ የሚናገሩት የዛጎል አስተያየት ሰጪ ” ስምምነቶቹ አሜሪካ ግልጽ ድጋፍ ማድረግ እንዲያስችላት የሚያደርግ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ብዙ ዝርዝር መናገር ባይቻልም ትልቅ መልዕክት ያስተላለፈ ነው” ብለዋል።

ከዚህ ቀደም እንደሆነው ሌሎች አካባቢዎችን ለማተራመስ የሚወጠነውን ውጥን ለመከላከል ዩናይትድ ስቴትስ ድጋፍ ለመስጠት የሕግ ማስከበርና የወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ስምምነት መፈጸሟን ያወሱት አስተያየት ስጪ፣” በየክልሉ አክራሪ ብሄረተኞች ወደ ስልጣን እንዲመጡ ለማድረግ በከፍተኛ ደረጃ እንቀስቃሴ እየተደረገ መሆኑንን መረጃ አለ” ብለዋል።

Related stories   አውሮፓ ህብረት - ላለፉት 28 ዓመታት በኢትዮያ ተላላኪ መንግስት እንደነበር ለኢትዮጵያ ህዝብ አመነ

ከራሷ ብሄራዊ ጥቅም አንጻር ድጋፍ ለማድረግ መወሰኗ የሚታወቅ ቢሆንም፣ ዛሬ ላይ ዩናይትድ ስቴትስ መንግስት እንዳለው ” ቁልፍ”  ድጋፍ ለመስጠት መወሰኗ አግባብ ተደርጎ እንደሚወሰድም ነው የገለጹት። አያይዘውም የነጮቹን ያህል ባይሆንም ሕዝብና ፖለቲከኞች አገሪቱ ያለችበትን አስጊ ሁኔታ በወጉ ሊረዱት እንደሚገባም ጠቁመዋል። ይህ ካልሆነና በመንጋ አስተሳሰብ የሚቀጠል ከሆነ በሴራውና በሴረኞቹ ቡድኖች ምኞት መሰረት አገሪቱ ወደማያባራ ቀውስ እንደምታመራ ግልጽ መሆኑን ጠቁመዋል።

ጉዳዩ እንዲህ አሳሳቢ ሆኖ ሰሞኑንን ትግራይ ተቀምጦ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ የሚያራምደው

Daniel Berhane

የሶማሊያው የአይሲስ (ኢስላሚክ ስቴት) አሸባሪ ቡድን ኢትዮጲያን ኢላማ አድርጓል የሚል ወሬ መጥቷል። በሌላ በኩል ኤርትራ ወታደራዊ ዝግጅት ጀምራለች የሚል ወሬ መጥቷል።  እቺ እንግዲህ ከ4 ኪሎ የመጣች የእድሜ ማራዘሚያ ወሬ ነች። አለበለዚያ ኢሳያስም ፎርማጆም “የወዳጅ ሀገራት መሪዎች” ሆነው እንዴት ይሄ ይከሰታል? የማይመስል ነገር ለሚስትህ አትንገር አለ ሰውየው። ኢሳያስ ለወታደሮቹ የሚከፍለው አጥቶ ነጋ ጠባ ሳውዲና አረብ ኤሚሬትስን እየጨቀጨቀ ያለ ሰው ነው።

ሲል መንግስት ሆን ብሎና ፈጥሮ ያናፈሰው ዜና እንደሆነ አድርጎ ሊስል ሞክሯል። የዓለም መገናኛዎች የአሸባሪውን መሪ መልዕክት በቪዲዮ አስደግፈው በስፋት እያሰራጩት ሳለ አቶ ዳንኤልና ተከታዮቹ ጉዳዩን አሳንሰው የፈጠራ ወሬ እንደሆነ ለማስመሰል የፈለጉበት ምክንያት ብዙም ግራ እንደማያጋባ በርካቶች ከአስተያየቱ ግርጌ አስተያየታቸውን ስጥተዋል።

Related stories   አየር ሃይል " ትዕግስትም ልክ አለው" ሲል ለሱዳን ምክረ ሃሳብ ሰጠ

የአሜሪካ የፌደራል ምርመራ ቢሮ ረዳት፣ እንዲሁም የዩናይትድ ስቴትስ አሸባሪዎችን አጣርቶ የመለየት ማዕከል ዋና ሥራ አስኪያጅ ቻርልስ ኤች ኬብልና የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሥለላና የደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ደመላሽ ገብረሚካኤል ሁለቱ አገራት በቅርቡ አሸባሪዎችን ለይቶ የማጣራት መረጃን የመለዋወጥ ሥምምነት መፈረማቸውን አዲስ አባበ ያለው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ባወጣው መግለጫ ማስታወቁን ቪኦኤ ዘግቧል። ስምምነቱን የፈረሙት ሁለቱም ከፍተኛ ባለስልጣናት ናቸው። ሥምምነቱ ሁለቱ ሀገሮች የአሸባሪነትን ተግባር ለመከላከል ያላቸውን ብቃት ለማጠናከር ሲሉ መረጃ ለመለዋወጥ የሚችሉበትን አሰራር የሚቀይሱበት ነው። በሌላ አነጋገር ከአሸባሪው ቡድን ጋር ግንኙነት ያላቸውን ሃይሎች ለመለያት በስለላ ተቋማቸው አማካይነት ህብረት ፈጥረው ይሰራሉ። ይህ ይፋ የሆነው ደግሞ የሽብር ቡድኑ ማሰጠንቀቂያ ከሰጠ በሁዋላ ነው።

ሶማሊያ የሚገኘው የእሥላማዊ መንግሥት ክንፍ ኢትዮጵያ ውስጥ ጀሌዎችን ለመመልመል የሚያስችሉትን በአማርኛ በድምፅና በቪድዮ የተቀረፁ ጂሃዳዊ የቅስቀሳ ውጤቶችና ፅሁፎችን ሊያወጣና ሊያሠራጭ እንደሆነ አመልክቷል።

እሥላማዊ መንግሥት ቡድን ለአዲሱ ዘመቻው ኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየው የጎሣና የፖለቲካ አለመረጋጋት አመቺ ሁኔታ እንደፈጠረለት ኬንያ ውስጥ የሚገኘው የሳሃን ምርምር ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ማት ብራይደን ከአሜሪካ ድምፅ የሶማሊኛ አገልግሎት ባልደረባ ሃሩን ማሩፍ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ አስታውቀዋል።

ሶማልያ ያለው “እስላማዊ መንግሥት ነኝ” የሚለው ቡድን በአማርኛ የጂሐዳዊ ጽሑፎች እንደሚያወጣ ገልጿል። ኢትዮጵያ ላይ ያነጣጠረ ምልመላ የማካሄድ ዓላማ እንዳለው ያመለክታል ተብሏል።

Related stories   በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ከተሞች የሽብር ጥቃት ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የሽብር ቡድን በቁጥጥር ስር ዋለ- ትህነግ “ክብሪት” የተባለ ገዳይ ቡድን ማቋቋሙ ታወቀ፣

ይህ ማስታወቅያ ባለፈው ወር በሦስት ደቂቃ ቪድዮ መልክ የተለቀቀው በፅንፈኛው ቡድን ደጋፊ ድረ-ገፆች ላይ ሲሆን ኦፊሴላዊው እስላማዊ መንግሥት ነኝ የሚለው ቡድን ሚድያ ደግፎታል። ቪድዮው የአማርኛ ቃላትን ተጠቅሟል፣ ተጨማሪ ጽሑፎችን በአማርኛ እንደሚያወጣም ተናግሯል ተብሏል።

ማት በረየደን የተባሉ ኬንያ ባለው የሳሃን ጥናትና ምርምር ተቋም የሚሰሩ ተንታኝ እስላማዊ መንግሥት ነኝ የሚለው ቡድን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ያለመረጋጋት ሁኔታን ተጠቅሞ ሙስሊም ማኅበረሰብን የመስበክ ዓላማ አለው ብለው እንደሚያምኑ ገልፀዋል።

አያይዘውም ተንታኙ ጽንፈኛው ቡድን ኢትዮጵያ ውስጥ ዕድል እንዳለው ይታየዋል የሚል አመለካከት እንዳላቸው ጠቁመዋል። እስካሁን ባለው ጊዜ በአብዛኞቹ የአፍሪካ ሀገሮች ብዙም ባይሳካለትም አፍሪካ ውስጥ ተቀባይነት ለማግኘትና እንቅስቃሴውን ለማስፋት ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል ይላሉ ብራይደን።

የሽብር ቡድኑ ኢትዮጵያ በመተራመስ ላይ ያለች አገር መሆኗን ተንተርሶ ወደ አዲሱ እቀዱ ከመጣ፣ አካሄዱ የቀውሱ የተጠና አካሄድ አመላካች እንደሆነ ያሳያል። በሶማሌ የመሸገው አሸባሪን የመደምሰሱ ጉዳይ ላይ በአሜሪካና በህወሃት መካከል ልዩነት ተፈጥሮ እስከመጋጨት እንዳደረሳቸው ጎልጉል ህወሃት በሚያኮርፍባቸው የሶማሊያ ‹አሸባሪ› ድርጅቶች ይጠረጠራል” በሚል ርዕስ በስፋት ዘግቦ ነበር።