የቀድሞው የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሳን አልበሽር ከሳዑዲ ዓረቢያ በሚሊየን የሚቀጠር ዶላር መቀበላቸውን አምነዋል። በህገ ወጥ የውጭ ምንዛሬ፣ በሙስና እና የተለያዩ ስጦታዎችን ያለ አግባብ በመቀበል ክስ የተመሰረተባቸው የቀድሞ የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር በትናንትናው ዕለት ፍርድ ቤት ቀርበዋል ።

በህዝባዊ አመፅ ከስልጣናቸው የተወገዱት የ75 ዓመቱ አልበሽር ነጭ ባህላዊ ልባሳቸውን ለብሰው በፍርድ ቤቱ የእስረኛ ክፍል ላይ በመገኘት የፍርድ ሂደታቸውን ተከታትለዋል።

ፍርድ ቤቱ በዋለው ችሎትም የቀድሞ የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሳን አልበሽር ከሳዑዲ ዓረቢያ በሚሊየን የሚቆጠር ገንዘብ እንደተቀበሉ ማመናቸውን መርማሪ ፖሊስ አስታውቋል።

በዚህ መሰረትም አልበሽር 90 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ከሳዑዲ ልዑል ብርጋዴር ጀነራል አህመድ አሊ እጅ በጥሬ ገንዘብ መቀበላቸው ተገልጿል።

ከዚህ ባለፈም በመኖሪያ ቤታቸው በተደረገ ፍተሻ 7 ሚሊየን የሚጠጋ ዩሮ፣ የተወሰኑ የአሜሪካ ዶላሮችና የሱዳን ፓውንዶች የተገኙባቸው መሆኑ በዘገባው ተመላክቷል።

እነዚህ ገንዘቦችም የሳዑዲው ዓልጋ ወረሽ ሞሃመድ ቢን ሳልማን በስጦታ መልኩ ካበረከቱላቸው 25 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ውስጥ የሚካተቱ መሆኑ ተጠቁሟል።

በተጨማሪም ኦማር ሀሰን አልበሽር በ2015 ህይወታቸው ካለፉት ከከቀድሞው የሳዑዲ ንጉስ አብደላህ 65 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር መቀባለቸውን መርማሪ ፖሊስ አስታውቋል።

የአልበሽር ጠበቃ አህመድ ኢብራሂም  በበኩላቸው  መርማሪ ፖሊስ በደንበኛቸው ላይ ያቀረበውን ክስ የሚያረጋግጥ ምንም አይነት መረጃም ሆነ ማስረጃ የሌለው መሆኑን ተናግረዋል።

ምንጭ ፦አልጀዚራ – FBC

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   Ethiopia’s transition misrepresented. Reply to Obang Metho

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *