የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በኢትዮጵያ ከእንግሊዝ አምባሳደር አላስተር ማክፊል ጋር ተወያይተዋል። አምባሳደሩ እንግሊዝ ከአማራ ክልል ጋር ከዚህ በፊት በጀመረቻቸው እና በአዳዲስ የልማት እቅዶች በትብብር ለመሥራት ፍላጎት እንዳላት ተናግረዋል።

አምባሳደር አላስተር ማክፊል ከዚህ በፊት በንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፣ በዘመናዊ የመሬት አያያዝ እና በኢንቨስትመንት አማራጮች ዙሪያ ከክልሉ ጋር በትብብር ለመሥራት መሞከራቸውንም ነው የተናገሩት።

በመገናኛ ብዙኃን ነፃነት ላይ ለመስራት እና ጋዜጠኞችን በስልጠና ለማብቃት ማቀዳቸውንም የእንግሊዙ አምባሳደር አስታውቀዋል።

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በኢትዮጵያ ከአሜሪካ አምባሳደር ማይክ ራይነር እና ከእንግሊዝ አምባሳደር አላስተር ማክፊል ጋር በቀጣይ የትብብር ተግባራት ዙሪያ መምከራቸውን አስታውቀዋል።

ከሀገራቱ ጋር በፀጥታ መዋቅር እና በፍትህ ስርዓት ማሻሻያ፣ በፖሊሲ ምርመር እና ስልጠና ዘርፎች በጋራ ለመሥራት መወያየታቸውንም አቶ ተመስገን ገልጸዋል።

በኢንቨስትመንት አማራጮች ላይም የየሀገራቱን ባለሃብቶች ለመሳብ እና አደጋ ላይ ያሉ ቅርሶችን ለመታደግ በትብብር ለመሥራት መወያየታቸውን ከአማራ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

 ዩኒሴፍ ከአማራ ክልል ህዝቦች ጋር የሚሠራቸውን ልዩ ልዩ ትብብሮች አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አስታወቀ

በኢትዮጵያ የዩኒሴፍ ተወካይ አዲል ሆደር እና የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በቀጣይ የትብብር መስኮች ዙሪያ በትናንትናው ዕለት በባሕር ዳር ተወያይተዋል።

ዩኒሴፍ በኢትዮጵያ ለ 67 ዓመታት ሕፃናት ላይ ትኩረት አድርጎ ሠርቷል ያሉት፥ አዲል ሆደር በአማራ ክልል በአማካይ ዕድሜ 16 ዓመት የሆነውን ያለዕድሜ ጋብቻ ለማስቀረት አሁንም በትኩረት ለመሥራት ከርዕሰ መስተዳደሩ ጋር መምከራቸውን ተናግረዋል።

ባለፉት ዓመታት በጤና ተቋማት የሚወለዱ ሁሉም ሕፃናት የልደት ካርድ እንዲኖራቸው፣ የንፁሕ መጠጥ ውሃ አቅርቦት እንዲሻሻል ለማድረግ እና በትምህርት ተቋማት ድጋፍ የሠሯቸው ተግባራት ውጤታማ እንደነበሩ አስታውቀዋል።

በቀጣይ በክልሉ በሕፃናት እንክብካቤ፣ በትምህርት ቁሳቁስ እና ግንባታ ድጋፍ፣ በአመጋገብ፣ በንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፣ ያለዕድሜ ጋብቻን በማስቀረት እና በበጎ አድራጎት ሥራዎች ለመሳተፍ መምከራቸውንም ተናግረዋል።

ርዕሰ መስተዳድር ተመስገን ጥሩነህ በበኩላቸው በትምህርት ቅበላ ችግር ያለባቸው አከባቢዎች ላይ ትኩረት ለማድረግ፣ በንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት እና በጤና ዘርፍ በትብብር ለመሥራት ከተወካይዋ ጋር መግባባታቸውን ተናግረዋል።

የሕዝቡ ጥያቄ ሆነው የክልሉ በጀት መሸፈን ባልቻላቸው የልማት ሥራዎች ላይ ዩኒሴፍ ትኩረት አድርጎ እንዲሠራ መምከራቸውንም ነው ርዕሰ መስተዳድሩ የገለፁት።

ከዚባለፈም የአቅም ግንባታ ሥራዎች ላይ እንዲሳተፉ እና በዩኒሴፍ የተጀመሩ ግንባታዎችን በወቅታቸው እንዲያጠናቅቁ መምክራቸውን አብመድ ዘግቧል።

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   ብርሃኑ ነጋ አቋማቸውን ቀየሩ፤ ኢዜማ ደርግ በግፍ የዘረፈውን የግል ሃብት ለተከራይ እንደሚሸጥ ይፋ አደረገ፤ የኢዜማ የ ” ፍትህ” ሩጫ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *