ከሀብት ምዝገባ ጋር በተያያዘ የባለስልጣናት ፈቃደኛ አለመሆን ፈታኝ እንደሆነበት የስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ገለፀ።ኮሚሽኑ በ2011 አፈጻጸምና በ2012 እቅድ በዛሬው እለት ውይይት በማካሄድ ላይ ይገኛል።

በውይይቱ ላይም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ሀብት ማስመዝገብ ላይ ያለው አፈጻጸም ደካማ መሆኑ በመድረኩ ተነስቶ ተገምግሟል።

ኮሚሽኑ ይህ ሊሆን የቻለውም ከሀብት ምዝገባ ጋር በተያያዘ የባለስልጣናት ፈቃደኛ ካለመሆን ጋር በተያያዘ መሆኑን የገለፀ ሲሆን በዚህም የሀብት መዝገባ ስራው ፈታኝ እንደሆነበት አስገንዝቧል።

አዲስ በመዘጋጀት ላይ ካለው ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት የስነ ምግባር ደንብ በተጨማሪ በሀብት ማሳወቅና ማስመዝገቢያ እንዲሁም የስነምግባር መኮንኖች አሰራርን ለመወሰን በወጣው ደንብ ላይ ረቂቅ ማሻሻያዎች መዘጋጀታቸውንም ገልጿል።

ከሀብት ምዝገባ በተጨማሪም ሙስና በሃገሪቱ ያለበትን ደረጃ ላይም ውይይት ተደርጎበታል። በዚህም ሙስና በሃገሪቱ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ እንደሚያስችል የታመነበት 3ኛው ሃገር አቀፍ የሙስና ቅኝት
ጥናት መጀመሩን ነው ኮሚሽኑ ያስታወቀው።

ከዚህ በተጨማሪም ሀገራዊ የፀረ ሙስና ፖሊሲና ስትራቴጂ የዝግጅት ሂደት መጀመሩንም ነው ኮሚሽኑ የገለፀው። የስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አየልኝ ሙሉዓለም እንደተናገሩት፥ የኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅን ጨምሮ ተቋማዊ የውስጥ አሠራርን የተመለከቱ መመሪያዎች ተዘጋጅተው ውይይት እየተደረገባቸው ነው።

ብልሹ ስነ ምግባርንና ሙስናን የመዋጋቱ ስራ በተቋማዊ አደረጃጀት ብቻ የሚሳካ ባለመሆኑም የህብረተሰቡን እና የሚመለከታቸው አካላትን የተቀናጀ ተሳትፎ ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡
በትዕግስት አብርሃም – fana broadcast 

Share and Enjoy !

Shares
Related stories   "የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለጀግኖች አርበኞች ነፃ ህክምና እንዲሰጥ ወሰነ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *