9 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚገመት የብር ጌጣጌጥና 520 የሞባይል ቀፎ በኮንትሮባንድ ሲንቀሳቀስ መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ በዛሬው እለት በያቤሎ መቅረጫ ጣቢያ ግምታዊ ዋጋው 9 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሆነ 190 ኪሎ ግራም የብር ጌጣጌጥ እና ግምታዊ ዋጋቸው 312 ሺህ ብር የሆኑ 520 የሞባይል ስልክ ቀፎዎች መያዙን አስታውቋል።

ንብረቶቹ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 A – 59037 አ.አ በሆነ ተሽከርካሪ ሲንቀሳቀሱ የተያዙ ናቸው።፡

ከዚህ ባለፈም ሚኒስቴሩ በዛሬው እለት በጅግጅጋ ቶጎ ጫሌ የመቅረጫ ጣቢያ ቅያሪ ጫማው ውስጥ በመደበቅ የውጭ ምንዛሪ ለማሳለፍ የሞከረን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሏል።

ልዑል ገብረየስ የተባለው ግለሰብ 53 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በህገ ወጥ መልኩ ከሃገር ሊያስወጣ ሲል፥ በጅግጅጋ ጉምሩክ የቶጎ ጫሌ ፈታሾችና የፌደራል ፖሊስ አባላት መያዙን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በተመሳሳይ በትናንትናው እለት ከምሽቱ 5 ሰዓት አካባቢ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 02764 ሱ.ማ የሆነ ባለ ስድስት ጎማ ኒሳን ዩዲ ተሽከርካሪ ግምታዊ ዋጋቸው 2 ሚሊየን ብር የሚሆን የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን ጭኖ ሊገባ ሲል በቁጥጥር ስር መዋሉ ይታወሳል።

FBC

Related stories   ኢትዮጵያ በግድቡ ዙሪያ እየተካሄደ ያለው ውይይትን በተመለከተ ያላትን አቋም ግልፅ አደረገች

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *