ZAGGOLE – ዛጎል

“Our true nationality is mankind.”H.G.

በጋምቤላ ክልል 285 ባለሃብቶች ከአካባቢው ተሰወሩ፣ ከፍተኛ እዳ እላባቸው

በጋምቤላ ክልል ሁለት መቶ ሰማኒያ ስምንት ባለሃብቶች መሰወራቸው ተሰማ። ባለ ሃብቶቹ በእርሻ ኢንቨስትመንት ለመሰማራት ሰፋፊ መሬትና ብድር ከወሰዱ በሁዋላ ላለፉት ሶስት ዓመታት ስራ በፕሮጀክታቸው ላይ እንዳልታዩ ነው የተገለጸው። እነማን እንደሆኑ በስም ባይገለጽም በክልሉ አብዛናውን የእርሻ መሬት ላምልማት ብድር የወሰዱት የትህነግ ነባር ታግዮችና የሚቀርቧቸው እንደሆነ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ያስተኑት ጥናት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

አዲስ ዘመን የክልሉን ኢንቨስትመንት ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ ዋና ዳሬክተር አቶ ኡጁሉ ኡሞድ ጠቅሶ እንደዘገበው በክልሉ በተለይም በግብርና ኢንቨስተመንት ለመሰማራት ፈቃድ ከወሰዱ ባለሃብቶች አብዛኛዎቹ መሬት ተረክበው ከሶስት ዓመታት በላይ መሰወራቸውን ተናግረዋል።

14 ባለሙያዎች ተሳተፉበት  ጥናት “በሰፋፊ እርሻ” ስም ከተፈቀደው 5 ቢሊዮን ብድር ውስጥ 25በመቶው ማለትም “ለሥራ ማስኬጃ” በሚል የተለቀቀው “1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ለምን አላማ እንደዋለ ለመተንተን” አልቻለም፡፡ ለመተንተን ያልተቻለው ገንዘቡ እንዳይተነተኑ ልዩ ፈቃድ በተሰጣቸው ወይም በማይተነተኑ የህወሃት “የመሬት ከበርቴዎች” ገብቶ ስለመሆን በጥናቱ  ምንም የተባለ ነገር የለም

Related stories   አውሮፓ ህብረት እየተሽኮረመመ ታዛቢ ሊልክ ነው

“የጥልቅ ተሃድሶ” መንፈስ የተጠናወተው የተባለለት ሪፖርት ሌላም ጉዳይ “አጋልጧል”፡፡ ቀረጥ ሳይከፈልባቸው ለእርሻ ልማት ብቻ እንዲገቡ ከተደረጉት “565 ትራክተሮች ውስጥ መስክ ላይ የተገኘው 312፣ ከ731 ማረሻ የተገኘው 523፣ ከ261 ፒክ አፕ ተሽከርካሪ የተገኘው 102፣ ከ62 ዶዘር 42 ብቻ የተገኘ” ነው ይላል፡፡ በእንግሊዝኛ የሚታተመው አዲስ ፎርቹን እንደዘገበው ከሆነ ደግሞ “ከ242ቱ የቀረጥ ነጻ ዕድል ከተሰጣቸው ባለሃብቶች” መካከል አንድ ስሙ ያልታወቀ “ልማታዊ ባለሃብት” 78 መኪናዎችን ሳንቲም ቀረጥ ሳይከፍል ማስገባቱን ዘግቧል፡፡  የጥናቱን ሙሉውን ሪፖርት  እዚህ ላይ ያንብቡ

የኢዜአ ዜና እንዲህ ይነበባል

በጋምቤላ ክልል ለግብርና ኢንቨስትመንት መሬት የወሰዱ ባለሃብቶች ፈጥነው ወደ ሥራ እንዲገቡ የክልሉ መንግሥት ጥሪ አቀረበ። በክልሉ በግብርና ኢንቨስትመንት ለመሰማራት መሬት የተረከቡ 285 ባለሃብቶች ከአካባቢው እንደተሰወሩ ተገልጿል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ሰሞኑን በአበቦ ወረዳ የባለሃብቶችን እርሻ በጎበኙበት ወቅት እንዳሳሰቡት  ኢንቨስትመንት ለአገር ልማት ያለውን ድርሻ በመገንዘብ መሬት የተሰጣቸው ባለሀብቶች ሥራ ፈጥነው መጀመር ይጠበቅባቸዋል።

በክልሉ በግብርና ኢንቨስትመንት ለመሰማራት ከገቡት ከ700 በላይ ባለሃብቶች መካከል 285ቱ መሬት ተረክበው መሰወራቸውን ተናግረዋል።

የኢንቨስትመንቱ ዘርፍ ለአገር ልማትም ሆነ ለዜጎች ሥራ ለመፍጠር ዓይነተኛ መሣሪያ መሆኑን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ የክልሉ መንግሥት የባለሃብቶች ችግሮች ለመፍታት ዝግጁ መሆኑን አስታውቀዋል። ለዚህም አልሚ ባለሃብቶች በመደገፍ ረገድ የክልሉ መንግሥትና በየደረጃው ያለው አመራር በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

የክልሉ ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ ዋና ዳሬክተር አቶ ኡጁሉ ኡሞድ በበኩላቸው በክልሉ በተለይም በግብርና ኢንቨስተመንት ለመሰማራት ፈቃድ ከወሰዱ ባለሃብቶች አብዛኛዎቹ መሬት ተረክበው ከሶስት ዓመታት በላይ መሰወራቸውን ተናግረዋል።

ኤጀንሲው አልሚ ባልሆኑ ባለሃብቶች የተያዘው መሬት ወደ መንግሥት ተመላሽ እንዲሆን ለክልሉ ኢንቨስትመንት ቦርዱ የውሳኔ ጥያቄ ቢያቀርብም፤ ቦርዱ ለተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ማድረጉን ተናግረዋል።

ኤጀንሲው እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2011 ባለው ጊዜ የጠፉት ባለሃብቶች ቀርበው ጉዳያቸውን ማስረዳት ካልቻሉ የያዙት መሬት ተመላሽ ሆኖ ለሌሎች ባለሃብቶች የሚተላለፍ ይሆናል ብለዋል።

መሬት መያዝ ያለበት ”በልማት አርበኛ ባለሀብቶች” ነው ያሉት ዳይሬክተሩ፣ ኤጀንሲው ለአልሚ ባለሃብቶች ድጋና እውቅና እንደሚሰጥ ልጸዋል።

በወረዳው በግብርና ኢንቨስትመንት ከተሰማሩት ባለሃብቶች መካከል የዘሩ ገብረሊፋያኖስ የእርሻ ልማት ተወካይ አቶ ሮቤል ገብረሊፋያኖስ አካባቢው ለግብርና ልማት ምቹ በመሆኑን ተጠቃሚ ሆነናል ይላሉ።

ከገበያ በስተቀር በአካባቢው ችግር ያለመኖሩን ተናግረዋል።

በክልሉ ከውጭ የገቡትን ሳይጨምር ከ700 ለሚበልጡ ባለሃብቶች ከ600 ሺህ ሄክታር መሬት ለባለሃብቶች መተላለፉን የኤጀንሲው መረጃ ያመለክታል።