በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ከሐምሌ ወር መጨረሻ ጀምሮ በተከሰተው የቺኩን ጉንያ በሽታ ወረርሽኝ እስካሁን 15 ሺህ 192 ታማሚዎች መመዝገባቸውን በኢትዮጵያ ማህበረሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የህብረተሰብ ጤና አደጋ ቅኝት እና ምላሽ ተጠባባቂ ዳይሬክተር አቶ መስፍን ወሰን ተናግረዋል፡፡

በበሽታው ምክንያት ምንም አይነት ሞት እስካሁን እንዳልተመዘገበ አቶ መስፍን አያይዘው ገልጸዋል፡፡ ቺኩን ጉንያ በሽታ አብዛኛውን ጊዜ በሞቃታማ አካባቢ በምትራባ ኤደስ በምትባል ትንኝ ንክሻ አማካኝነት ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍ ነው እንደሆነ ተነግሯል፡፡

ከፍተኛ ትኩሳት፣የመገጣጠሚያ ህመም፣የጡንቻ ህመም ፣ማስመለስ እና በሰውነት ላይ ሽፍታ መፍጠር ከበሽታው ምልክቶች ውስጥ ናቸው፡፡ አንድ ሰው በኤደስ ትንኝ ከተነከሰ ከ3 እስከ 4 ቀን ውስጥ ምልክቱ ሊታይበት ይችላል ፡፡

በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ ከንቲባ የሚመራ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ወረርሽኑን ለመቆጣጠር እየተሰራ መሆኑን እና በየቀኑ ስራዎችን እየገመገመ እንዳለ ተጠባባቂ ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

ህብረተሰቡ የሚያጠራቅመውን የዝናብ ውሃ ዝግ የማድረግ ፣የቤት ለቤት የኬሚካል ርጭት እና ያቆሩ ውሃዎችን ማፍሰስ ለትንኟ መራባት ምቹ ሁኔታ እንዳይፈጠር ለማድረግ ማህበረሰቡ ግንዛቤ እንዲኖረው የማድረግ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ ተብሏል፡፡

ህክምናው በሁሉም የመንግስት ጤና ተቋማት እና የግል የህክምና ተቋማት እተሰጠ እንደሚገኝም ተነግሯል፡፡

በተለይ ድሬዳዋ አካባቢ የሚገኝ ህብረተሰብ ውሃ ያቆሩ አከባቢዎችን ነፃ ማድረግ፣ ሰውነትን የሚሸፍን ልብስ በመልበስ እና ቅባት በመቀባት እንዲሁም አጎበርን መጠቀም ወረርሽኑን እንዲከላከል አቶ መስፍን ጠይቀዋል፡፡

የህመሙ ምልክት ሲታይ ወደ አቅራቢያው የጤና ተቋም በፍጥነት በመሄድ ህክምና መውሰድ እና ወደ ከተማዋ የሚመጡ የህብረተሰብ ክፍሎችም አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉም አቶ መስፍን ጥሪ ማቅረባቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

OBN

Related stories   ምክር ቤቱ በሕግ ማስከበር ዘመቻ ጉዳት ለደረሰባቸው የሠራዊቱ አባላት 9 ሚሊዮን ብር የሚገመት የዓይነትና የገንዘብ ድጋፍ አደረገ

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *