በቀጣይ የትምህርት ዘመን በ30 ሺ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የ 0 ክፍል ትምህርት ይሰጣል። ለትምህርት ጥራት ልዩ ትኩረት በመስጠት በቀጣይ የትምህርት ዘመን በ30 ሺ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የ 0 ክፍል ትምህርት እንደሚሰጥ ተገለጸ።

29ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ በጅግጅጋ ከተማ “ስር ነቀል የትምህርት ሥርዓት ለውጥ ለሁለንተናዊ ሀገራዊ ዕድገት” በሚል መሪ ሀሳብ ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ቀናት በመካሄድ ላይ ነው፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ጥላዬ ጌቴ በመክፈቻው ላይ እንዳሉት የሚፈለገውን የትምህርት ጥራት ለማምጣት የትምህርትና ስልጠና ስርዓቱ በየጊዜው መገምገም ይኖርበታል፡፡

ትምህርት ከድህነት ማምለጫና የዴሞክራሲ ስርዓት መገንቢያ በመሆኑ የነበሩ ክፍተቶችን ለማስተካከል የትምህርት ስርዓቱ በየጊዜው ይፈተሻል ብለዋል፡፡

በዚህም መዳረሻውን 2022 ዓ.ም ያደረገና በ2012 የሚጀምረው አዲሱ የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ ካርታ ዝግጅት ተጠናቋል ብለዋል፡፡ በዚህም ለትምህርት ጥራት ልዩ ትኩረት መስጠት ከቀጣዩ የትምህርት ዘመን አንስቶ ዋናው ስራችን ነው ብለዋል። በዚህም በ30 ሺ የመደበኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የቅድመ መደበኛ ክፍል ወይም የ 0 ክፍል ትምህርት ይሠጣል ብለዋል፡፡

ለሶስት ተከታታይ ቀናት በሚቆየው በዚሁ የትምህርት ጉባዔ የ2011 የትምህርት ዘመን ዕቅድ አፈፃፀም ይገመገማል፤ የ2012 የአጠቃላይ ትምህርትና የከፍተኛ ትምህርት እቅድ ላይም ውይይት ይደረጋል፡፡ ኢዜአ

Related stories   ድርቅ በኢትዮጵያ ታሪክ አስከፊ ወደ ተባለ ረሃብ አደገ፤ “ዕድገታችን የረሀብ አደጋን ቀንሶልናል” መለስ 2004

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *