“Our true nationality is mankind.”H.G.

የስድስተኛው አገር አቀፍ ምርጫ ጉዳይ ለመጨረሻ ውስኔ ለቋሚ ኮሚቴ ተመራ

150 ሺህ የሚሆኑ የምርጫ አስፈጻሚዎችን ለማሰልጠንም እንዲሁ ወረርሽኙ አዳጋች በመሆኑ ቦርዱ የዳሰሳ ጥናት አካሂዶ ውሳኔ ላይ ደርሷል

(ኢዜአ) በኮቪድ-19 ምክንያት ለጊዜው እንደማይካሄድ የውሳኔ ሀሳብ የቀረበበት ስድስተኛው ብሔራዊ ምርጫ ለሕዝብ ተወካዮች ቀርቦ ለመጨረሻ ውስኔ እንዲረዳ በዝርዝር እንዲታይ ለቋሚ ኮሚቴ ተመራ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ከተወያየባቸው ጉዳዮች ውስጥ አንዱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ስድስተኛው ብሔራዊ ምርጫን በተመለከተ ያቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ ማጽደቅና ቀጣይ የመፍትሄ ሀሳብ እንዲቀርብ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መምራት ነው።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ የጠቅላላ ምርጫን በተመለከተ ለምክር ቤቱ ዝርዝር ማብራሪያ አቅርበዋል።

ዘንድሮ ይካሄድል ተብሎ ለነበረው ምርጫ በቦርዱ የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ መሰረት የመራጮች ምዝገባ የሚጀምረው ከሚያዚያ 14 ቀን 2012 ዓ.ም ነበር።

በዚሁ መሰረት ከዚህ ቀን ጀምሮ የምርጫ አስፈጸሚው ምልመላ፣ ስልጠናና ስምሪት፣ የመራጮች ትምህርትና መመዝገቢያ ቁሳቁስ ስርጭቶችን ለማካሄድ ታስቦ ነበር ብለዋል።

ይሁን እንጂ ኮቪድ-19 በወረርሽኝ መልክ መከሰቱ ቁሳቁስ ለማሸግና የህትመት ውጤቶችን ለመዘጋጀት እንዳልተቻለ ተናግረዋል።

Related stories   አገርን የከዱ ተደመሰሱ፤ የሳተላይት መገናኛና መድሃኒት " ጁንታው" እጅ ሳይገባ ተያዘ

“በተጨማሪም 150 ሺህ የሚሆኑ የምርጫ አስፈጻሚዎችን ለማሰልጠንም እንዲሁ ወረርሽኙ አዳጋች በመሆኑ ቦርዱ የዳሰሳ ጥናት አካሂዶ ውሳኔ ላይ ደርሷል” ብለዋል።

የቦርዱ ውስኔም በጊዜ ሰሌዳው መሰረት መከናወን ያለባቸው ሥራዎች ለጊዜው እንዲቆሙ ተወስኗል፣ በቀጣይ ነገሮች ሲለወጡ ቦርዱ አዲስ የምርጫ ኦፕሬሽን ዕቅድና ሰሌዳ በማውጣት እንቅስቃሴ እንደሚጀምርም ተወስኗል።

ሌላው ቦርዱ መሰራት የሚችሉትን ስራዎች እየሰራ ለመቆየት ውስኔ መወሰኑን ጠቅሶ ምክር ቤቱ በዚህ ሁኔታ ምርጫውን ማካሄድ እንደማይቻል ተገንዝቦ ውስኔ እንዲያሳልፍ ጠይቀዋል።

ከአንድ የምክር ቤት አባል በስተቀር በአመዛኙ የምክር ቤቱ አባላት ውሳኔው ወቅታዊ፣ ትክክለኛና የሕዝቡን ደህንነት ያስቀደመ በመሆኑ ቦርዱ ሊመሰገን ይገባል ብለዋል።

እንድ አባል “እንደዚህ አይነት ውሳኔዎችን ረጋ ብሎ፣ አስተውሎ፣ የሚከተለውን ጦስ አመዛዝኖ ውሳኔ ላይ መድረስ አስፈላጊ ነው” ብለዋል።

አባሉ በምርጫ ቦርድ በኩል የቀረበው ውሳኔ ውስንነቶች ያሉበት መሆኑን ገልጸው በተለይ ደግሞ ቫይረሱ አሁን በኢትዮጵያ ወረርሽኝ ደረጃ ላይ ስለመድረሱ ጥርጣሬ እንዳላቸውም ገልጸዋል።

Related stories   “የግድቡ ግንባታ ውሃ ይቀንስብኛል የሚለው የግብጽ ጩኸት የማጭበርበሪያና የተለመደ የሃሰት ክስ ነው››

ነገሩ በአግባቡ ካልተጤነ ሊያስከትል የሚችለው የፖለቲካ አደጋ ቀላል አለመሆኑን መገንዘብና ለፖለቲካ ጤንነቱም መጨነቅ ተገቢ መሆኑን አሳስበዋል።

ሌሎች የምክር ቤት አባላት ግን ኮሮናቫይረስ የዓለም ዓቀፍ ስጋት እንደመሆኑ ቅድሚያ ለሰብዓዊነትና ለሰው ልጅ መስጡቱ ተገቢ ውስኔ ነው ብለውታል።

የቀረበው ውስኔ እውነታን መሰረት ያደረገ፣ ሕዝብ ከምርጫ በላይ መሆኑ የተገለጸበትና ትክክለኛ ውሳኔ ነው በማላትም ገልጸዋል።

ሂደቱ የኢትዮጵያን ፖለቲካና ፖለቲከኞች ሁኔታ የሚፈትን እንደመሆኑ መጠን አሁንም በዚህ ጉዳይ ሁሉንም አማራጮች መቃኘት ተገቢ መሆኑም ተመልክቷል።

አባላቱ የተወሰኑ አካላት በሽታውን ተገን አድረገው የስልጣን ጥማቸውን ለማርካት እየተንቀሳቀሱ መሆኑንም ጠቁመው ለዚህም በር መክፈት እንደማያስፈልግም ጠቁመዋል።

የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ በበኩላቸው ምክር ቤቱ ቦርዱን በቅርበት ክትትል ሲያደርግና ሲደግፍ መቆየቱን ያስታውሳሉ።

ውሳኔው ለሕዝቡ ጤንነት ቅድሚያ የሚሰጥና የፖለቲካ ጤናማነት ማስጠበቅ የሚያስችል እንዲሁም ሕግ መንግስቱን አክብሮ ለማስከበር የሚረዳ ነው ብለውታል።

በመጨረሻም ምክር ቤቱ ውሳኔውን በአብላጫ ድምጽ መርምሮ ካጸደቀ በኋላ ቀጣይ ለመጨረሻ ውሳኔ ይረዳ ዘንድ የመፍትሄ ሃሳብ እንዲቀርብ ለሕግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቷል።

Related stories   “ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን በአንድነት በመከባበር፤ በመተሳሰብ እና በመረዳዳት ሊያከብር ይገባል”

በተመሳሳይ ምክር ቤቱ በዛሬ መርሃግብሩ ለቆላማ አካባቢ የኑሮ ማሻሸያ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚውል ከዓለም አቀፍ ግብርና ልማት ፈንድ የተገኘ የ90 ሚሊዮን ዶላር ብድርም አጽድቋል።

“ብድሩ በአራት ክልሎች ለሚገኙ 100 ወረዳዎች የሚውል ሲሆን በዚህም 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሰዎችን ተጠቃሚ ያደረጋል” ተብሏል።

ከዚህ ባለፈ ኢትዮጵያ ለሁለተኛው አገር አቀፍ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት፣ ሳኒቴሽንና ሃይጂን ፕሮግራም ማስፈጸሚያ እንዲሁም ለደብረማርቆስ – ሞጣ መንገድ ማሳደጊያና ማሻሻያ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ ከሳዑዲ ለማት ፈንድ ጋር የተደረሰውን የብድር ስምምነት ረቂቅ አዋጅ አጽድቋል።

ሌላው ምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት ያጸደቀው ረቂቅ አዋጅ የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የልህቀት ማዕከል መመስረቻ ማስፈጸሚያ እንዲውል ከኮሪያ ኤግዚም ባንክ ጋር የተደረገ የብድር ስምምነት ነው።

ምክር ቤቱ የኤሌክትሮኒክ ትራንዛክሽንን ለመደንገግ የወጣውን ረቂቅ አዋጅም ለሰው ኃብት ልማትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች መርቷል።

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0