የጦር መሣሪያን የመያዝ፣ የመግዛትና የመሸጥ ሥርዓቱ በመንግሥት እውቅና ብቻ የሚያደርግ ዓዋጅ ሥራ ላይ መዋሉንና የመሳሪያ ፈቃድ በየዓመቱ ማደስና ግብር መክፈል ግድ መሆኑንን ፋና ወይዘሮ አዳነች አቤቤን ጠቅሶ ይፋ አደረገ።

የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጋር ባደረጉት ቆይታ ዓዋጁ በጦር መሣሪያ ዝውውርና አስተዳደር ላይ የነበረውን የሕግ ክፍተት ይሞላል።

Related stories   The Legend of the “Greater Republic of Tigray” and the Delirious TPLF Media

በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት በመንግሥት ኃላፊነት የተሰጣቸው አካላት ዓዋጁን በማስተግበር የጦር መሣሪያ ያለው ግለሰብም ይሁን ተቋም ምዝገባውን የማድረግ ግዴታ እንዳለባቸው ገልጸዋል።

የጦር መሣሪያ የያዘና ያስመዘገበ ሁሉ እንዲይዝ እንደማይፈቀድና ፈቃድ የሚሰጠው ተቋም ወይም ግለሰብ በዓዋጁ መሰረት ህጋዊ የሚያደርጉትን መስፈርት አሟልቶ መገኘት እንደሚጠበቅበት ወይዘሮ አዳነች አብራርዋል።

ዓዋጁ የአገር ውስጥ ድርጅቶችንና ሌሎች አካላትንም የሚያይበት ሕጋዊ አካሄድ እንዳለውም ዐቃቤ ሕጓ ገልጸዋል።

Related stories   ወርቃማ ድል የተጎናጸፍነው ትልቁን ስዕል ማየት የሚችሉ ፣ ችግሮቻቸውን የመፍታት ልምድ ያላቸው እናትና አባቶች ስላሉን ነው – ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ

በመሆኑም ማንኛውም በአገር ውስጥ የሚንቀሳቀስ ድርጅት የጦር መሣሪያ እንቅስቃሴውም ይሁን ይዞታው ህጋዊነቱ የተረጋገጠና በውል የሚታወቅበት አሰራር ይዘረጋለታል ብለዋል።

በኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ የጦር መሣሪያዎችን የመሸጥና የማዘዋወር ህጋዊ እውቅና የተሰጠው አካል ባለመኖሩ ግዥና ዝውውሩ የሚካሄደው ህግን ባልተከተለ መንገድ ነበር።

ይሁን እንጂ የጦር መሣሪያውን የገዛው አካል የምዝገባ መስፈርቱን ካሟላና ወንጀል ያልተሰራበት መሆኑ ከተረጋገጠ አስመዝግቦ መያዝ ይፈቀድለት እንደነበርም ይታወቃል።

Related stories   በኢትዮጵያ የትግራይ ጉዳይ ላይ የጸጥታው ምክር ቤት ሳይስማማ ተበተነ፤ አማራ ትህነግን በህግ ሊጠይቅ ነው

አሁን ተግባር ላይ የዋለው ዓዋጅ አሰራሩ ሙሉ በሙሉ እንደሚያስቀርና የጦር መሣሪያን ሽያጭና ዝውውር የሚከታተል በመንግሥት እውቅና የሚሰጠው አካል እንደሚኖርም ወይዘሮ አዳነች አስረድተዋል።

በዓዋጁ መሠረት ለጦር መሣሪያ የሚሰጠው ፈቃድ በየዓመቱ ይታደሳል፤ ባለ ፈቃዱም በየዓመቱ ክፍያ ይፈጽማል።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *