ZAGGOLE – ዛጎል

“Our true nationality is mankind.”H.G.

ኮቪድ 19 ወደ ሁለተኛው ደረጃ – ፖለቲከኞ ወደ አዘቅት!!

ሕዝብን መናቅ – ለኢትዮጵያ ፖለቲከኞች በወርቅ የተቀባ ገድላቸው ነው

የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ በኢትዮጵያ የማሻቀብ ምልክት አሳየ። ልክ በአውሮፓ እንደሆነው አዝጋሚም ቢሆን በአንድ ቀን 17 ሰዎች መገኘታቸው መጪውን ጊዜ አስፈሪ ያደርገዋል። የጤና ሚኒስትሯ ዛሬም ሕዝብ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ወትውተዋል። በተመሳሳይ መንግስት ለማፍረስ ሴራው ቀጥሏል።

በዛሬው እለት የቫይረሱ ተጠቂ የሆኑ ሰዎች መብዛት ዜጎችን ማስደንገጡን የተለያዩ መገናኛዎችና የማህበራዊ ገጾች መረጃ ናቸው። በተመሳሳይ ለመስከረም መንግስት ለማፍረስ 30 ቀጠሮ የያዙት እጅግ ውስን ስልጣን ብቻ የሚናፍቁ ክፍሎች በተለያዩ ሚዲያዎች ዓመጽ የሚያራቡ መረጃ እያከፋፈሉ ነው።

የኢትዮጵያ መከላከያና ፖሊስ ለመንግስት ጀርባቸውን እንዲሰጡ ውትወታው በበዛበት በአሁኑ ወቅት አንድ ሰው መሞቱንና 17 አዲስ ጠጠቂዎች መገኘታቸውን የጤና ሚኒስትሯ የገለጹት በሃዘን ነው። ” በኢትዮጵያ እስካሁን በአንድ ቀን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ ሆኖ ተመዝግቧል፤ በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸውን ሰዎች ቁጥር 162 አድርሶታል፣ እባካችሁን ተጠንቀቁ” ሲሉ ወገናዊና ለባዊ ልመና አቅርበዋል።

Related stories   በምናለሽ ተራ ገበያ – ከሰኞ እስከ እሁድ

“ትክክለኛ ትምህርትና እርምጃ ለመውሰድ፣ በብዙ ቁጥር መያዝ፣ በብዙ ቁጥር መሞት የለብንም” ያሉት ዶክተር ሊያ፣ ኬንያ አስቀድሞ ትንሽ ቁጥር በመመዝገቡ ዛሬ ዋጋ እንዳስከፈላቸው አመላክተዋል። የሃይማኖት አባቶችም የመከሩት ይህንን ነው።

ዜጎች እየከፋ የመጣውን ወረሺኝ ለመታደግ፣ አደጋውን ለመቀነስ፣ መከራውን ለማርገብና በዚሁ ችግር ሳቢያ ረሃብ እንዳይከሰት፣ ዝርፊያና ወንጀል እንዳይስፋፋ፣ ኢኮኖሚው እንዳይሰበር የሚያነቃቃቸው ሃይል በሚናፍቁበት ውቅት ላይ አቶ ጃዋርና አቶ ልደቱ እንዲሁም የትግራይ ክልል በጣምራ እየፈጠሩት ያለው ጫና በታሪክ የሚመዘገብ መሆኑን ለጉዳዩ ትኩረት የሰጡ ተቆርቋሪዎችና ሕዝብ እየተናገሩ ነው። ፋና ከታች ያለውን መረጃ ዘግቧል።

Related stories   የቻይናው ሮኬት ስብርባሪ በኢትዮጵያ ቢወድቅ ምን ዓይነት የጥንቃቄ እርምጃዎች ሊወስዱ ይገባል?

ባለፉት 24 ሰዓታት ለ1 ሺህ 382 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 17 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

ሚኒስትሯ በፌስ ቡክ ገጻቸው እንዳስታወቁት ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ፥ አሁን ላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 162 ደርሷል።

ቫይረሱ ከተገኘባቸው ውስጥ ሰባቱ ከጂቡቲ የተመለሱና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበሩ ሲሆኑ፥ ስድስቱ ደግሞ ከሶማሊያ የተመለሱና በሶማሌ ክልል አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበሩ ናቸው ተብሏል።

Related stories   የዓለም ጤና ድርጅት ለቻይናው ክትባት ይሁንታውን ሰጠ

አራቱ ደግሞ በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ሲሆኑ፥ ሁሉም የውጭ ሃገር የጉዞ ታሪክ የሌላቸው ናቸው።

ከእነዚህ ውስጥ የ27 አመቱ ወጣት የስራው ባህሪ ተጋላጭነት ያለው ሲሆን፥ የ28 አመቷ ወጣት እና የ53 አመቷ ሴት ደግሞ ቫይረሱ ከተገኘበት ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው ናቸው።

የአፋር ክልል ነዋሪ የሆነውና አዲስ አበባ ከተማ የተገኘው የ39 አመቱ ኢትዮጵያዊ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ያለው ንክኪ እየተጣራ መሆኑ ተገልጿል።

አሁን ላይ በኢትዮጵያ በለይቶ ህክምና ውስጥ ያሉ 63 ሲሆኑ፥ 93 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል ተብሏል።