በፖለቲካ ዙሪያ መነጋገር የሚቻለው የዜጎች ደህንነት እና የሀገር ህልዉና ሲረጋገጥ በመሆኑ ፣መጀመሪያ ሁሉም ዜጋ ሳይለያይ ከመጣው ወረርሽኝ ራሱንና ማህበረሰቡን እንዲጠብቅ ፓርቲዎቹ አስታውሰዋል፡፡

በሶማሌ ክልል የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ጊዜ መራዘሙን ተከትሎ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ ምክክር አደረጉ። ፓርቲዎች በሀገራዊ እና ወቅታዊ ሁኔታ ላይ በዛሬው ዕለት በጅግጅጋ ውይይት አካሂደዋል፡፡

በውይይቱ የተካፈሉት የፖለቲካ ድርጅቶች የምዕራብ ሶማሌ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ፣ህብረት ለዲሞክራሲና አንድነት ፓርቲ ፣የዱቦና ደግኖ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ፣ የዲል ወቢ ፓርቲ እና የሶማሌ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ናቸው፡፡

የኮቪድ 19-ን ወረርሽኝ መስፋፋትን ተከትሎ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በዕቅዱ መሰረት ማከናወን ባለመቻሉ ሀገራዊ ምርጫው በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ ሊደረግ እንደማይችል ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውሳኔ እንዲሰጥበትና ምርጫው እንዲተላለፍ  መደረጉ ላይ ፓርቲዎቹ ተወያይተዋል ፡፡

የኮቪድ 19-ን ወረርሽኝ መስፋፋትን ተከትሎ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በዕቅዱ መሰረት ማከናወን ባለመቻሉ ሀገራዊ ምርጫው በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ ሊደረግ እንደማይችል ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውሳኔ እንዲሰጥበትና ምርጫው እንዲተላለፍ  መደረጉ ላይ ፓርቲዎቹ ተወያይተዋል ፡፡

በዚህም የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከል ለነሐሴ መጨረሻ ተይዞ የነበረው አገራዊ ምርጫ መራዘሙ ተገቢ መሆኑን የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች በዛሬው ዕለት ባደረጉት ውይይት ላይ ገልፀዋል።

በፖለቲካ ዙሪያ መነጋገር የሚቻለው የዜጎች ደህንነት እና የሀገር ህልዉና ሲረጋገጥ በመሆኑ ፣መጀመሪያ ሁሉም ዜጋ ሳይለያይ ከመጣው ወረርሽኝ ራሱንና ማህበረሰቡን እንዲጠብቅ ፓርቲዎቹ አስታውሰዋል፡፡

የኮቪድ-19ን የመከላከል ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የገለጹት የፓርቲ ተወካዮቹ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያፀደቀው ህገ-መንግስት ትርጓሜ መጠየቅ የሚለው አማራጭ የተሻለ በመሆኑ በጉዳዩ ላይ ተመሳሳይ አቋም መያዛቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

ዜናው የፋና ነው

Share and Enjoy !

0Shares
0

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *