ጀርመን ሱቆች ይከፈቱ፤ እግር ኳስም ይጀመር አለችመራሄተ መንግሥት አንጌላ መርክል ጀርመን የቫይረሱን የስርጭት ፍጥነት ለመቀነስ የወጠነችው ግብ በመሳካቱ የንግድ ቦታዎች እንዲከፈቱና ደንበኞቻቸውን ማስተናገድ ይችላሉ ብለዋል።
ከዚህም በተጨማሪ ቡንደስሊጋውም እንዲጀመር የተወሰነ ሲሆን፤ ትምህርት ቤቶችም በቀጣይ ወራት ይከፈታሉ ተብሏል። የጀርመን መሪ አንጌላ መርክል መንግሥታቸው ይህን የሚያስፈጽመው በከፍተኛ ጥንቃቄ ነው ብለዋል።
16ቱም የጀርመን ግዛቶች ከፌደራል መንግሥቱ ጋር በመጣመር የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር አመርቂ ውጤት ማምጣታቸው ይነገራል።
Related stories እውነትን ለሥልጣን መናገር !! ሳማንታ ፖወር - ለኢትዮጵያ ዘር ፖለቲከኞች መከላከል አቁሚ!
Powered by Inline Related Posts
ባቫሪያን የተሰኘው ግዛት መሪ ማርኩስ ሶደር ጀርመን የተሻለ ስትራቴጂ በመንደፏ ከየትኛውም አገር በተሻለ ሁኔታ ቫይረሱ ሊያስከትል የሚችለውን ጉዳት መቀነስ ችላለች ብለዋል።
አንጌላ መርኬል ጀርመናዊያን ከመንግሥት የሚተላለፉ ምክረ ሃሳቦችን በመከተላቸው ምስጋና አቅርበዋል። ስፋታቸው እስከ 800 ካሬ ሜትር የሆኑ የንግድ ቦታዎች እንዲከፈቱ ግዛቶቹ እና ፌደራል መንግሥቱ ተስማምተዋል። ባለሱቆችም ሆኑ ገበያተኛው የፊት እና አፍንጫ ጭምብል ማድረግ እና ማህበራዊ እርቀት መጠበቃቸውን መቀጠል አለባቸው ተብሏል።
Related stories Ministry Urges Amnesty Int’l to Use Appropriate Sources in Report to Uncover the Truth
Powered by Inline Related Posts
በተጨማሪም ቡንደስሊጋው በባዶ ስታዲያም ከ10 ቀናት በኋላ እንዲጀምር ተስማምተዋል።
BBC amaharic