የሽግግር መንግስት መቋቋም አለበት በሚል ቅስቀሳ የጀመሩ ውስን አካላት የጀመሩትን የጊዜ ገደብ ያስቀመጠ ዘመቻ መንግስት እንደማይታገስና ህግ የማስከበርም ሙሉ ብቃት እንዳለው አስታወቀ። ጠመንጃ አንስቶ ጫካ የከተመው ኦነግ ሸኔ በገለልተኛ አገር ወይም አካል መደራደር እንደሚፈልግ ይፋ አደረገ። ዘመቻው መንግስትን አጣብቂኝ ውስጥ በመክተት እጁን ለመጠንዘዝ በመቀናጀት የሚከናወን ዘመቻ መሆኑም እየተነገረ ነው።

ዛሬ ጠዋት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በሰጡት ከሰላሳ ደቂቃ የዘለለ መግለጫ እየቀረቡ ያሉ ህገ መንግስታዊ መፍትሄዎች ሁሉንም አካል በእኩል ደረጃ ባያስደስቱም ከህገ መንግስታዊ መፍትሄ ውጪ መሆን እንደማይቻል አጽንዎት ሰጥተው ተናግረዋል።

በተለያዩ መልኩ እንደ አማራጭ የቀረቡትን የመፍትሄ ሃሳቦችን ያብራሩት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከሕዝብ በተለያዩ ጊዜያት ለሚነሱ ህግ የማስከበር ጥያቄዎች ዛሬ ምላሻ ሰጥተዋል።

በህገ መንግስቱ ከተካተቱት አንቀጾች ተለይተው ትርጓሜ እንዲሰጥባቸው አግባብ ላለው አካል መላኩን ያወሱት ዶክተር አብይ፣ ከዚህ ህጋዊ የመፍትሄ አማራጭ በዘለል ጥናትና ምርምር ሳያደርጉ ህጋዊ መፍትሄ የለም የሚሉት ክፍሎች በአቋራጭ ስልጣን ለመያዝ ያላቸውን ፍላጎት ማንጸባረቃቸውን ነው የተናገሩት።

Related stories   ደመቀ መኮንን በፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሚመራ የአውሮፓ ህብረት ልዑክ ጋር ተወያዩ

ኮቪድ 19ን ከተቆጣጠሩ መቆጣጠር ከተቻለ በሁዋላ በአጭር ጊዜ ወደ ምርጫ እንደሚገባ ደግመው ያስታወቁት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ይህን ህጋዊ አካሄድ ተከትሎ ወደ ምርጫ መግባት እየተቻለ ” ራሳቸውን መድሃኒት” ያደረጉና በተወሰነ ከባቢ ውስን ድጋፍ ያላቸው ስልጣን በአቋርጭ የሚሹ አደብ እንዲገዙ አሳስበዋል።

” ሁሉም እየተነሳ ህግ ተርጓሚና ፈራጅ ዳኛ ልሁን ካለ ምስቅልቅል ያመጣል” ሲሉ ግራ ቀኙን በማሳየት ንግግራቸውን ያሰተላለፉት አብይ፣ ” የህገ መንግስት አጣሪዎች” የተሰኘው ገለልተኛ አካል ብቻ ይህንን የማድረግ ህጋዊ ስልጣን እንዳለው ጠቁመዋል። አያይዘውም ይህንን አካሄድ በመግፋት ከመስከረም በሁዋላ መንግስት የለም የሚሉትን መንግስት እንደማይታገስ አስረግጠው ተናግረዋል።

” መንግስት ህግ የማስከበር ሙሉ ብቃትና ዝግጅት አለው” ሲሉ ያስታወቁት ዶክተር አብይ ባለፈው ሳምንት ” ከተቀናቃኝ ፓርቲዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ባንዶችና የኢትዮጵያን ጥቅም ከባዕድ አገራት ጋር በመሆን ለማምከን ደፋ ቀና ለሚሉ ማሳሰቢያ መስጠታቸው አይዘነጋም። በዚሁ ማስጠንቀቂያቸው የአገሪቱ የድህንነት፣ የጸጥታና፣ የፍትህ አካላት በነዚህ አካላት ላይ ማናቸውንም እርምጃ ለመውሰድ መንግስታቸው ሙሉ አቅም እንዳለው ያስታወቁት ” እመኑኝ” በማለት ነበር።

Related stories   “ዶላር እናወርዳለን” የውጭ አገር ዜጎችን የዝርፊያ ድራማ ፖሊስ አለሳልሶ ይፋ አደረገው

እስር፣ ማሳደድና፣ ትዕግስትን የመረጠው የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መንግስት እንደ ደካማና ህግ ማስከበር እንደማይችል ተደርጎ የሚወሰደው ስህተት እንደሆነ የሚናገሩ እንደሚሉት ” የኢትዮጵያ የጸጥታ አካላትና መከላከያ እጅግ መዘመኑንና አቅሙም ሆነ ዲሲፒሊኑ ከቀድሞው ጋር የማይወዳደር ነው”

ለአገሪቱ የጸጥታ ተቋማት ቅርበት ያላቸው እነዚህ ወገኖች እንደሚሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከወዳጅ አገራት ጋር በመሆን አየር ወለድና የአየር ሃይሉን እጅግ አስገራሚ መሳሪያ አስታጥቀውታል። በባለሙያም ደረጃ አግዝፈውታል። የእግረኛ ሰራዊቱም ቢሆን ለማንኛውም ግዳጅ የተዘጋጀ ነው።

ይህ በንዲህ እንዳለ ለቪኦኤ ሪፖርተር ናኮር መልካ ቅርብ የሆነው የኦነግ ሸኔ አዋጊ ጃል መሮ ለድርድር ዝግጁ መሆኑንን በስልክ ባደረገው ቃለ ምልልስ ይፋ አድርጓል። ይሁን እንጂ በገለልተኛ ወይ በሌላ አገር አደራዳሪነት ሊሆን እንደሚገባ አመላክቷል።

Related stories   “ትህነግ ከጁንታነትም ወርዶ በየጫካው ተሹለክላኪ የእህል ሌባ ሆኗል፣ ከያለበት እየታደነ ነው “ሜ/ጀ መሐመድ ተሰማ

ጃል መሮ ዛሬ በድንገት ለናኮር መልካ ስለድርድር ለመናገር ያነሳሳው ምክንያት በዝርዝር ባይቀርብም የኦሮሚያ የፖሊስ ኮሚሽነር ” ትጥቃቸውን ፈተው ከገቡ ማንም አይነካቸውም። መነጋገር ይቻላል” የሚል ምልሽ ሰጥተዋል። ናኮር ቀደም ሲል አቶ ታዬ ደንደአ የኦነግ ሸኔ ይፈጽማቸዋል ያሉትን እጅግ ዘግናኝ የተባሉ ጉዳዮች በመዘርዘር ጃል መሮ እንዲያስተባብሉ እድል ሰጥቷቸዋል። ይሁን እንጂ አቶ ታዬ በምስል አስደግፈውና ስም ጠቅሰው ያቀረቡትን መረጃ ሳይዘረዘር በግርድፍ ከማቅረብ በስተቀር መከራከሪያ ጋዜጠኛው መከራከሪያ ጥያቄ አልሰነዘረም። ወይም አቶ ታዬን አልጋበዘም።

ጉዳዩን የሚከታተሉ እንዳሉት የጃል መሮ የእርቅ ጥያቄና ዛሬ ላይ ያስፈለገው የሽግግር መንግስት የሚለውን ከኮረና ቫይረስ ወረሺኝ ጋር ተያይዞ የተነሳ አዲስ ዘመቻ የመቀላቀልና የኔት ወርክ እቅድ እንደሆነ እየገለጹ ነው።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *