ወዲ ስብሃት

ስምዖን እናት ዳቦ ቆርሳ የሰጥችው ስም ይሁን የቀበሮ ስም በውል አይታወቅም። ይህ ስም በቀጥታ ባይነሳም ዛሬ ተንስቷል። ይህ ቀበሮ አስሊ ሰላይ ስለሆነ ለዚህ ዘገባ ” ማላጩ” በሚል ይወሳል። ምላጩ መረጃ ሲጠባ እሱን ከሚጠባው መንታ ሰላይ ጋር ይገናኛሉ። ስራ ያገናኛቸውና አንዱ ፈላጊ፣ ሌላው ተፈላጊ ለመሆን በቁ። ቆይቶ ተውደዱ። ረብጣ ጉርሻ ፈላጊና ተፈላጊን አያያዛቸውና የሃሳብ ዳንስ በየጎራው ተጀመረ።

የሻዕቢያው ቀበሮ የሰማውን ጉዳይ እያብላላ ባለበት ቅጽበት የቀበሮው አሰማሪ መረጃው ደርሶት ነበርና ስምዖን ሌላ ቀለበት ወዲያው እየተጠመደለት ነበር። ዳሩ ምላጩ የቤቱን ጉዳይ ያውቀው ስለነበር ጉዳዩን አንግቦ አለቃው ደጅ በሚስጢር ተናዘዘ።

ጉዳዩ ሰሞኑንን ሲቦካ የከረመውና እየተቀነጨበ ሲቀርብ የነበረው የፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጉዳይ ነበር። ህወሃት ኢሳያስን ባደባባይ እርቅ መጠየቅ፣ በጓሮ ማስወገድ በሚለው ስልቷ ማድባቷን ከጀመረች ዘመን ተቆጥሯል። በቀጥታም ይሁን በተዛዋሪ፣ የህወሃት እጅ ይኑርበት አይኑርበት መረጃ ማቅረብ ባይቻልም አቶ ኢሳያስን ለማስወገድ በርካታ ሙከራዎችም ተደርገዋል። ይህኛው ሙከራ ግን እጅግ ቅርብ በሆነው የስለላው ክፍተኛ ታማኝ አማካይነት በመሆኑ ከጅምሩ ስኬት የሚገኝበት ተደርጎ ታላቅ ግምት ተወሰደበት።

ስምዖን ሁሉንም ጉዳይ ለፕሬዚዳንት ኢሳያስ ሲያስረዳ ምንም እንዳልሰሙ ሆነው ሰሙት። ይሁን እንጂ ይህ ሃሳብ ከተጀመረበት ቀን ጀምሮ እሳቸው በጣምራው ሰላያቸው አማካይነት ሁሉንም ጉዳይ ያውቃሉ። እናም ኦፕሬሽን እንዲካሄድበት እቅድ እንዲወጣ ምላጩ ተግባሩን እንዲገፋበት ተወሰነ።

ሻእቢያና ወያኔ ገና ከበረሃ ጀምሮ መረጃ መጠባባት፣ አብረው እየገዘገዙ አወዳደቁን ተደብቆ የማስላት፣ አንዱ ሌላውን ከጀርባ የማጥናት ልምድ አላቸው። ሻዕቢያ አባት በመሆኑ ስለላውን እንዳስተማረና እንደረዳ በርካታ ምስክሮች ቢኖሩም፣ አስተማሪ ከተማሪው አይበልጥም የሚለውን ተረት በመተረት ህወሃት ከድል በሁዋላ በዘርፉ ተመንጥቆ እንደሄደ ያምናል። ሻዕቢያ ደግሞ ይህ ተረት እንጂ እውነት አይደለም በሚል ሁሌም የበላይነቱ እጁ ላይ እንደሆነ ይናገራል።

እናም ምላጩ ህወሃት በምታመልከው በጌታቸው አሰፋ ተጠንስሶ የዳበረውን ኢሳያስን የማስወገድ እቅድ እንዴት እውን እንደሚያደርግ፣ ተባራዊ ለማድረግ በሚያስፈልጉ ጉርሻዎችና ዋና የስራ ማስኬጃ ጉዳይ ላይ በወኪሎቻቸው አማካይነት በጎረቤት አገርና አዲስ አበባ ሲመክሩ ይቆያሉ። ኦፕሬሽኑ ሲዘጋጅ ህወሃት ድንጽ አጥፍታ ቀጣዩን እቅዷን እያዘጋጀች ነበር። ውሎ አድሮ ሁሉም የዝመቻው እቅድ ተጠናቀቀና ኢሳያስ የሚወገዱበት የሁለት ግፋ ቢል የሶስት ቀን የዕቅድ ማከናወኛ ጊዜ ተቆረጠ።

Related stories   ከኢትዮጵያ ተዘረፏል የተባለውን ከፍተኛ ሃብት በማጣራቱና መረጃ በማሰብሰቡ ጉዳይ አሜሪካ እየሰራች ነው

የመጨረሻው እቅድ ላይ ኢሳያስ ሙሉ በሙሉ ለምላጩ ማረጋገጫ ሰጡ። እቅዱ ተግባራዊ እንዲሆን ኢሳያስ ኦፕሬሽኑ የሚተገበርበትን ማንኛውንም ነገር ለማድረግ ተዘጋጁ። ቢጭኑት አህያ ቢለጉሙት ፈረስ እንዲሉ ለተጠቀሱት የቁርጥ ቀናቶች ኢሳያስ ራሳቸውን ገደሉ።

የመጀመሪያው የሃምሳ በመቶ ክፍያ ተፈጸመ። ሻእቢያ ባዘጋጀው አካውንት ወያኔ ካላት የውጭ አገር አካውንቷ ገቢ አደረግች። ኢሳያስ ወደ ሳዑዲው ሮያል ሆስፒታል አቀኑ። በአምቡላንስ እንዲሄዱ ተደርጎ ወደ አውሮፕላን ገቡ። የሳዑዲ ሆስፒታል ኢሳያስ ሆስፒታል መግባታቸውን ማረጋገጫ ሰጠ። እቀዱ ወደ መጠቃለያው በመቃረቡ የኢሳያስ መሞት በቀጥታ በማይታወቁ ሚዲያዎች መናፈስ ጀመረ። ከዛም አየሩ ሁሉ በስርግና ምላሽ፤ እንዲሁም በቁጣ ታጠነ። አጅሬ ይህ ሁሉ ሲሆን ጉዳያቸውን የሚያውቁት እጅግ ውስን ሰዎች በመሆናቸው የወያኔ መንታ ኤጀንቶች መረጃ ማፈትለክ አልቻሉም። ይልቁኑም ” ሞተ” ለሚለው ዘመቻ ተጋለጡ። የወያኔ መንታ ሰላዮች ምንም አይነት መረጃ ማግነት አለመቻላቸው ድግስ እንዲጀመር እገዛ አደረገ።

አሁንም በተመዘገበና በተረጋገጠ በረራ ኢሳያስ አስከሬን ሆነው ወደ አገራቸው ሲገቡ ምስል ተቀርጾ ለእነ ጌታቸው አሰፋ ተላከ። ይህን ጊዜ የመጨረሻው አዋጅ የሚታወጅበት ቀነ ገደብ መጠናቀቁ ግድ ሆነ። ተተኪና ጊዜያዊ መንግስት የማደራጀቱ ስራ ቀጠለ። በዚህ መሃል ምላጩ ቀሪው ገንዘብ ገቢ እንዲሆን መመሪያ ሰጠ። በውለታው መሰረት ሁሉም ተፈጸመ።

በመጨረሻም በአስመራ የተረጋጋ ሹም ሽር እንዲደረግ የአቶ ኢሳያስ ልጅና የሻዕቢያን የውጭ ምንዛሬ የሚቆጣጠረው ታማኝ በቁም እስር እንዲቆዩ፣ ኢሳያስን የሚያልመኩ ተብለው የተፈረጁ መኮንኖች እንዲታሰሩ የወጣው እቅድ በሚስጢር ተግባራዊ እንዲሆን ምላጩ የሁለት ቀን ጊዜ ጠየቀ።

ይህ ሁሉ ሲሆን ኢሳያስ ራሳቸውን ስለገደሉ ምንም የተሰማ ፍንጭ አልነበረም። እናም በተባለው ጌዜ የሞት አዋጅና የሽግግር መንግስት አዋጅ ሲጠበቅ ኢሳያስ አፉውርቅ አዲስ አበባ መግባታቸው በዜና ብቻ ምስል አልባ ሆኖ ተነገረ። ለዳንኪራ ያሰፈሰፉ የኦፕሬሽኑ መሪዎች ይህን ሲሰሙ ፍየልና ጥጃ መለየት እንዳቃታት እረኛ ግራ ተጋቡ። ምስል ባለመቅረቡ ዜናውን በመጠራጠር ለመጽናናት ቢሞክሩም የወዲ አፍሆም ልጅ እንዳለ ሆኖ አራት ኪሎ ቤተ መንግስት ታዩ። በቅጽበት ለምን ኩራንቲ አይገቡም የሚል ወበቅ ተነዛ። ከህልፈትና የሽግግር መንግስት ዜና ወደ ኩራንቲ አስገዳጅ ህግ !!

Related stories   Ethiopia says 148 rebels from Eritrea surrender

እዚህ ላይ ወያኔ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ባስቸኳይ እያለች በውስጥ ለውስጥ ኢሳያስን ልታስወግዳቸው መስራቷና 26 ሚልዮን ዶላር መታጨዷ እንደማይገርምም። የሚገርመው ጭላንጭል ያሳይ የነበረው የሰላም ግንኙነት ላይቀጠል መበጠሱ ነው።

ኢሳያስ አንድ ሰው ናቸው። እሳቸው ነገም ያላፋሉ። ነገር ግን እሳቸውን አጥፍቶ ኤርትራ ላይ ሊተከል የሚታሰበውን አስተዳደር ድፍን ህዝብ ያውቀዋል። የኤርትራን ደጋማ አካባቢዎች ወደ ትግራይ ጠቅልሎ ቆላማው ግዛት ላይ ሌላ የክልል መንግስታት በማስፈን ኤርትራን ማፈራረስ እንደሆነ ማኒፌስቶውን መለስ በገሃድ ነገሮናል። አናም ከእነ ችግራችንም ቢሆን አገራችንን እንወዳለንና ይህ በየትኛውም ዘመን አይታሰብም።

በዚህ ኦፕሬሽን ወያኔ የከሰርችው ዶላር ሳይሆን የወደፊቱን የመጪው ትውልድ እምነትን ጭምር ነው። ይህንን ኪሳራ የሚጠግንና የሚያቃና ለማግኘት ሌላ ትግል ይጠይቃል። ሌላ ትውልድ፣ ሌላ ጊዜና ከባቢያዊ ምክንያቶች ይፈልጋል።

ኢሳያስ አዲስ አበባ ችግኝ ጣቢያ መርቀው በከፈቱ ማግስት የኤርትራ መካላከያ ጀነራል ፍሊጶስና የድህንነት ሰዎች አዲስ አበባ ገብተዋል። የሱዳን የድህንነት ባለስልጣናትና የመካላከያ ጀነራሎችም አብረው ነበሩ። ከዛ በፊት ኢሳያስ ሱዳን ሄደው ነበር። ይህ ሁሉን የሚሆነው ለምን ይሆን? ኤርትራ በፖለቲካ ደባና በተነደፈ ሴራ እንዲሁም በሚከፈላቸው የአፍሪካ ጉዳይ ሃላፊዎች አማካይነት ተፈርጃ እንዲቀረቀርባት ተደርጎ ነበር። በዚህም ሳቢያ ማእቀቡ ህዝቡን እጅግ በላው። ጎዳው። የአገሪቱንም ኢኮኖሚ አዳሸቀው። እስኪ እናንተም ሞክሩት። መቼም እንደ እኛ ሰላሳ ዓመት አትችሉትም። እንዲህ የተጫወታችሁበትን፣ ንብረቱን ነጥቃቹህ ያሳደዳችሁትን ሕዝብ ዛሬም ለትበትኑት ላይ ታች ትላላችሁ!!

ይህንን የጻፍኩት ለመነሻ ነው። የተነካካ ጉዳይ ቢሆንም ምላጩን ለማስተዋወቅ ፈልጌ ነው!! ይህ ጽሁፍ የጸሃፊውን ሃሳብ ብቻ የሚያንጸባርቅ ነው – አዘጋጁ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *