Share and Enjoy !

Shares

ሰሞኑንን ከመስከረም ሰላሳ በሁዋላ መንግስት እንደማይኖር፣ የመከላከያ ሰራዊት፣ የፌደራል ፖሊስ፣ የደህንነት ተቋማትና በየእርከኑ ያለው መዋቅርም መታዘዝ እንደሚያቆሙ በይፋ መገለጹን ተከትሎ መንግስት ማብራሪያ ለመጠቅ መዘጋጀቱ ተሰማ።

የዛጎል መረጃ ሰጪዎች እንዳሉት መንግስት በሕጋዊ መንገድ ማብራሪያ ለመጠየቅ ዝግጅት የጀመረው እነዚሁ ክፍሎች የጊዜ ገደብ አስቀምጠው ” መንግስት አይኖርም” ማለታቸውን ተከትሎ ነው። ይህ ጥሪ ሲተላለፍ ምን ለማለትና ምን ዓይነት ዝግጅት ተደርጎ ስለመሆኑ ነው መንግስት ማብራሪያ የሚጠይቀው።

“ከመስከረም ሰላሳ በሁዋላ መንግስት ስለማይኖር እንዳሻችሁ ሁኑ” የሚለው ጥሪ አገሪቱን ወደ የትኛው አቅጣጫ ለመውሰድ ታስቦ እንደሆነ፣ እንዲሁም አገሪቱ አደጋ ላይ ብትወድቅ ምን አማራጭ ሃይል እንዳዘጋጁ ነው ማብራሪያ የሚሰጡበት ጉዳይ።

ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የሚመሩት የፌደራል አቃቤ ህግ የክስ ሰነድ እያዘጋጀ ሲሆን ማብራሪያ እንዲሰጡ የሚጠየቁት ክፍሎች ፈቅደው ማብራሪያ ከሰጡ ክስ ላይመሰረት እንደሚችል የዜናው ምንጮች አስታውቀዋል። ይህ የሚሆነው በማብራሪያቸው ይቅርታ ከጠየቁና ካስተባበሉ ብቻ ነው።

Related stories   በሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ከሃሰተኛ መረጃ ራሳቸውን እንዲጠብቁ ጥሪ ቀረበ፣ የተጭበረበረ መረጃ ተሰራጭቶ ነበር

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከሰላማዊ አካሄድና ከውይይት ውጪ ሌላ አማራጭ እንደማያስኬድ፣ መንግስትም እንዲህ ያለውን አካሄድ እንደማይታገስ ይፋ ማድረጋቸው ከላይ ከተገለጸው ጋር እንደሚስማማ ምንጮቹ ይፋ አድርገዋል።

በተያያዘ ዜና የመንግስት የጸጥታ አካላት ስማቸውን ይፋ ያላደረጓቸው ክፍሎች ክልል ከተቀመጡ ክፍሎች ጋር በመሆን መንግስትን እጁን ለመጠምዘዝ እየሰሩ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ አግኝቷል። ለዚሁም ሲባል በጀት መመደቡና በጀቱንም እነማን እንደሚያንቀሳቅሱና እንደሚያሰራጩ የሰውና የሰነድ ማስረጃ አሰባስቧል። እንደ ዜናው ሰዎች ከሆነ መንግስት አይኖርም የሚለው ጥሪ ታስቦበት በእቅድና በትሥሥር የሚሰራ ነው።

አቶ ጃዋር መሐመድና አቶ ልደቱ አያሌው መንግስት ከመስከረም 30 በሁዋላ አይኖርም ማለታቸው አይዘነጋም። የሽግግር መንግስት እንዲመሰረት በይፋ ጠይቀዋል። ይህንን በመቃወም በርካታ ድርጅቶችና ክልሎች የሽግግር መንግስት የሚባለውን ጥያቄ እንደማይቀበሉትና ቅድሚያ ለወረሽኙ እንዲሰጥ እየተየቁ ነው።

Related stories   "ሬንጀርስ" የሚባል በመሳሪያ የተደገፈ ዝርፊያ የሚፈጽም የማፍያ ቅርጽ ያለው ቡድን በቁጥጥር ስር ዋለ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *