“Our true nationality is mankind.”H.G.

የትብብር ለህብረ-ብሔር ዲሞክራሲያዊ ፊዴራሊዝም ጥምረት – “ሁላችንም እኩል ነን፣ ነገር ግን አንዳንዶቻችን ከሁላችሁም የበለጠን እኩል ነን”

By Mushe Semu

የትብብር ለህብረ-ብሔር ዲሞክራሲያዊ ፊዴራሊዝም ጥምረት (ኦብነግ፣ ኦነግ፣ኦፌኮ፣አረና ወዘተ) ሚያዝያ 26 ቀን፣ በጋራ ባወጣው መግለጫ ላይ “ውይይቱ እና ድርድሩ የ2012 ምርጫን ለመወዳደር ተመዝግበው መስፈርት ያሟሉ የፖለቲካ ድርጅቶችንና ጥምረቶችን “ብቻ” ያሳተፈ መሆን አለበት” የሚል ቃል በቃል ዝግ የሆነና ያለቀለት ገደብ ጥሏል።

አንድም አስገዳጅና ሕጋዊ ስልጣን የሌላቸው ሃይሎች፣ ለውይይትና ለስልጣን ድርድር ማን እንደሚሳተፍና ማን ውጭ እንደሚቀር በመግለጫ ሲያውጁ፣ “ሁላችንም እኩል ነን፣ ነገር ግን አንዳንዶቻችን ከሁላችሁም የበለጠን እኩል ነን” እያሉን እንደሆነ ግልጽ ነው።

በዚህ መግለጫ መሰረት ያለ ሕጋዊ ማንዴት አዲስ ለሚፈጠረውም ሆነ ለነባሩ ተቃዋሚው ያስቀመጡት መስፈርት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ለስልጣን ክፍፍል ሳይሆን ለሀገር ዘላቂ ጥቅምና ለሰላማዊ ሽግግር ሲባል በጎ አስተዋጽኦ ማድረግ የሚችሉ በርካታ ታዋቂ ግለሰቦች፣ “ምሁራን”፣ የሙያ ማህበራት፣ የዴሞክራሲና የሰላም ተቋማት በሙሉ ተገልለዋል። ጥምረቱ፣ በራሱ ጊዜና በብቸኝነት በመወሰን “ሁሉን አቀፍ ከተባለለት ውይይትና ድርድር” ተደራዳሪዎችንና የስልጣን ተጋሪዎችን ከወዲሁ በማስወገድ “በእኩልነት፣ ሁሉን አካታች” ይሆናል ያሉትን ውይይት ገና ከጅምሩ ገደል ከተውታል።

Related stories   የተላላኪው ጠበቃዎች

እንቀጥል፣ በመግለጫው መሰረት ጥሪው የተከናወነው ለስልጣን መዳረሻ የሚሆን ውይይትና ድርድር ለማካሄድ ነበር። ነገር ግን፣ ገና ውይይቱ ሳይጀመር በአንድ ጥምረት መግለጫ ብቻ የተሰናበቱትን ተቃዋሚዎችና የተረሱትን ዜጎች አስቧቸው፣ በዚህ መገለልና መረሳት ላይ እስከዛሬ የተጠራቀመ ድርጅታዊ ክልላዊና ቡድናዊ ቁጣ፣ ብሶትና የመገፋት ስሜት ታክሎበት ሊቀሰቀሰ የሚችለውን ጫጫታ፣ ሁከት፣ አለመረጋጋት፣ ስደት፣ መፈናቀልና ሞት ጨምሩበት።

አሁንም እንቀጥል። ሕግና ስርዓት የማስከበር አቅም፣ ሃይልና ማንዴት የሌላቸው ምርጦች፣ የፈለጉትን አግልለውና ቅድመ ሁኔታ ደርድረው ሲያበቁ፣ ስልጣንን ከገዢው ፓርቲ ጋር እስኪከፋፈሉ ድረስ “መንግስት” ተገፋን የሚሉትን ዜጓች የእኩልነት መብት እየረገጠ፣ የሕይወትና የንብረት ዋጋ እያስከፈላቸውና እየቀጣቸው “ሁከትን” በማብረድ” ፣ “ሰላም በማስፈን” የአምባገነን ስራ እንዲሰራ ይጠበቃል።

Related stories   ሻለቃ ሰከን ይበሉ እንጂ! – ባይሳ ዋቅ-ወያ

በተቃራኒው ደግሞ፣ በሕገ መንግስቱ የዜግነት መብት ላይ ተመስርቶ “መንግስት” በገለልተኝነትና በእኩልነት መርህ ላይ ተመስርተው፣ ሁሉንም ዜጎች በሀገራቸው ጉዳይ የመወያየት፣ በውይይቱ ከሚገኙ ትሩፋቶች የመጠቀምና ስልጣንንም ቢሆን በድርድር የመጋራት መብታቸውን የማስከበር ግዴታ አለበት። እንግዲህ ጨዋታው ፈረሰ ዳቦ ተቆረሰ ሲባል ከ “መሃል” ሳይሆን “ከ”መጀመርያው” መጀመር ግድ ይላል ማለት ነው።

እንደሚታወቀው፣ የምርጫ ቦርድን መስፈርት አሟልቶ ሰርተፊኬት መያዝ ለምርጫ ውድድር ብቁ ያደርጋ ይሆናል እንጂ በሀገር ጉዳይ የመወሰን የተለየ የዜግነት መብትና ስልጣን አይሰጥም። ሁሉም በሀገሩ ጉዳይ እኩል፣ የመምከርና የመወሰን መብትና ስልጣን አለው። በሀገር ጉዳይ እንደ አዲስ መምከር ከተጀመረ ደግሞ ውይይት፣ ድርድር፣ ስልጣን ክፍፍል ከመጀመሩ በፊት ይመለከተኛልና በሂደቱ መሳተፍ እፈልጋለሁ የሚል የተደራጀውንም ሆነ ያልተደራጀውን ዜጋ ከመሰረታዊ መብቱ ማግለል “አምባገንነት” ነው።

Related stories   ሕዝብን ማን ይሰራዋል?

ገና ከጅምሩ፣ ሁሉንም አሳታፊ የተባለለት ውይይት በዚህመንገድ መስመሩን እየሳተ መሆኑን መግለጫ በቂ ምስክር ሊሆን ይችላል። ስጋታችንም፣ በሽግግር ስም አምባገነንነት እንዳይነግስ በቂ ተሞክሮ ስላለ ነው። የገዢውን ፓርቲ የአምባገንነትን ስጋት ለመግታት እንዲቻል ፣ በጊዜ የተገደበ፣ በስልጣኑ የተወሰነ (Minimal) መንግስት በማድረግ በአንድ በኩል ኮሮናን እየተከላከለ፣ በሌላ በኩል ዴሞክራሲያዊና ተአማኒነት ያለው ምርጫ እንዲያስፈጽም፣ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በምርጫው ስርዓትና አካሄድ ላይ በውይይት፣ በግምገማና በድርድር … የዳበረ የጋራ ፍኖተ ካርታ ማዘጋጀት ይቻላል።

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0