“Our true nationality is mankind.”H.G.

” የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሰብዓዊ መብት ተቋም ሪፖርት ሚዛናዊነት የጎደለው ነው »የአማራ ክልል መንግሥት

የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሰብዓዊ መብት ተቋም ሰሞኑን ያወጣው ሪፖርት ሚዛናዊነቱን ያልጠበቀ በመሆኑ የአማራ ክልል መንግስት እንደማይቀበለው አስታወቀ።የአማራ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ሪፖርቱ በኦሮሚያና አማራ ክልሎች ላይ አተኩሮ መውጣቱ ራሱ ሌላ ትርጓሜ አለው ብለዋል፡፡

የሁለቱን ታላላቅ ህዝቦች የቆየ አንድነትና ወንድማማችነት ለማፍረስ ሲሰሩ የነበሩ የተሳሳቱ ትርክቶችን የማመላከት እይታ ያለው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ተቋሙ  ከአማራ ክልል የፀጥታና ሰላም ግንባታ ቢሮ ወስጀዋለሁ የሚለውን መረጃ ባልተሟላ ሁኔታ የተጠቀመበት በመሆኑና የክልሉ መንግስትም ያልተወያየበት፣ የጋራ ያላደረገው በመሆኑ እውቅና እንደማይሰጠው ነው ዋና ዳይሬክተሩ ያመለከቱት፡፡

Related stories   “ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን በአንድነት በመከባበር፤ በመተሳሰብ እና በመረዳዳት ሊያከብር ይገባል”

በዓመቱ መጀመሪያ በምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር የተፈጠሩ ግጭቶችን በተመለከተ አማራው በቅማንት ማህበረሰብ ላይ እንደፈጸመ የሚተነትነው የአምነስቲ ሪፖርት በተፈጠረው ግጭት የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ቅማንቶች ብቻ ናቸው ብሎ ማቅረቡም ሚዛን የጎደለው ነው ብለዋል።አጠቃላይ ችግሩን ለመፍታት የተደረጉ ጥረቶችን፣ የፀጥታ ኃይሉ የከፈለውን መስዋዕትነት ያላካተተና በመሰረታዊ ጭብጦች ላይ ያልተመሰረተ ሪፖርት በመሆኑ የአማራ ክልላዊ መንግስት ተቋሙ ያቀረበውን ባለ 50 ገፅ ሪፖርት አይቀበለውም ብለዋል፡፡

Related stories   እስራኤል አልጃዚራ ቴሊቪዥን፣ አሶሲየትድ ፕሬስና ሌሎች ሚዲያዎች የሚጠቀሙበትን ህንጻ አወደመች

dw amharic

Share and Enjoy !

Shares
0Shares
0