ZAGGOLE – ዛጎል

“Our true nationality is mankind.”H.G.

“ጆርጅ ፍሎይድን አንቆ የገደለው ፖሊስ ‘አስቦና አቅዶ’ ነው”

በምድር አሜሪካ እንደ ሰደድ እሳት የተዛመተ ተቃውሞን ያስነሳው የጆርጅ ፍሎይድ ጉዳይ ዛሬም አልበረደም። በበርካታ የአሜሪካ ግዛቶች ምሽቱን ዘረፋና ንብረት ማውደም፣ መኪናዎችን ማቃጠል እንዲሁም ሰላማዊ ተቃውሞዎች እየተፈራረቁ ሲደረጉ ነበር።

በዚህ ተቃውሞ መሀል የጆርጅ ፍሎይድ ቤተሰብ ጠበቃ ግድያውን በተመለከተ አዲስ መረጃን ይፋ አድርጓል። ነጩ ፖሊስ በጆርጅ ፍሎይድ አንገት ላይ እጅ በኪስ አድርጎ በጉልበቱ ሲቆምበት ፍሎይድ ትንፋሽ አጥሮት እየሞተ እንደነበር አሳምሮ የተገነዘበ ሲሆን፤ ነፍሱ እስክትወጣ ድረስ በዚያው ሁኔታ ተጭኖት መቆየቱን የሚያሳዩ ተጨማሪ የተንቀሳቃሽ ምሥል መረጃዎችን ማግኘቱን ተናግሯል።

Related stories   በአቡነ ማቲያስ መልዕክት ሳቢያ - ሲኖዶስ በመቆጣቱ አስቸኳይ ስብሰባ ተደርጎ የተግሳጽና የማስተካከያ መግለጫ ሊሰጥ ነው

በዚህም ምክንያት ክሱ የ3ኛ ደረጃ የግድያ ወንጀል ሳይሆን መሆን ያለበት የ1ኛ ደረጃ የግድያ ወንጀል ሊሆን ይገባል ሲል ጠበቃው አስታውቋል።

የሜኒያፖሊስ የፖሊስ መኮንን የሆነው ተከሳሽ ዴሪክ ቾቪን ክስ የተመሰረተበት 3ኛ ደረጃ የግድያ ወንጀል በሚል ነው።

የሟች ቤተሰብ ጠበቃ ቤንጃሚን ክራምፕ ለሲቢኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ እንደተናገረው ክሱ አሁኑኑ መሻሻል ይኖርበታል።

“እኛ እንደምናስበው ክሱ 1ኛ ደረጃ ግድያ ነው መሆን ያለበት፤ ምክንያቱም ለ9 ደቂቃ አንገቱን ሲጫነው ትንፋሹ ጨርሶውኑ እንዲጠፋ አስቦና አቅዶ ነበር። በዚያ ላይ ‘ትንፋሽ አጥሮኛል’ እያለ እየለመነው ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ ነው የጭካኔ ድርጊቱን የገፋበት” ብሏል ጠበቃው።

የሟች ቤተሰብ ጠበቃ ለሲቢኤስ ቴሌቪዥን ጨምሮ እንዳስረዳው የፖሊስ መኮንኑ፤ ሟች ፍሎይድ ትንፋሽ አጥሮት መንፈራገጥ ማቆሙን አስተውሎ እንኳ ከአንገቱ ሊነሳለት ፍቃደኛ አልነበረም። ይህም የሚያሳየው ድርጊቱን የፈጸመው ሆን ብሎ አስቦበትና አቅዶ መሆኑን ነው።

Related stories   አውሮፓ ህብረት እየተሽኮረመመ ታዛቢ ሊልክ ነው
ዴሪክ ቾቪን
አጭር የምስል መግለጫዴሪክ ቾቪን

ጠበቃው ሌላ ያነሳው መከራከርያ ከፖሊስ አገኘሁት ባሉት ሌላ ተንቀሳቃሽ ምሥል ላይ የተመሰረተ ነው። ይኸውም በወቅቱ ከነበሩት ፖሊስ መኮንኖቹ አንዱ “አሁን የልብ ምቱ ቆሟል በጀርባው እናዙረው” በሚልበት ጊዜ ተጠርጣሪው ፖሊስ ዴሪክ ቾቪን “ተወው ባክህ በዚሁ ሁኔታ (ቆልፈን) እናቆየዋለን” ሲል ይደመጣል። ይህም ግድያውን ሆን ብሎ አስቦ መፈጸሙን የሚያስረዳ ማስረጃ ነው ሲል ተከራክሯል።

ጠበቃው ሌላ ያነሱት አዲስ መረጃ ደግሞ ገዳይና ሟች ከዚህ ክስተት በፊት ይተዋወቁ እንደነበረ ነው። ትውውቃቸው በምን ደረጃ እንደነበር ግን አላብራሩም። ይህ በእንዲህ እንዳለ ምሽቱን በፊላደልፊያ የተካሄደን የተቃውሞ ሰልፍ ተከትሎ ከፍተኛ ዝርፍያ ነበር ተብሏል።

Related stories   የፌደራልና የክልል ፖሊስ አዲስ የአደረጃጀት ሰነድ ለጠቅላይ ሚንስትሩ ቀረበ

በፊላደልፊያ የፖሊስ መኪናዎች ከመቃጠላቸውም በላይ የልብስ ቤቶች፣ መድኃኒት ቤቶችና ሌሎች ሱቆች ተዘርፈዋል።

ፕሬዝዳትን ትራምፕ በትዊተር ሰሌዳቸው ላይ የፊላደልፊያ ተቃዋሚዎች አደብ እንዲገዙ ካልሆነ ግን ልዩ ኃይል እንደሚያዘምቱባቸው አስጠንቅቀዋል።

የፍሎይድ ግድያ ጉዳይ የፈርጉሰኑን ማይክል ብራውንና የኒውዮርኩን ኤሪክ ጋርነርን ግድያዎች ተከትሎ በአሜሪካ ከፍተኛ ተቃውሞ እንዲቀሰቀስ ምክንያት የሆነ ዘረኝነት የተጸናወተው ተግባር ሆኖ ተመዝግቧል።

ይህ ድርጊት “ብላክ ላይቭስ ማተር” የሚለው የጥቁሮች የመብት እንቅስቃሴ ዳግም እንዲፋፋም ያደረገ ሆኗል።

ይህን የጆርጅ ፍሎይድን ግድያ ተከትሎ ከአሜሪካ ውጪ በበርካታ የአውሮፓ ከተሞችም ተቃውሞዎች የተካሄዱ ሲሆን በዩናይትድ ኪንግደም መዲና ለንደን በርካቶች አደባባይ ወጥተው ድምጻቸውን አሰምተዋል።

Read the original story – BBC Amharic