በአዲስ አበባ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 889 ደርሷል

በአዲስ አበባ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 889 ደርሷል።በዛሬው እለት የኮሮና ቫይረስ ከተገኘባቸው 85 ሰዎች ውስጥ 72 ሰዎች ከአዲስ አበባ መሆናቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

ይህን ተከትሎም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በከተማዋ የቫይረሱ ስርጭት በክፍለ ከተሞች ደረጃ የሚያመላክት መረጃ አውጥቷል።በዚህም በአዲስ አበባ በ24 ሰዓት ውስጥ ቫይረሱ ከተገኘባቸው 72 ሰዎች መካከል 28 ሰዎች ከአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ እንዲሁም 12 ሰዎች ከቦሌ ክፍለ ከተማ ይገኛሉ።

በተጨማሪም አራዳ ክፍለ ከተማ 8፣ ልደታ 7፣ የካ 5 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።በተጨማሪም አቃቂ ቃሊቲ 4፣ ቂርቆስ 3፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ 2 ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ተረጋግጧል።በአጠቃላይም እስካሁን በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ 251 ሰዎች ቫይረሱ ሲገኝባቸው በልደታ 158 እንዲሁም በጉለሌ ክፍለ ከተማ 122 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

የዉሃኑ ሀኪም ከሞተ ከወራት በኋላ እጮኛው ወለደች

Related stories   የትህነግ "ውሮ ወሸባዬ" - የመንግስት ሩጫ - የሃላኑ የኢትዮጵያን ቋንጃ የመበጠስ የእባብ አካሄድና ባንዳዎች!

የካቲት አጋማሽ ላይ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው ቻይናዊ እጮኛ ሴት ልጅ በሰላም ተገላግላለች። ዶ/ር ፒንግ ይንሃን ሲሞት መላው ቻይናውያን ሀዘናቸውን ገልጸው ነበር። ዶክተሩ ኮሮናቫይረስ መጀመሪያ በተገኘባት ዉሃን ከተማ ይሠሩ ከነበሩ ሀኪሞች አንዱ ነበር።

ህሙማንን ለማከም ሲል የካቲት መጀመሪያ ላይ ሊካሄድ የነበረውን ሠርጉን ሰርዟል። በዉሃን በከፍተኛ ሁኔታ በታማሚዎች ተጨናንቀው ከነበሩ ሆስፒታሎች በአንዱ ውስጥ ነበር የሚሠራው። ሕይወቱ ሲያልፍ እጮኛው የስድስት ወር ነፍሰ ጡር ነበረች።

በቻይና ጥንዶች ከመጋባታቸው በፊት የሠርግ ልብስ ለብሰው ፎቶ ይነሳሉ። ሀኪሙ ሲሞት የቻይና መገናኛ ብዙሃን ከእጮኛው ጋር የተነሳውን ፎቶዎች ያሳዩ ነበር። የሠርጋቸው መጥሪያ ሳይላክ በሀኪሙ ቢሮ ውስጥ እንደተቀመጠ ይገኛል። የጨቅላዋ መወለድ ‘መባረክ’ ነው ያሉ በርካቶች ቢሆኑም፤ ‘ጀግና’ አባቷን በማጣቷ ሀዘናቸውን ገልጸዋል።

ሐዋሳ-የኮሮና ተሕዋሲ በደቡብ ኢትዮጵያ

አዲስ አበባ ዉስጥ የግንባታ ሥራ በመቀዝቀዙ ምክንያት ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ የሚመለሱ የአካባቢዉ ተወላጆች የኮሮና ተሕዋሲን ያሰራጫሉ የሚል ስጋት ማሳደሩን የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ አስታዉቋል።በኮሮና ተሕዋሲ መያዛቸዉ የተረጋገጠ አምስት ሰዎች ባለፈዉ አርብ ሲዳማ ዞን መግባታቸዉን የቢሮዉ ኃላፊዎች አስታወቀዋል።

Related stories   ደመቀ መኮንን በፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሚመራ የአውሮፓ ህብረት ልዑክ ጋር ተወያዩ

የሐዋሳዉ ወኪላችን ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ የቢሮዉን ባለሥልጣናት ጠቅሶ እንደዘገበዉ ከአምስቱ ሰዎች 3 ለይቶ ማቆያ ቢገቡም 2 ግን እስከ ዛሬ ቀትር ድረስ ያሉበት አልታወቀም።ባለፉት ሶስት ቀናት በኮሮና ተሕዋሲ ተለክፈዋል ወይም ከተለካፊዎች ጋር ንኪኪ አላቸዉ ተብለዉ የተጠረጠሩ 411 ሰዎች ሐዋሳ፣ ይርጋለምና በንሳ ከተሞች በሚገኙ ለይቶ ማቆያ ጣቢያዎች ገብተዋል።

የኮሮና ተሕዋሲ ስርጭት በኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ ዉስጥ በኮሮና ተሕዋሲ የሚለከፉ ሰዎች ቁጥር ዛሬም እንደመሰንበቻዉ እያሻቀበ ነዉ።የጤና ሚንስቴር ዛሬ ባሰራጨዉ የ24 ሰዓት ዘገባዉ እንዳስታወቀዉ 85 ተጨማሪ ሰዎች በተሕዋሲዉ መለከፋቸዉ ተረጋግጧል።ሚንስቴሩ እንዳለዉ 85ቱ ሰዎች በተሕዋሲዉ መለከፋቸዉ የተረጋገጠዉ በ2926 ሰዎች ላይ ባደረገዉ ምርመራ ነዉ።

በኮሮና ተሕዋሲ መለከፋቸዉ የተረጋገጠዉ ሰዎች ቁጥር 1257 ደርሷል።217 ሕሙማን ተሽሏቸዋል።ከዚሕ ቀደም በተሕዋሲዉ ተለክፎ ኤካ ኮቴቤ ሕክምና ሲደረግለት የነበረ አንድ የ30 ዓመት ኢትዮጵያዊ ወጣት ሞቷል።ወጣቱ ተጓዳኝ ሕመም ነበረበት ተብሏል።የወጣቱ ሞት ኢትዮጵያ ዉስጥ በኮቪድ 19 በሽታ የሞቱትን ሰዎች ቁጥርን 12 አድርሶታል።

Related stories   Ethiopia’s transition misrepresented. Reply to Obang Metho

ሞስኮ-የሩሲያ ዉሳኔ፣የኮሮና ተሕዋሲ ስርጭት

ሩሲያ በቅርቡ ያፀደቀችዉን መድሐኒት በመጪዉ ሳምንት ለኮቪድ 19 ሕሙማን መስጠት እንደምትጀምር አስታወቀች። ሮይተር ዜና አገልግሎት የሩሲያ ባለስልጣናትን ጠቅሶ እንደዘገበዉ ፀረ ተሕዋሲዉ መድሐኒት በሽተኞችን ብቻ ሳይሆን በሩሲያ የጤና ስርዓት ላይ ያረፈዉን ጫና ለማቃለል ይረዳል።

የሮይተር ዘገባ የመድሐኒቱን ዓይነት፤የመፈወስ አቅሙንና ሙከራዉን ግን አልጠቀሰም።ይሁንና ጃፓን በተመሳሳይ መድሐኒት ላይ ሙከራ ማድረጓን አመልክቶ ቶኪዮ ለበሽተኞች ለመስጠት ገና አለመወሰኗን አስታዉቋል።የኮሮና ተሕዋሲ ባጭር ጊዜ በከፍተኛ ፍጥነት የተሰራጨባት ሩሲያ በተሕዋሲዉ በተያዙ ሰዎች ቁጥር ከዩናያትድ ስቴትስና ከብራዚል ቀጥላ ከዓለም የሶስተኛነቱን ደረጃ ይዛለች።

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *