በአማራ ክልል በሁለት የተለያዩ ቦታዎች ላይ ትናንት እሁድ ሁለት የወረዳ ባለስልጣናትና አንድ የፖሊስ አባል በጥይት መገደላቸውን ቢቢሲ አረጋገጠ።

ግድያዎቹ የተፈጸሙት ትላንት ግንቦት 23/2012 ዓ.ም የአማራ ክልል በሰሜን ወሎ ዞን በራያ ቆቦ ወረዳ እና በክልሉ መዲና በባህር ዳር ውስጥ ነው።

የራያ ቆቦ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ስዩም መስፍን እና የወረዳው የሕዝብ ሠላምና ደኅንነት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መንገሻ ሞላ ህይወታቸው ያለፈው ሕግ ለማስከበር ጥረት ሲያደርጉ መሆኑን የወረዳው የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት የቡድን መሪ አቶ አየነ አማረ ለቢቢሲ ገልጸዋል።

አመራሮቹ በወልዲያ ከተማ የነበራቸውን ሥራ አጠናቀው ወደ ቆቦ ከተማ በመመለስ ላይ እያሉ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በሚጻረር እና ለኮሮናቫይረስ ስርጭት በሚያጋልጥ መልኩ አንድ የባጃጅ አሸከርካሪ ስድስት ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ ተመልክተው ሕግን ለማስከበር መሞከራቸውን ገልጸዋል የቡድን መሪው።

Related stories   “አማራ ከትግራይ ክልል ውጣ”አሜሪካ ”ግፍ” ታውቃለች? ጋምቤላ፣ ማይካድራ፣ ራያ፣ በደኖ፣ሆራ፣ ዋተር…ምን ተደርጓል?

ይህንንም ተከትሎ ከሮቢት ከተማ ወጣ ብላ በምትገኝ መንጀሎ 036 ቀበሌ አካባቢ ሁለቱ አመራሮች ከመኪና ወርደው የተመለከቱትን ሕግን የተላለፈ ድርጊት ለማስቆም ሲጥሩ ከሁለት ሰዎች በተተኮሰ ጥይት ተመትተው ወዲያው ሕይታቸው ማለፉን ተናግረዋል።

በክስተቱ ሟቾቹ በነበሩበት አሽከርካሪ ውስጥ የነበሩ ሌሎች ሰዎች በጥቃቱ ምንም ጉዳት ያልደረሰባቸው ሲሆን ግድያውን ተከትሎ የጸጥታ ኃይሎችን ከሮቢት ከተማ ይዘው በመመለስ ተጠርጣሪዎቹ ለመያዝ ጥረት መደረጉን አመልክተው፤ የድርጊቱ ፈጻሚዎች ይዘዋት የነበረችውን ባለጎማ ተሽከርካሪ (ባጃጇ) ጢሻ ውስጥ ደብቀው መሰወራቸውን አስታውቀዋል።

Related stories   WAR, JUSTIFIABLE WAR? "ጦርነት ለሃገር ህልውና" by Dr. Haymanot

ከግድያው በኋላ ፖሊስ ምርመራ በማካሄድ ድርጊቱን ፈጽመዋል ተብለው የተጠርጠሩትን ሰዎች ማንነት ለመለየት የቻለ ቢሆንም እስካሁን በቁጥጥር ስር አለመዋላቸው ታውቋል።

የወረዳ አመራር አባል የሆኑት ሁለቱም ሟቾቹ አቶ ስዩምና አቶ መንገሻ ባለትዳር እና የአንድ አንድ ልጆች አባት ነበሩ። የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው መፈጸሙንም ቢቢሲ ከቤተሰቦቻቸው ለማወቅ ችሏል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን መምሪያ ኮማንደር መሠረት ደባልቄ ለክልሉ መገናኛ ብዙሃን እንደተናገሩት ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ ፖሊስ ከአካባቢው ሕብረተሰብ ጋር በመተባበር እየሠራ መሆኑን አስታውቀዋል።

Related stories   “ፍትህ ለትግራይ! ሞት ለመከላከያ ሰራዊትና … በትግራይ ሕዝብ ስም ትህነግ የመዘዙ ምንጭ ላይሆን?

በተመሳሳይ በትላንትናው ዕለት ሻምበል አዛዥ የነበረው ምክትል ኢንስፔክተር ጀግኔ ዋሱ የተባለ የፖሊስ አባል ባህር ዳር በተከተኮሰበት ጥይት ህይወቱ ማለፉንም ኮማንደር መሠረት አስታውቀዋል።

እንደ ኮማንደር መሠረት ከሆነ ባህርዳር ከተማ ሰባታአሚት በሚባል ቦታ በለቅሶ ሥነ ሥርዓት ወቅት ጥይት የሚተኩሱ ሰዎችን ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡና ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጥረት በሚያደርግበት ጊዜ ተተኩሶበት የጸጥታ ኃይል አባሉ ህይወቱ እንዳለፈ ገልጸዋል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን እንዳለው ድርጊቱን ተከትሎ በግድያው እጃቸው አለበት የሚባሉ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ክትትል እያደረገ እንደሆነ አመልክቷል።

Read the original story – BBC Amharic

Share and Enjoy !

Shares

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *